ክንፈሚካኤል ገረሱ

ጊዜን እያሰሉ በሰዓት መጥኖ፣
በጥበብ በምጥቀት ዓላማን ከውኖ።
ትላንትናን ሳይሆን ዛሬን እየኖሩ፣
የሕይወትን ቅኔ እየመሰጠሩ።
እንደ ጧፍ ተቃጥሎ እንደ ሰምም ፈሶ፣
ለተተኪው ትውልድ አሻራን አውርሶ።
ይህ ነው መኖር ማለት መመላለስ በዓለም፣
እንደ ሻማ ቀልጦ የአዳም ዘርን መጥቀም።

ከዚህ በተረፈ፤

መውለድ መዋለዱ መሰል መተካቱ፣
ማደግ መመንደጉ በአካል መጎልበቱ።
መኖር ከተባለ መደርጀት መለምለም፣
ለዚህ ለዚህማ ዱባም አይቦዝንም።

ክንፈሚካኤል ገረሱ
ኅዳር 18 ቀን 2009 ዓ.ም.

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!