እሱባለው ተሻገር

እያለህ ከሌለህ ኑሮ ምን ያደርጋል?

አዎ ኑሮ ምን ያደርጋል?

ስትደክም ኑረህ ከሰው ተራ ወጥተህ

ስትዳክር ኑረህ ራስክን አዋርደህ

የመጨረሻው ለት የዓለም ውዳቂ ኹነህ ትቀራለህ

ወይጉድ የዚህች ዓለም ጣጣ

አስር ላትሞላ ተቆናጣ

ታንገላታለች ልብ ድረስ ሰርጣ

ኧረ መች በዚህ ያበቃና የመራራው ሕይወት ቃና

ሕይወት ወጥታ ከጎዳና

ትሆናለች ባዶ ... ወና

አዳምጥ የሰው ልጅ የኔን ምክር

እንዲህ ባለም ላይ አትዳክር

እያለህ አጥተህ ከምትኖር ይሻልሃል ባትፈጠር!!!


እሱባለው ተሻገር (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!