የአጫሾች ሳንባ

የአጫሾች ሳንባ ይሄን ይመስላል

ክንፈሚካኤል ገረሱ

ሆስፒታል ተኝቶ ሳንባ በሽተኛው፣

ተደብቆ ሲያጨስ ሱሱ ቢያሸንፈው

ዶክተሩ አዩና አጥብቀው ገሰፁት፣

ከቶ ዳግም ቢያጨስ እንደሌለው ሕይወት

ከዚያ!

ነገሩ አናዷቸው ደጋግመው ደጋግመው አጨሱ፣

አብጠርጥረው አዩት ከ'ግር እስከ 'ራሱ

ደነገጠ ደግሞም ገረመው፣

አልፎ አልፎ እያጨሰ ከነተበ ሳንባው፣

የ'ርሳቸው ብሶበት ሲጨስ ሲተን ታየው፣

ሳንባ በሽተኛው


ኅዳር ፱ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም.

ክንፈሚካኤል ገረሱ

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!