ጭንቀት ጭንቀት

ገ/ኢ. ጐርፉ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

እንዲህ ተዋርጄ በሰው ፊት አፍሬ

ተስፋ መቁረጥ ቆሞ ያንኳኳል ከበሬ

ወዴት ነው እምገባው ከንግዴህስ ወድያ

ይቅር ሁሉ ይብቃኝ፣ ኧረድያ! ኧረድያ!

 

ሰፊው ዓለም ሳለ የተንጣለለው

ልቤ ተጨነቀ መሬት ጠበበው

ወይእኔ ዘንድሮ የገባሁት ዕዳ

ማምለጫውም ጠፋኝ መሹለኪያ ቀዳዳ

 

ልቤ እንዳረረ፣ ነድዶ እንደበገነ

ጉዴም ሰው ሳያውቀው እንደተከደነ

ሌላ ተጨማሪ ሳይመጣብኝ ጣጣ

ከመከራው ዓለም በየት በኩል ልውጣ?


ገ/ኢ. ጐርፉ mailto:This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ