የት ይሆን ቀብሬ?

ቅዱስ ያሬድ ከኖርዌይ

እኔም እንደሰው

እንደው የሞትኩ ቀን

አይቀር መቀበሬ

እኔን ያሳሰበኝ ያስጨነቀኝ ቢኖር

ስልጣኔን ሳልጠግበው ከህመሜ ብኖር

ከሞት ይሻለኛል ከስቃዬ ብኖር

 

 

በህይወት እያለው በሰው ተጠልቼ

በሞት ከተለየው መቃብር አጥቼ

ምኑን አተረፍኩት በህይወት ቆይቼ

በህይወት እስካሉ የትም ይኖሩታል

አስክሬንም ቢሆን በክብር ያኖሩታል

እንደ ዕምነት ስርዐቱ ሁሉን ይሸኙታል

 

በህይወት እያለው ሁሉን አይቻለው

ወዳጅ ባይኖረኝም ጠላቴን አውቃለው

ሁሉንም ሳስበው ሞቴን እፈራለው

እናም እንደጀግና ከውጭ እሞታለው

መቅደላ አድዋ ለኔም ቦታ የለው

መቀበሪያ ቦታም ቤልጄም አገኛለው

አገሬ እንደው ብሞት ...

ሙስሊም ክርስትያኑም ለኔም ቦታ የለው


ቅዱስ ያሬድ ከኖርዌይ

 

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!