ክንፈሚካኤል ገረሱ

ዓይንና አፍንጫዬ ተጋጭተው አንድ ቀን፣

ሲንቅ ሲያንኳስሰው አንዱ ሌላኛውን።

ነገሩ ቢደንቀው ጆሮ አሽሟጠጣቸው፣

ጥርስ ሳቀባቸው ምላስ ታዘባቸው።

እናም! እናማ!

የአንድ አካል ቅንጣቶች አጋር መሆናቸው አቻ መሆናቸው፣

እንደተሳሰረ መስተጋብራቸው ተስፋ ሕልውናቸው፣

ምናል ቢታያቸው ምናል ቢገባቸው ቢገለጽላቸው።

ክንፈሚካኤል ገረሱ
ኅዳር 25/2009 ዓ.ም.

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!