የረቡዕ ግጥም ፬ኛ ዓመት፣ ቁ. ፲፫
ምንድነው የሚለው?
በኑሮው በጤናው ሁሉ ተሟልቶለት
ሲጠላ ለሚኖር ማስመሰል አቅቶት
አስመሳይ የኾነ አስመሳይ ላልኾነው
ሊመክረው ቢነሳ ምንድነው የሚለው?
ሙሉውን አስነብበኝ ...በኑሮው በጤናው ሁሉ ተሟልቶለት
ሲጠላ ለሚኖር ማስመሰል አቅቶት
አስመሳይ የኾነ አስመሳይ ላልኾነው
ሊመክረው ቢነሳ ምንድነው የሚለው?
ሙሉውን አስነብበኝ ...የሀብት መለኪያው መስፈሪያው ገረመኝ
ሀብታሙን ድሀ አ'ርጎ ምስኪን ነው የሚለኝ
እሱ ድሀ አይደለም፤ ደሀ ኾኖ አልኖረም አውቃለሁኝ እኔ
በጁ ባይዝ እንኳን፣ ዘርፎ ይሠጥ ነበር እጅግ ብዙ ቅኔ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የትኛው ነው የኛ? የቱ ነው የነሱ?
አብሮ ተቆላልፎ ተጋምዶ እርስ በእርሱ
ኧረ በሕግ አምላክ! የኛ የኛ አትበሉን
የናንተም የኛ ነው፣ የኛም የናንተ ነው፣ ባዕድ አይስማብን!
ሙሉውን አስነብበኝ ...ሕሊናውን ጋርዶ በሰው የሚነዳ
አይቀርም መክፈሉ ያልበላውን እዳ
ይልቅስ ይሻላል ራስን መዳበስ
እጅን በገዛ እጅ፤ ከንፈርን በምላስ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የሰው ልጅ ተፈጥሮ፣ ጠቅላላ ባሕርይ፣ ስለሚወራረስ፣ አንዱ ከአንዱ ጋራ
በደልን ለማጥፋት፣ ግፍን ለማስቀረት፣ አንተም በዛው መንገድ ሌላ ግፍ አትሥራ።
ሰው መኾን መርሳት ነው፣ ተፈጥሮን መዘንጋት፣ አመልን ማዳፈን
ክፋትን ተንኮልን፣ ሴራ መጎንጎን፣ አንተ እንደማታውቀው እንዴሌለህ መኾን
ሙሉውን አስነብበኝ ...