ትኩሳት

Down, Down ወያኔ
ሕልሜን አየሁ በእውኔ
ድል ሲቀዳጅ ወገኔ

የአቦይ ስብሀት መንጋ
መስሎት አልጋ ባልጋ
መጣ ማልዶ ሲነጋ
ጦር ሰብቆ ሊወጋ

ምን ጦር ቢደረደር
በሰማይ ሆነ በምድር
"በቃኝ!" ብሏል ሀገር
"ታጥቆ" ዱላና ጠጠር
ለመድፍ፣ ለታንክ ሳይበገር
ራሱን ሰውቶ በክብር
ሰማዕት ሊሆን ለሰላምና ፍቅር

ማተቡን ቋጥሮ በክር
ሶላቱን ሰግዶ በፈጅር
እጅ ለእጅ ተያይዞ እንደአጥር
መውጪያ ሊያሳጣው ይሄን ቅጥር

ህዝብ ሰማ የክተት ጥሪ
ሳይበተን ወረቀት በበራሪ

ፈረሱ እንደጠፋ ጋሪ
አይመራም በሸውራራ "መሪ"
አንገሽግሾታል የምትግተው ቅራሪ

መስለህ አልሞት ባይ ተጋዳይ
ምን ብትቧጥጥ ሰማይ
ብርሃን የለ ሚታይ
ጠልቃብሃለች ፀሐይ

ተስፋ ቁረጥ ልቀቅ
ተነስቷልና ከሊቅ እስከ ደቂቅ

ነፍስህም ትረፍ እዘንላት
በዘረኝነት ለገደልካት።


ትኩሳት (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!