የረቡዕ ግጥም ፪ኛ ዓመት፣ ፴፩
ሚስጥር ያስተርፋል
ብልህ አያወራም - ሁሉንም ዘርግፎ
ለራሱ ያስቀራል - ሚስጥር አስተርፎ
ሰነፍ ይሄን ጊዜ - ብዙ ይሳሳታል
አልታወቀም ብሎ - ጥፋት ያካብታል
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5
ሚስጥር ያስተርፋል
ብልህ አያወራም - ሁሉንም ዘርግፎ
ለራሱ ያስቀራል - ሚስጥር አስተርፎ
ሰነፍ ይሄን ጊዜ - ብዙ ይሳሳታል
አልታወቀም ብሎ - ጥፋት ያካብታል
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5
አፈር ያቅልለት
እጅግ ረቂቅ ነው
የአበሻ ምርቃት
ከሞተ በኋላ
አፈር ያቅልለት
እኔን አትመርቁኝ
አልፈልግም ይቅር
ኑሮ ያቅልልህ
ባላችሁኝ ነበር
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5
እንዳታለቅሱብኝ
ከዚህ ዓለም ስቃይ
አረፈ እያላችሁ
ለቀብር ስትወስዱኝ
በሳጥን ከታችሁ
እንደገና እናንተው
እንዳታለቅሱብኝ
እኔ ነኝ አልቅሼ
መቀበር ያለብኝ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5
በሽበቴ ሳቀች
ከኔ ተነጥላ ርቃ እየሄደች
ሜዳ አልበቃ ብሏት እየፈነጠዘች
በተጨማደደ የፊቴ ገጽታ
ከከንፈሬ መሀል በወጣው ፈገግታ
ታምር እንዳየ ሰው እየተደነቀች
በወላቃ ጥርሴ በሽበቴ ሳቀች
እንዲህ የናቀችኝ እንዲህ የገረምኳት
ሌላ እንዳትመስላችሁ ወጣትነቴ ናት
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5
አርባ ቀን ቆጥራችሁ
አታውጡልኝ ቁርባን
እኔ ነኝ የማውቀው
የሞትኩበትን ቀን
ያሁኑ መራቅ ነው
ከጎናችሁ መጥፋት
አላያችሁኝም
በቁሜ እኔ ስሞት
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5
በሕይወት ዘመንህ
ነጻነትን ምረጥ
መብትህን አስከብር
በዳይን ተጋፈጥ
ወደድክም ጠላህም
ምድር ፈሪ አትወድም
እረፈው እንደውም
ብትሞትም አትጸድቅም
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5
በደልን አፍኖ - ዝም ብሎ መኖር
ይጠቅማል አትበለኝ - ለስምና ለክብር
ሰው ከተሰበረ - በየዕለቱ ቅስሙ
ኧረ! ምን! ሊበጀው - ምን ሊጠቅመው ስሙ?
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5
ከእብዶች መካከል ጤነኛ አንተ ብቻ
መሆኑ ያደርጋል የእብዶች መጫወቻ
ስለዚህ በቶሎ እንደነሱው እበድ
አለዛም ለመምሰል እብደት ተለማመድ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5
ልጇ ነፍሰ ገዳይ - ስለሆነ እርጉም
እሱን የወለደች - እናቱ ትረገም
ብለው ሲናገሩ
እያሉ ሲያወሩ ...
አትረገም ብዬ - ልጽፍ አሰብኩና
ትረገም ሆነብኝ - «አ»ን እረሳሁና
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5
እየተከፉ ጥርስ መግለጥ
እየጸለዩ ማላገጥ
እያነከሱ መሮጥ
እየጾሙ መጠጥ
ተፈጥሮም ይሄን ብታይ
እየዘነበ ፀሐይ
ሙሉውን አስነብበኝ ...