እናታችን አሸባሪ ናት!

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

አልክስ አብርሃም

አባቴ ስድስት ልጆቹን ሰበሰበና የመረረ ነገር ሲኖር ብቻ የሚጠቀምበትን ሰማያዊ ሽፋን ያለውን አጀንዳውን ፊቱ ዘርግቶ ስብሰባውን ከፈተ (ስለዚህ አጀንዳው ሌላ ቀን በሰፊው እና ወራለን)! ገና ከመጀመሪያው የእለቱን አጀንዳ ሲያስተዋውቅ ነበር ሁላችንም የደነገጥነው ‹‹ ወ/ሮ ማንያህልሻል ተክሌን የሚመለከት ነው ›› ሲል ግራ ተጋባን ...... የእናታችን ስም እንዲህ እንደባቡር ሃዲድ ረዝሞ ያውም በአባታችን ሙሉውን ሲጠራ ሰምተን አናውቅም! ማኑየ ....የኔገላ ....ወለላየ ነበር በደጉ ቀን ሲጠራት! ሌላው ያጨናነቀን ነገር አባባ የእናታችንን ስም እንዲህ ያራዘመ ዋናውን ጉዳይማ እስከ ነገወዲያም አይጨርሰው የሚል ስጋ ትነበር!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የደብሪቱ ወተት

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ወለላዬ

ሰፈራችንን መሀል ለመሀል ሰንጥቆ ከሚያልፈው መንገድ በስተቀኝ ሃያ አንድ መኖሪያ ቤቶች ይገኛሉ። ከነዚህ ቤቶች ነዋሪዎች ውስጥ ከአብዛኛዎቹ ጋር የስጋ ዝምድና አለን። በተለይ በአንድ ግቢ ውስጥ የምንኖረው ስምንት ቤተሰቦች ደግሞ የቅርብ - በጣም የቅርብ ዘመዳሞች ነን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፍለጋ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ተሾመ ገብረስላሴ Teshome Gebreselasseተሾመ ገብረስላሴ

በቅድሚያ ስለራሴ ልንገርህ። አለመኖርን አላውቀውም ላውቀውም አልጓጓም። በመኖር ቤተ-መቅደስ ውስጥ ነኝ። መኖርን እቀድሳለሁ። መኖርን አሞካሻለሁ። እንዳንተው ስለመኖር አዜማለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አጫጭር የሀገር ቤት ምናብ-አከል ዜናዎች

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ይነጋል በላቸው

  • ወያኔ ተለጣፊን በማፍራት የሚስተካከለው እንደሌለ አንድ ታዋቂ የፖለቲካ ተንታኝ ገለጹ

አዲሱ ሹመት የጭቡ መሆኑን ዜጎች ገለጹ

“የሰሞኑ የወያኔዎች የቁጭ በሉ ሹመት የልጅነት ጊዜ የዕቃ ዕቃ ጨዋታን ያስታውሰኛል። እልም ያለ ዐይን ያወጣ የጭቡ ሥራ ነው። ማንን ሊያታልሉ ይሆን እንዲህ እንሻቸው የሚጥሱትን የራሳቸውን ሕገ-መንግሥት ተብዬ ሳይቀር ሽረው ይህን የመሰለ ከማሳቅ ባለፈ የማንንም ቀልብ የማይስብ የአራድነት አይሉት የቂልነት ሥራ የሚሠሩት?” በማለት የገለጡት አንድ የመንደር አዛውንት፤ እንደዚህ ዓይነት ለአንዲት ድሃ ሀገር ለታይታዊው የማስመሰል ቲያትር ሲባል ብቻ ሦስት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮችን በመደርደር የብሔሮችን የሥልጣን እኩልነት ለማሳየት መሞከራቸው ሕዝቡን የመሳደብ በንቀት ልምጭም የመማታት ያህል እንደሆነ ገልጸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!