አጭር ልቦለድ

ዓለማየሁ ታዬ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

ጎጆዪቱ በሙቀትዋ ጎረቤቶችን አቅፋለች። ማዕዘን ላይ በበሬ ቆዳ ተለጉሞ በጠፍር ግጥም ተደርጎ የታሰረ አቧራ የጠጣ አገልግል ተሰቅሏል።

 

 

በሻ አጎናፍር ፍዝዝ ብለው አገልግሉን ሲያዩ ቆዩና እይታቸውን ወደ ውጭ አሻገሩ። ንፋስ የለም፣ መብረቅ የለም፣ ... በአንድ የሙዚቃ ስሌት ዝም ብሎ ያላዝናል።

 

“እንግዲህ ድሮ የሆነ ታሪክ ነው።”

 

“እሺ!” ተባለ። ያሮጊትዋን አልጋ የከበቡት መንደርተኞች የዝናቡን ማባራት በሽማግሌው ወግ ለመጠበቅ ቆሏቸውን እየቆረጣጠሙ ተመቻቹ። አሮጊትዋም እማማ አረጋሽ ብርድ የቆፈነነውን እግራቸውን በጋቢያቸው ውስጥ አጥፈው ሞጭሟጫ አይናቸውን አጎታቸው ላይ ተከሉ።

 

“ሴትዬዋ አንድ ያልታሰበ ዕለት ቁ! ቁ! ብላ ጮኸች። ፀጉሯን እየነጨች ደረቷን እየደለቀች። ሰዉ ከየቤቱ እየበረገገ እየተመመ መጣ፤ ደረሰና

 

“ምን ሆንሽ?” ተባለች። ”ምን ተፈጠረ? ማን ተቀበረ?”

 

“’ወይኔ! ወይኔ ወርቄን! ወይኔ! ወርቄን!’ እያለች እዬዬዋን አስነካችው”

 

“ኧረ! ያዟት ፀጉሯን ነጭታ ልትጨርስ ነው!”

 

“እንዴ ምንድን ነው ጉዱ? ተደብድባ ነው ወይስ …”

 

“ያዟትና ጠይቋት እንጂ! ... ተዘረፈች ወይስ ምን ሆነች?”

 

“ምን ሆነሻሌ እቱ? ምን ነካሽ የኔ ትርንጎ!” አሏት ጉረቤትዋ እማማ ዘነቡ።

 

“ምን ያልሆንኩት አለ! ኑ ጉዴን እዩ። ወይኔ ወርቄን! ወርቄን!”

 

እያለች ወሬ አዳናቂ ነገር አዳማቂውን እየመራች ወደ ቤትዋ በር ተጠጋች። ጥርቅም ተደርጎ በተዘረጋው በሯ ጉበን ቀዳዳ አንገቷን አስግጋ ወደ ውስጥ ተመለከተችና እየጮኸችና እያለቀሰች ወዲያ ስትሸሽ … የሰዉ አይን የሸረሪት ድር የተበተበው በር ላይ እየተንቀዋለለ። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!