ክንፈሚካኤል ገረሱ

ከወዳጅ ቢጣሉ ፈጥነው ይታረቋል፣
ጎረቤት ቢከፋ ሰፈር ይለቀቃል።
ደዌ ቢያጠቃዎት ይሽራል በሐኪም፣
ፈተና ቢበዛ ያልፋል እንደምንም።
ውድቀት ቢያጥለቀልቅ ይሳካል በሂደት፣
አመል ቢነሳዎት ይቃናል በትግስት።

ፍቅረኛ ቢከዳ ይተካል በሌላ፣
ትዳር ቢያረገርግ ይቆማል በመላ።
ያዳም ዘር ቢጨክን ይኖራል ለብቻ፣
ማጣት የሙጥኝ ቢል ይተኛል ስርቻ።
የወለዱት ቢሞት ይረሳል በግዜ፣
መከራ ቢበዛ ያልፋል በትካዜ።

ግና! ግና!

ከራስ ከተጣሉ ሳይመሽ ከጨለመ፣
የገዛ አዕምሮ ሙግት ከገጠመ፣
ወዴት ይደረሳል ሕሊና ካቄመ።


ክንፈሚካኤል ገረሱ
ኅዳር 26 ቀን 2009 ዓ.ም.

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!