ክንፈሚካኤል ገረሱ

ከስር እሳት ከስር እቶን አንገብግቦት፣
ሳያቋርጥ እስኪበቃው ተግለብልቦ አግለብልቦት።

ተርከፍክፎ ተጭኖበት ረመጥ ፍም፣
በግለቱ በገሞራው አርገብግቦት እስኪከስም።

ይህን ሁሉ ተቋቁሞ ሳይሆን አመድ፣
ዳቦ ሆነ ቁርስ ሆነ ግሩም መዓድ።

አቤት ብርታት አቤት ብቃት አቤት ፅናት፣
በእሳት መሃል በፍም መሃል መኖር በሕይወት።


መጋቢት 30 ቀን 2009 ዓ.ም.
ክንፈሚካኤል ገረሱ

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!