ደራሲና ጋዜጠኛ ማሞ ውድነህ Author & journalist Mamo Wudnehቴዎድሮስ አበበ

ቋንቋን ያከብራሉ። ቃላትን ይንከባከባሉ። ለሥነ ጽሑፋዊ ውበት ይጠነቀቃሉ። የአጻጻፍ ስሌታቸው ያስደስታል። ስለሆነም የእውነተኛ ታሪክም ሆነ የልብወለድ መጻሕፍቶቻቸው የአንባቢን ሙሉ ትኩረት ይስባሉ። ከሌላ ቋንቋ የተረጎሟቸውንም ሥራዎቻቸውን በጥንቃቄ መርጠውና በውብ አማርኛ አሳምረው የማቅረብ ስጦታቸውን ደጋግመው አስመስክረውባቸዋል።

 

በአጭር አገላለጽ ሰውዬው የጽሑፍን ክቡርነት ጠንቅቀው ያወቁና ለሙሉ የኃላፊነት ስሜት ጋር ግዴታቸውን የተወጡ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ጸሐፊ ነበሩ። ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ያከበሩ የብዕር ሰው ... ”የኛ ሰው”።

 

ወቅቱን በትክክል ባላስታውሰውም የአምስተኛ ወይም የስድስተኛ ክፍል ተማሪ ከነበርኩባቸው ጊዜያት ጀምሮ ነበር የደራሲ ማሞ ውድነህን ሥራዎች ማንበብና ማድነቅ የጀመርኩት። በጊዜው ርዝመት የተነሣ በትክክል ትዝ ባይለኝም ደራሲው ለሕትመት ያበቋቸውን አብዝኛዎቹን መጻሕፍት አንብቤአለሁ። ያን ጊዜ ለደራሲው የነበረኝ አድናቆትም አሁንም አብሮኝ አለ። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!