አውድማ

አውድማ

ክንፈሚካኤል ገረሱ

አተኩሮ ላያት ውስጧን አብጠርጥሮ፣

በንቁ ሕሊና በሰከነ አእምሮ።

ላስተዋላት ቀርቦ ባሕርይዋ ለገባው፣

ደስታ ሰቆቃዋን ባደብ ላሳለፈው።

ሕብሩን ለፈለገ ሳይታክት ለጣረ፣

ለማወቅ ለጓጓ ሩቅ ላማተረ።

ከአውድማው ለዋለ ወቅቶ ላበራየ፣

ምርቱን ከ'ንክርዳዱ አንፍሶ ለለየ።

መርምሮ ላገኘ ወርቁን ለተረዳ፣

የሕይወት ማጀቷ ላልሆነበት ባዳ።

መጣፈጥ መምረሯን ቀምሶ ላጣጣማት፣

ሕይወትም ቅኔ ናት ሕይወትም ምሥጢር ናት።


ክንፈሚካኤል ገረሱ

ኅዳር ፳፭ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም.

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!