ሶምራን

በመደመር ቋንቋ በፍቅር ዜማ ውሰጥ፤

ያለችውን ቅኝት አገር ሰታስነሳ መሬቱ ሲቀውጥ።

እኔ ነኝ ብቻ የሚል ከበሮ ቢመታ ነጋሪት ቢደለቅ፤

ሰሚ ጆሮ አይኖርም ቋንቋውም አይታወቅ።

ሁለት ዘር ኖሮኝ በየቱ ልከበር በየትኛው ልናቅ፤

መደመር ባይታለም መደመር ባይታወቅ

እንደምን ይቻላል ቢባል ከአካልህ መሐል አንዱ ክፍልህ ይጣል አንዱ ክፍልህ ይውደቅ።

ዛሬ ግልጽ ሆኖልኝ መካፈል ስም እንጂ አንዳችም ላይጠቅመኝ፤

ሲደመር ነው እንጂ ባብሮነት ሲባዛ እኩል የሚያደርገኝ።

ድንበር ለሰው ልጆች ሰዎች የሚተክሉት፤

አንድም እንዳይዋደድ አንድም ሊያመቻቹት ሊከፍሉት ሊገዙት።

ደባ ሳይቆፍረው መቀነስ ሳይበልጠው ወይ ጎራ ሳይከምረው ፤

መደመር አስፋፍቶ እኩል ከተውጣጣ አብዝቶ ቢቀንፍ መቸ ሊከፋው ሰው።

በማባዛት ቀንፎ ማካፈል ያለህን ምኑ ይከፋና፤

ባብሮነት ነጻነት አበርካች ያቅምህን ብትሆን ማንስ ይጠላና።

ሀብትና ሲሳይን፣ በረከት የምትሰጥ መሬት ከከርሷ ውስጥ፤

በፈጣሪ ፍቃድ በሰላም በፍቅር በመዋደድና ተባብረህ ስትለፋ ስትሮጥ።

የአገር ትእይንቷ የአገር መነሻ ካንድ ሰው ተነስቶ፤

ሕዝቦቿን በአንድ ዓይን በሰውነት መንፈስ ሰው መሆኑ ታይቶ።

በእኩልነት መንጽር በሰውነት ብቻ ባላማው ሳይንጓለል፤

አገር ትለማለች በእውቀቱ ሲሰለፍ ሰው በሚገባው ሲውል።

ልበል ወይ አገሬ መሥመሩን ይዘሻል መደመር መርጠሻል፤

እውነት! ተከብሮ የሰው ልጅ ኢትዮጵያዊነትን ያዘመረ እንቢልታ ዋሽንቱን ነፍተሻል።

ማባረር ማሳደድ ተብለህ የኔ አይደለህም ባይተዋር ተደርገህ ብሎም በመፈረጅ፤

መስካሪ ሰታጣ መቀነስ ፈርዶብህ ካድሬ የመረጠልህን ማንነትን፤ ዜግነትን ማወጅ።

ሃይማኖትና ዘር ዓላማና ሐሳብ ሚዛን ሳይኖራቸው፤

ብለሻል ኢትዮጵያ ሁሉም ድምር ውጤት ሰዎች ሰው ናቸው?።

የሰው ዘር ቀለሙ ሃይማኖት እውቀቱ በዜግነት ድርሻ እኩል ክታስቡ፤

መብትና ግዴታ ጥቅም ሳይበላለጥ ሕግ የበላይ ሆኖ ሳይሸራርፍ ግቡ።

ዛሬ ግልጽ ሆኖልን መከለል ክፍፍል መደንበር ላይጠቅመን፤

ብለሻል ኢትዮጵያ መደመር ብቻ ነው እኩል የሚያደርገን።

የጎበዘ እረኛ ሀብታም ሊሆን ያለው መንጋውን ያበዛል፤

ለከብቱም ለሰዉም ሽክሙን አራግፎ አብዝቶ ይደምራል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ