ክንፈሚካኤል ገረሱ

ሰውነቷ የተጣጋ ትንሽ መዥገር፣

ከጡቷ ሥር ተከንችራ ከአንዲት ጊደር።

ደም ሥሮቿን ተጎዳኝታ ተቆጣጥራ፣

አንዴ ከዚህ አንዴ ከዚያ በየተራ።

መጣ ... መጣ ... መጣ፣

አብጣ ... አብጣ ... አብጣ።

በቃኝ ሳትል ይብቃኝ ሳትል ሳትላወስ፣

ዳግም ላትመጥ ዳግም ላታብጥ ላትመለስ፣

ተራገፈች ዝላ ዑደቷን ስትጨርስ።


ክንፈሚካኤል ገረሱ
ጥር 13፣ 2009 ዓ.ም.

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ