AAU College of Natural Sciences

አራት ኪሎ ኮሌጅ ኦፍ ናቹራል ሳይንስ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ (የቀድሞዋ አራት ኪሎ ሳይንስ ፋኩልቲ)

ክንፈሚካኤል ገረሱ

ጥበብ ተፀንሶ የተወለደባት፣

መላ-ምት በተግባር የተፈተነባት።

የሆነች መሠረት ለኢንጅነር ዶክተሩ፣

የቴክኖሎጂ አስኳል የዕውቀት መንበሩ።

አንቺ አራት ኪሎ የሥልጣኔ አርማ፣

ጠረንሽ አወደ ዝናሽም ተሰማ።

የአብራክሽ ክፋዮች ጡትሽን የጠቡ፣

ዝናሽን አናኙት ዘልቀው ከምዕራቡ።

ብርቅዬ እንቁዎችሽ ጌታቸው አክሊሉ፣

ባካል ቢለዩሽም ደምቀው ያበራሉ፣

መሰል አክሊሉዎች ዛሬም ያፈራሉ።

ፊዚስት ጂኦሎጂስት ብሎም ስታትስቲሻን፣

ጠፈሩን መርምረው ዘልቀው ከርሰ-ምድሩን።

ቀመር መላ-ምቱን ሲያደርሱት ከውጤት፣

ማቲማቲሻኑ ሲተጋ ቀን ከሌት።

ኬሚስት ባዮሎጂስት ሲፈላሰፍ ሲጥር፣

ሁሉም ያኮሩሻል ያደርጉሻል ክቡር።


ክንፈሚካኤል ገረሱ

ኅዳር ፪ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም.

ማስታወሻ፦ ይህች ግጥም በ፲፱፺፩ (1991) ዓ.ም. የግጥሙ ጸሐፊ የመጀመሪያ ድግሪ ተመራቂ ተማሪ በነበረበት ሰዓት ለመመረቂያ መጽሔት የተፃፈች ስትሆን፤ መታሰቢያነቷም ለጥንቷ አራት ኪሎ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ፣ ለቀድሞዋ አራት ኪሎ ሳይንስ ፋኩልቲ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፤ እንዲሁም ለአሁኗ አራት ኪሎ ኮሌጅ ኦፍ ናቹራል ሳይንስ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ነው።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ