እሸቱ ታደሰ

በሰው ክፋት ሠርቶ ልቡን ያሳረረ

ወዳጅህ ነኝ ብሎ ሕይወቱን ያዞረ

ቃላት በማሳመር ባንደበቱ አፍዞ

ከግራና ከቀኝ

ከላይም ከታችም

ባይኑ እንዳያማትር ልቡን አደንዝዞ

እሱን ብቻ እንዲል ከሌሎች እንዲርቅ

ምክንያቶች ደርድሮ አረገው 'ንዲሳቀቅ

ማድረጉንስ ያድርግ ከክፋት ያሽሸው

ከሰው ሁሉ አግሎ ለግሉ ያድርገው

ችግሩ የሚታየው የአደጋው ጥልቀቱ

ከባድ የሚሆነው ለመጪው ሕይወቱ

በቀቢፀ ተስፋ በባዶ ቃል ሞልቶት

በድንገት ሳያስብ ከሄደ ነው ጥሎት


እሸቱ ታደሰ (Eshe Man Tade)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!