ምናለበት?!

(ለአምባገነኖችና ለግብረ-አበሮቻቸው)

ከጌታቸው አበራ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. )


የህዝብ ራዕይ ባታመክኑ፣

ያገር ተስፋ ባታተኑ፣

ያያችሁትን ፍጡር ሁላ - እንደ እብድ ውሻ ባትለክፉ፣

የትውልድን ውብ አበባ - በጭካኔ ባትቀጥፉ፣

ያድባር ቆሌ ባትገፉ፣ የጡር እንባ ባታተርፉ፣

ጣፋጭ ሲሳይ ማር ወለላ - በሬት መራር ባትለውሱ፣

ምናለበትኢ?! ቀኑ አክትሞ - ከመንበሩ ብትነሱ፣

 

በሥልጣን ጥም ባትሰክሩ፣

ካይጥ ጉድጓድ - የቆቅ ኑሮ ባትኖሩ፣

መውጫ መግቢያው ባይጠባችሁ - ጥላችሁን ባትፈሩ፣

እኩይ ድርጊት ተደራርቦ - ሰው ፊት መቅረብ ባታፍሩ፣

አራጅ፣ ውራጅ ... አምባገነን - የሰቆቃ የጭካኔ ...፣

የዲያቢሎስ ቁራጭ ቁንጮ - ሠይጣን፣ አውሬ፣ አረመኔ፣ ...

ተብላችሁ ተንቃችሁ - የውርደት ሥም ባትለብሱ፣

ምናለበት! ለክብራችሁ - ላገር ክብር ብትሳሱ!!

 

ልጆቻችሁ ያልታደሉት፣

ፍርሃት ታቅፈው የሚኖሩት፣

አንገት መድፋት፣ መሸማቀቅ - ሽብር፣ ሥጋት፣ ... ሳይገባቸው፣

ባደባባይ ቢራመዱ - ልበ-ሙሉ ኩሩ ሆነው ... ፣

 

ህዝበብ ሲራብ፣ ሀገር ሲወድም - ጥሪ ማሸሻ በያለበት፣

ላትበሉት ለዝንተ-ዓለም - ላትኖሩ ምዕተ-ዓመት፣

መኖር ከቶ እንዲያኮራ - በንጽኅና በነፃነት፣ 

ከማንዴላ፣ ከኦባማ፣ ... - ብትማሩ ምናለበት?!

 

የብዙኃን ምክር፣ ቁጣ፣ ... - የህዝብ ድምፅ ባትንቁ፣

ልቦናውን ቢሰጣችሁ - ከእንቅልፋችሁ ብትነቁ፣

ብልጽግና፣ ሠላም፣ ፍቅር፣ ... - ፍትህ፣ ጤና፣ ... እንዲያብቡ፣

ሰብዓዊነት እንዲሰፍኢኢ - እፎይ ብሎ ሊኖር ህዝቡ፣

እንዲከበበር ክቡር ድምፁ - ሳያሰልስ ሲወተውት፣

ሳትተብቱ ብትሰሙ - ቢያምርባችሁ ምናለበት?!

 

አልያ ግን ካልገባችሁ - የህዝብ እንባ ያገር ብሶት፣

አሁን ደርሶ ምናለበት?! - ቢጠርጋችሁ አንድ መዓት!!


 

ጌታቸው አበራ

ኅዳር 2001 ዓ.ም. (ኖቨምበር 2008)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!