Solomon Tekalegne ሠለሞን ተካልኝ ግርማዊ ተፈሪ

ዱሮ ገና ሠለሞን ተካልኝ ያቀነቅናቸውን የነበሩ የነፃነት ዜማዎች ደጋግሜ ስስማ፤ ይህ ሰው ቢያንስ በርታ ሊባል ይገባል በሚል የህዝብ ልጅ ነው ብዬ በግጥም አሞግሼው ነበር። ከዚያ ገልበጥ ብሎ ወደ አዲስ አበባ በመብረር የቆጥ የባጡን ሲዘላብድ ስሰማው፤ አይ ሰው መሆን ምነው ሰውየው እንዲህ ተጃጃለ ድሮስ ከሞኝ ምን ይጠበቃል እያልኩ አላግጨ ዝም አልኩ። ሰሞኑን ደግሞ ‘አወጣሁ’ ያለው ዘፈን አይሉት ምን ስሰማው፤ አይ ይህ ሰው ጃዝ ብለውታልና ዋ ካልተባለ የበለጠ ሊሸናብን ነው አልኩና እነሆ ይችን ወረቀት ጫርኩ። ዘፋኝ ነውና በግጥም ብፅፍለት ዘፈን እንዳይመስለው እነሆ ተ - ውሽ ሠለሞን ብየ በስድ ንባብ ልሰደድበት ጀመርኩ።

 

ሠለሞን ተካልኝን በአካል አውቀዋለሁ። ከዕለታት አንድ ቀን የሠላምታ ልውውጥና ተቀምጦም የማውራት ዕድል አጋጥሞን ነበር። በፀባይም ቢሆን አሜሪካን ሀገር ተቀምጦ የሴት ምግብ ቤት አሳላፊን ቂጥ ጨብ አድርጐ በጥፊ መቶ እንዲሳም የሚፈልግ፣ ዕድሜው አስራ አራት ዓመት ላይ የቆመ፣ ዘገመተኛ፣ ድንዝዝ ወደል እንደሆነ ሀገር ያወቀው ፀሓይ የሞቀው ነው። ከሠለሞን ተካልኝ ጋር አብሮ ኖሮ ስለዚህ ፍጥረት ጥሩ ምስክርነት የሚሰጥ ሰው የሱ ብጤ ዘገምተኛ ብቻ ነው። ለነገሩ አቶ መለስ እንኳን ይህንን የሠለሞን ተካልኝ ሙገሳ የሚያስቃቸው እንጂ የሚያስደስታቸው አይሆንም።

 

ከአሁን በፊት ለሠለሞን ተካልኝ የሙገሳ ግጥም መፃፌን ያወቀ አንድ ወዳጄ፤ “አንተ ሰው በጤናህ ነው ይህን በሽተኛ የሆን ፍጥረት አሞግሰህ የምትፅፈው” ብሎ ወቅሶኝ ነበር። በጊዜው ግን “ለነፃነት የዘመረ ይሞገስ ነፃነቱን ብሎልና” የሚል መልስ ነበር የሰጠሁት። በፀሐፊነታቸውና በሙዚቃ አቀናባሪነታቸው ወደር የሌላቸው አንገታቸውን ደፍተው ሹመትና ጭነት ሳይፈልጉ የህዝብን ብሶትና የሀገርን ለቅሶ በመቃኘት ጉሮሮውን የተጠቀሙትበን ደራሲዎች መልዕክት ሲያንጐራጉር ለብዙ ዓመታት ከርሞ አንዱም ቃል የገባው አለመሆኑ ምን አይነት የተጃጃለ ፍጡር እንደሆነ የሚያሳይ እውነታ ነው።

 

ለነገሩ ሠለሞን ተካልኝ አሜሪካን ሀገር ከረገጠ እነሆ ቢያንስ አስራ አራት ዓመት ይሆነዋል። እርሱ አሜሪካ ሀገር ተቀምጦ ቢያንስ የኦባማን፣ የቡሽንና የክሊንተንን አስተዳደሮች ያየ ይመስለኛል። በእኛይቱ ኢትዮጵያ ግን አንድ መለስ ዜናዊ ተለጥፏል። ይህንንም ሰው “አዋቂ” ነው ብሎ ዘፍኖለታል። “አማራ በገዛ እጁ ለትግሬ ፊት ሰጥቶ” ሲል የነበር ሠለሞን ተካልኝ፤ እነሆ ዛሬ የእራሱን ዘረኝነት ትቶ መለስ ዜናዊ ጫማ ስር ወደቆ ተንከባለለ። ይህ አይነቱን አድርባይነት ምን ይሆን የወለደው ብዬ ሳስብ፤ የገንዘብና የምቾት ፍላጐት አልያም ደግሞ የድንቁርና ሕመም ነው ብዬ አልፌዋለሁ።

 

ሠለሞን ተካልኝ ከአቶ መለስ ይህን ጥቅም አግኝቷል ብዬ ባላምንም፤ ምን አልባት ሽርፍራፊ ሣንቲሞች ተወርውረውለት ይሆናል። እንደዚህ አይነቱ ግለሰብ ግን እንኳን ከኢትዮጵያ ውጭ ነዋሪ ሆነ እንጅ፤ በሀገሩ ቢቀመጥ ኖሮ የስንቱን ደፋር ሕይወት እየገደለና እያስገደለ ይቀጭ እንደነበር ሳስበው ይዘገንነኛል። ሠለሞን ተካልኝን በፀባይ ያወቁ ሰዎች እንደሚሉትም ነውርን የማያውቅ አሳደጊ የበደለው፣ ራሱን ከምንም የበለጠ አጥብቆ የሚወድ፣ ዛሬ ያለውን ነገ የሚሽር፣ በገንዘብ ወዳድነቱ ሚስቱን እንኳን ለመሸጥ የማይመለስ፤ በስተመጨረሻም ደግሞ በፈሪነቱ ጥላውን እንኳን የማያምን ጰርጳራ እንደሆነ ሲናገሩ ተደምጠዋል። አልፎ አልፎም የአዕምሮ መቃወስ የደረሰበት ሰው ስለሆነ ሊታዘንለት የሚገባ ግለሰብ ነው ሲሉም የሰማናቸው የሙያ ጓደኞቹ አሉ። ውሽ በሉት ሰዎች ብለውንም ነበር።

 

ለነገሩ በዓለም ላይ ሠለሞን ተካልኝ ያዜመለትንና ያሞገሰውን ያህል የተሞገሰ እየሱስ ብቻ ነው። በዘመነ መንግሥቱ ታላቁ መሪያችን ተብሎ መፈክር ቢወርድለትም አንድ ግለሰብ አቀንቃኝ ለብቻው ተነስቶ ቆራጡ መሪያችን ብሎ ዜማ አልተቀኘለትም። አባባ ጃንሆይ ግርማዊ ታላቁ መሪያችን ታሪካዊ ተብሎ ሲዘመርም እንደ ህዝብ አስዘመሩን እንጅ አንድ አቀንቃኝ ለብቻው አንድ ነጠላ አላሳተመላቸውም፣ … ወዘተ ስለሆነም ሠለሞን ተካልኝ አንዱና ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ደንቆሯችን ያደርገዋል።

 

የወያኔ የባህል ቡድን እንኳን ወያኔና ወያኔያዊነትን አሞግሰው ከበሮ ደለቁ እንጂ፤ ለመለስ ዜናዊ ለብቻው ነጠላ ዜማ አላወጡለትም። ቢሆንም አልፎ አልፎ ይህ ከልክ ያለፈ አድርባይነት እንደግለስብ የሚጫንባቸው ሕመምተኛ ሰዎች እንዳሉ አሌ አልልም። ነገር ግን ይህ አይነት ሎሌነት አጠንክሮ የሚታየው እንደውሻ አይነት አውሬዎች ላይ ነው። ውሻ ለጌታው የሚያሳየውን አይነት ፀባይ ከሠለሞን ተመለከትን። ውሻኛ ብንችል ኑሮ ውሾች ለጌቶቻቸው ይዘፍናሉ አይዘፍኑም ብለን ማወቅ በቻልን ነበር። ሠለሞን ግን ሰው ነገር ሆነና (ከሰው ከተቆጠረ ማለቴ ነው) በሰው ልሳን ስላንጐራጐረ ወድቆ የተንከባለለበትን የአድርባይነት መጠን አዳመጥነው።

 

የአድርባይነት መጠኑና ጥልቀቱ የተለያየ ቢሆንም እራስን የሚያሸጥ አድርባይነት የዘቀጠውና አስጠያፊው አይነት አድርባይነት ነው። ሰው እንደ ውሻ አድር ብሎ አድርባይ ሲሆን ምርጫ አጥቶ ነው ሊባል ይችላል። በሠላም የሚኖርበትና ሠርቶ የሚታደርበት ሀገር ተቀምጦ ጭራ መቁላት ምን የሚሉት አይነት አድርባይነት እንደሆነ ለራሱ ለሠለሞን አዕምሮ መልስ ትቸለታለሁ።

 

በስተመጨረሻ አቶ መለስ ከእግር እስከራሳቸው በብዙ ንፁሐን ደም የተነከሩ ነፍስ ሆነው ሳለ፤ ሠለሞን ተካልኝ ባልገደለበት (አስገድሎ እንደሆን ባላውቅም) የዚህ ደም ተለቅላቂ፣ ተጨምላቂና ውዳቂ መሆን በመወሰኑ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን ከልብ እንዳሳዘነ ሊያውቀው ይገባል። ደም ከንቱ ሆኖ አይቀርምና ከዕለታት አንድ ቀን ሀገሪቱ እንደሀገር ጥያቄ እንደምትጠይቅው ላስታውሰው እወዳለሁ።


ግርማዊ ተፈሪ

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!