ክንፈሚካኤል ገረሱ
አንተ ብቻ ግዙፍ ታላቅ ከእንስሳት፣
ፈርጠም ያለ ጡንቻ ደልዳላ ሰውነት።
አጋዘን ኒያላው አይገባም ከቁጥር፣
አንበሳ ቀጭኔው አያክልህም ነብር።


የሚጋራህ የለም ታላቅነትህን፣
የፍጡራን ቁንጮ የበላይነትህን።
መኖር ጥሩ ነበር እንደተከበሩ፣
አቆልቁሎ እያዩ ዘወትር እንደኮሩ።
ግን አይቀርምና ሲያጋድል መረታት፣
ምን ይበጅህ ይሆን የተበለጥክ ዕለት።
"አለሁኝ!" ያለ እንደው ያ ዓሣነባሪ፣
የአጥቢዎች ንጉሥ ከውቅያኖስ ነዋሪ።


ክንፈሚካኤል ገረሱ

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!