ክንፈሚካኤል ገረሱ

ማን እንዳንቺ እናትዓለም፣
አልዘነጋሽ ለደቂቃ ለሴኮንድም።
ከጨቅላነት አጎልምሰሽ፣
ሲያተኩሰኝ አተኩሶሽ።

ስስቅ ስቀሽ፣ ከፍቶሽ ሳዝን፣
በቁም አልቀሽ በሰመመን።
ያሳደግሽኝ ውዷ እናቴ፣
አልረሳሽም በሕይወቴ።

እናም፤
እንዳይበርደኝ ብቸኝነት፣
በናፍቆትሽ እንዳልቃትት።
እስትንፋስሽ ከቶ አይራቀኝ፣
ሰላም ጤና ያድልልኝ።


ክንፈሚካኤል ገረሱ
ታህሳስ 19 ቀን 2009 ዓ.ም.

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!