ኢትዮጵያ ከሰው በላይ ወዳህ

ሣሌህ ማሕሙድ ኦምራን (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. )

 

አይ! ሀገር ኢትዮጵያ

ከሰው በላይ ወዳህ

አይ! ሀገር ኢትዮጵያ

ከሰው በላይ ወዳህ

ለሚወዱህ ሥራህን ትተህ

ኢትዮጵያ ለዘላለም አቅፋህ

ማልቀሷን ማ በነገረህ

 

ኢትዮጵያ አለቀሰች

እየየ ወየው እያለች

አንጀቷን የሚያርስላት

የኪነቱ ንጉሥ የዘፈነላት

ያዘፈነላት የሸለለላት

‘ወይኔ!’ ብሎ መራቧን የነገረላት

በብዙ ምስጢር ውስጧን የገለጠላት

 

አይ! ሀገር ኢትዮጵያ

ከሰው በላይ ወዳህ

አይ! ሀገር ኢትዮጵያ

ከሰው በላይ ወዳህ

ለሚወዱህ ሥራህን ትተህ

ኢትዮጵያ ለዘላለም አቅፋህ

ማልቀሷን ማ በነገረህ

 

ፍቅር ብሎ ሳያበቃ

ወንድም ብሎ ሲያነቃ

እናት ብሎ ሲያሞግስ

ዳር ድንበር ብሎ ሲያታኩስ

ጓደኛ ብሎ ሲገልጽ

ሠላም ብሎ ሲቀልጽ

ውለታ ብሎ ሲያለቅስ

ሀገር ብሎ ሲያነግሥ

 

አይ! ሀገር ኢትዮጵያ

ከሰው በላይ ወዳህ

አይ! ሀገር ኢትዮጵያ

ከሰው በላይ ወዳህ

ለሚወዱህ ሥራህን ትተህ

ኢትዮጵያ ለዘላለም አቅፋህ

ማልቀሷን ማ በነገረህ

 

ማህደሩን ዘጋው

ደብተሩን አጠፈው

ላይጽፍበት ላያነሳው

ጭማሪ አርዕሰት ሳይሻው

 

አይ! ሀገር ኢትዮጵያ

ከሰው በላይ ወዳህ

አይ! ሀገር ኢትዮጵያ

ከሰው በላይ ወዳህ

ለሚወዱህ ሥራህን ትተህ

ኢትዮጵያ ለዘላለም አቅፋህ

ማልቀሷን ማ በነገረህ

 

ሲዋሸ አላየሁትም

ዋሸ መሰለኝ ዘንድሮ

ሳያሰማን እሮሮ

አሰማለሁ ብሎ ነግሮ

አዜማለሁ ብሎ ፎክሮ

 

አይ! ሀገር ኢትዮጵያ

ከሰው በላይ ወዳህ

አይ! ሀገር ኢትዮጵያ

ከሰው በላይ ወዳህ

ለሚወዱህ ሥራህን ትተህ

ኢትዮጵያ ለዘላለም አቅፋህ

ማልቀሷን ማ በነገረህ

 

በድብቅ ተደብቆ

ካገሩ አፈር ዘልቆ

ተማከራችሁ መሰለኝ

ከኢትዮጵያ ጋራ

በሮማን ትከሻ ተመሳጥራ

ልታስተኛህ ዘላለም

ሳታሰማ ሳታወራ

 

አይ! ሀገር ኢትዮጵያ

ከሰው በላይ ወዳህ

አይ! ሀገር ኢትዮጵያ

ከሰው በላይ ወዳህ

ለሚወዱህ ሥራህን ትተህ

ኢትዮጵያ ለዘላለም አቅፋህ

ማልቀሷን ማ በነገረህ

 

ይኸው አልጋየን ለውለታህ

ተኛበት አረፍ በል ብላህ

እኔ ብቻ ሀገርህ

ለሌላም አልሰጥህ

ጥላ ልሁንህ

ጥላሁን አልልህ

ያ የሆንከው እስኪ ይብቃህ

እኔ ነኝ የመቃብር እጮኛህ

እኔ ነኝ ሠላም መካ ያገኔህ

 

አይ! ሀገር ኢትዮጵያ

ከሰው በላይ ወዳህ

አይ! ሀገር ኢትዮጵያ

ከሰው በላይ ወዳህ

ለሚወዱህ ሥራህን ትተህ

ኢትዮጵያ ለዘላለም አቅፋህ

ማልቀሷን ማ በነገረህ


 

ሣሌህ ማሕሙድ ኦምራን (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. )

 

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!