“የቴዎድሮስ ራእይ” ትያትር - በኔ እይታ

“የቴዎድሮስ ራእይ” ትያትር

ክንፉ አሰፋ

በታሪከኛዋ አምስተርዳም ከተማ በሚገኝ አንድ የሲኒማ ማዕከል ውስጥ የአበሻ ዘር ታጭቋል። ቲያትር ቤቱ ጢም ያለው ቲያትሩ ከመጀመሩ ከሰዓታት በፊት ነው። ወትሮውን በዚህ ሁኔታ ኢትዮጵያዊ በግዙፍ አዳራሽ ውስጥ ሞልቶ የሚታየው በጸሎት ቤቶች ብቻ ይመስለኛል። ምሽት ላይ የሚደረጉ የአበሻ ኮንሰርቶችም ቢሆኑ አረፋፍደው ነው የሚሟሟቁት። በዚህኛው እንግዳ ክስተት አግራሞቴን ገና ሳልጨረስ፣ ሌላ ነገር አየሁ። ትያትሩን ጨርሼ ስወጣ በሩ ላይ ሕዝብ ለሁለተኛው ዙር ተሰልፏል። … ከሰዓት እረፍት በኋላ “የቴዎድሮስ ራእይ”ን በአምስተርዳም ደገሙት!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሞት የሰጠን ደስታ (አብርሃም በየነ)

አብርሃም በየነ

የታጨደው ሳር ድርቆሽ ነው የከብቶች መኖ በመሆን

በበሬ ጫንቃ ድካም ጠግቦ አደር ያደረገን፤

የሞተው የግጦሽ ሳር ነው ጮሌ ፈረስ አሳድጎ

በጦር ሜዳ የድል ብሥራት ያቀዳጀን ጀግና ተዋጊ አድርጎ፤

የበሬውን ቆዳ ከበሮ የበሬውን አንጀት ጅማት

የፈረሱን ሞት በደል የሸንበቆውን ያካል ስብራት፤

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አርቲስት ጥላሁን ጉግሳ ምን ነካው?

Betoch part 185

ክንፉ አሰፋ

ከአጭር ግዜ እረፍት በኋላ፣ EBC ላይ ብቅ ያለው "ቤቶች" በተሰኘው ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ በክፍል185 እጅግ አስደምሞናል። ተመልካቹ ሕዝብ በማኅበራዊ ድረ-ገጾች ጥላሁን ጉግሳ ላይ እየወረደበት ያለው "አሽቃባጭ፣ የወያኔ አቃጣሪ ..." ወዘተ ውግዘቶችና ስድቦችን ባልጋራም፤ ይህ አንጋፋ አርቲስት ጥበብን የፖለቲካ መደለያ ስለማድረጉ ግን ምስክር አያሻም። በአንድ ወቅት እጅግ ተወዳጅ የነበረ ይህ ድራማ በመጠነኛ የሕወሓት ልማታዊ ቅኝት እየተቃኘ መጥቶ፤ አሁን ላይ ወገን የለየ ይመስላል። ዶፍ ሲጥል ገሚሱ ይበሰብሳል፤ ሌላው ተጠልሎ ይመለከታል፤ ጥቂቱ ደግሞ ይቀልዳል። ቀልደው ሞተዋል!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!