የአምላክ ገጸበረከት

ታደለ ሀብቴ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. (ከፍራንክፈርት)

 

የማይነጥፍ የምዕተ ዓመት

የዝማሬ ጥበብ ሊቅ

የኢትዮው ዕጹብ ድንቅ

በትውልድ የሚወራረስ

የእንጉርጉሮ ለዛ የደስታ መንፈስ

 

የጠዋት ዜማ የአዕዋፍ

ጣዕመ ፍቅር ከአጽናፍ አጽናፍ

ኪነ ንጉሥ የመድረክ ጮራ

ሕያው ይሆናል የጥሌ ሥራ

በዜማ ጉዞ ጣራ የነካ

መልሶ የሚወርድ ልብ እያረካ

የመድረክ ውበት የዓይኑ ጉልበቱ

ያስፈነደቀን የዘፈን ስልቱ

እንደ ግዙፍ ዓለት የማይነቃነቅ

የተቃቀፈ ተራራ የማይላቀቅ

በህሊናችን የሚኖር የማይጠፋ ክትባት

የሕይወት ምንጭ ውሃ ፍሰት

ያ ርቱዕ መረዋ አንደበት

እንደጧፍ እየነደደ ሁሌ በርቶ

መንፈሣችንን መግቦ - ልባችንን በደስታ ሞልቶ

ለዛቅነው ደስታ ከጥሌ ከሱ

ምን ይሆን የኛ መልሱ

ለጣዕመ ዜማህ ልንሰግድለት

የወገንህን መከራ ደስታ ያዜምክበት

ጥልዬ ያኑርህ ጌታ በገነት

የምድር ሥራህ እንደ ማገር

ተተክሎ የሚቀር የሚዘከር

የማይናወጥ መሰረቱ

የኢትዮጵያዊ ሀብቱ

የኪነጥበብ ክብሩ የማይገሰስ ኩራቱ

ዳግም ተወልዶ ፍቅር እየዘራ

የጥሌ ሙያ የጥሌ ሥራ

የጥሌ ሥራ


 

ታደለ ሀብቴ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.  

ከፍራንክፈርት

 

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!