እሸቱ ታደሰ (Eshe Man Tade)

ይሄ ሰው ጠገበ ማሰብም ተሳነው

ወንድሙን ጠቁሞ ለእስር ዳረገው

ምን ይጠቅመው ይሆን ሲሰቃይ ወንድሙ?

ደስታ በዚ አይገኝ በሚፈሰው ደሙ

ላገር እና ወገን ቅድሚያውን ለግሶ

ሕዝብን ለመታደግ ከራሱ ቀንሶ

ጊዜውን ቢሰዋ ፍትህን በመሻት

ምነዋ ወንድሜ ከፋህ እንደመርዳት

የሱ አገር ያንተ፣ ወገኑም ወገንህ

አይደለም ብለህ ነው ከጠላት ማበርህ?

ይሁን ካመንክበት እውነትን መደበቅ

የኛ ጊዜ ሲደርስ ያንተ ሲጠናቀቅ

ጨለማው ተገፎ ብርሃኑ ሲታይ

ፍርዱን ታገኛለህ ላደረስከው ስቃይ


እሸቱ ታደሰ (Eshe Man Tade)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ