"ወያኔም ማታለል፣ እኛም መታለል ችሎታችን ነው!"

ወያኔ

ፊልጶስ

አሁን … አሁን ”'ከልሂቃኑ እስከ ኢ-ልሂቃኑ” ድረስ፤ ቀድም ብሎ ሙሶሎኒያዊያንና ሂትለራዊያን፤ ካለፉት ሃምሳ ዓመታት ወዲህ ደግሞ ሻዕቢያዊያንና ወያኔያዊያን፤ እንዲሁም ኦነጋዊያን ከባንዳ አያቶቻቸውና አባቶቻቸው የተቀበሉትን የፈጠራና የጥላቻ ታሪክ ስላወሩትና የሥልጣን ኮርቻውን ስለተፈናጠጡት፤ የሚናገሩትና የሚጽፉት ሁሉ እንደ እውነት ተቆጥሮ፤ “በኢትዮጵያ ሕዝብ መኻል ጥላቻና በደል አለ!” መባሉ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ይድረስ ለኦሕዴድና ብአዴን፤ ኢትዮጵያዊነቱም፣ አንድነቱም ከመፈክር እንዲያልፍ

አቶ ለማ መገርሳ

ያሬድ ኃይለማርያም

የመጠፋፋት ዜና በሰማንበት ማግስትና ዘረኝነት ነግሦ አንዱ ኢትዮጵያዊ ሌላውን በማንነቱ ብቻ ሲያገል፣ ሲገል፣ ሲያፈናቅልና ሲያዋርድ እያየን ባለንበት በዚህ ክፉ ወቅት፤ ከወደ ባህር ዳር ከተማ የተሰማው ዜና፤ ኦሕዴድና በብአዴን ያሳዩት የአንድነት ስሜትና ኢትዮጵያዊነትን የማስቀደም መንፈስ ይበል የሚያሰኝ ነው። ይሁንና እነዚህ ድርጅቶች ከዳንኪራና ከሆይ ሆታ ባለፈ አገሪቱ የተጋፈጠችውን አስፈሪና ውስብስብ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የተወሰኑ እርምጃዎችን ወደፊት መራመድ ካልቻሉ፤ የዛሬው ንግግራቸው ከባዶ ፕሮፓጋንዳነት የዘለለ ሊሆን አይችልም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ንጉሠ ነገሥት የሌላቸው የኢትዮጵያ ንገሦች

Bekele Gerba

ይገረም አለሙ

“አይተዳደርም ሁለት ኮርማ አንድ ቤት

አንዱ ተሸንፎ ካላለ አቤት አቤት” ውርሰ ቃል

በዘመነ መሳፍንትም በሉት በፊውዳሉ፣ በአጼውም ይሁን በወታደራዊው ወይንም በተጋዳላዮቹ በየትኛውም የኢትዮጵያ የመንግሥትነት ዘመን አንድም በሕገ ሥርዓቱ አለያም በጉልበቱ የነገሠ ንጉሠሠ ነገሥት ነበር። በመሆኑም በየአካባቢው ራሱን የሚያነግሠውም ሆነ በንጉሠ ነገሥቱ የሚሾመው ንጉሥ እንዳሻው አይሆንም። ሥልጣኑ ገደብ ኀላፊነቱ ልክ አለው። ጡንቻው ሕሊናውን አደንዝዞት፣ አለያም ከማን አንሼ እብሪት ተጠናውቶት ራሴ ንጉሥ ነኝ የምን ለንጉሥ ማደር ነው ብሎ ያሻውን ለመሥራት ቢሞክር፣ ትዕዛዝ አልቀበል አላከብር ማለት ቢዳዳው በንጉሠ ነገሥቱ ትዕዛዝና ውሳኔ አንድም በሕግ እንዲያም ካለ በጉልበት አቅሙን እንዲያውቅ ልኩን እንዲረዳ ይደረጋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኛ ሰው በሄግ ችሎት

Eshetu Alemu

ክንፉ አሰፋ (ዘ ሄግ)

ለ25 ዓመታት በኔዘርላንድ ውስጥ ሲኖር ሰብአዊነት ማለት ምን እንደሆነ በደንብ የተረዳ ይመስላል። ምዕራባውያን ለሰብአዊ ፍጡር የሚሰጡትን ዋጋ ሳይገነዘብ አልቀረም። አምላክ በአምሳሉ የፈጠረው የሰው ልጅ ሕይወት ቀርቶ ለእንሰሶች ሕይወት የሚሰጠውን ክብር ሌት ተቀን እያየ የአመለካከት ለውጥ አያደርግም ብሎ ለመናገር ይከብዳል። እዚህ ሰብአዊ ፍጡርን በፖለቲካ አመለካከቱ መግደል ከቶውንም አይታሰብም። መግደል አይደለም የሰው ልጅ ላይ እጁን የሚያነሳ፣ ጸያፍ ስድብ ከአንደበቱ የሚያወጣ እንኳ ባለሥልጣን ቢኖር ዋጋ ይከፍላል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአማራ ሕዝብ ሞቱ ሲዘገብ እንዴት ሆኖ ነው ወንጀል የሚሆነው? ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋውን እንደማሳያ

Muluken Tesfaw

ሸንቁጥ አየለ

ጥቅል ሃሳብ

የሞተው ወገን መከፋት ሲገባው ሞትህ በመነገሩ ለምን ትንፍሽ ትላለህ ብሎ ሰውን መውቀስ አስደማሚ ነው። ገዳይ እና አስገዳይን መውቀስ እና መገሰጽ ቢቻልም ተባብሮ ለፍርድ ማቅረብ ሲገባ ለምን የሞተው ሰው ተገደለ ብለህ ትናገራለህ ብሎ ስለፍትሕ የሚጮህን ሰው መክሰስ አስደናቂ ብቻ ሳይሆን፤ በዓለም ላይ የመጨረሻው የግፍ ግፍ ነው። አማራ ሕዝብ ላይ ከሚደረገው የግድያ ወንጀል የበለጠው ግፍ ለምን የአማራ ሕዝብ ሞት ተዘገበ ብሎ በድፍረት መናገር ነው።

ሰሞኑን ከማስተውላቸው አስገራሚ ነገሮች የአማራ ሕዝብ በየቦታው ሲታረድ ለምን ታረደ፣ ተገደለ እያላችሁ ትዘግባላችሁ የሚል ነው። በተለይም ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው ጊዜውን ሰጥቶ የአማራን ሕዝብ በየቦታው መታረድ እና መገደል እየዘገበ ሰነበተ። እናም ዘይገርም የሚባለው ነገር የሚከተለው ታዲያ ይሄኔ ነው። የአማራ ሕዝብ ሞቱ መዘገቡ ዘረኝነት ነው፣ የኢትዮጵያን አንድነት ለማናጋት ነው የሚል ትችት በብዛት ይደመጣሉ። የአንድ ሕዝብ መገደል፣ መታረድ እና መሰደድ አለመዘገቡ ለአገር አንድነት ፍቱን መድኃኒት እንዴት ሊሆን እንደሚችል ደጋግሜ ባስበውም ጠብ የሚል ምክንያት አላገኘሁም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ተደራዳሪ ወይንስ ተባባሪ

አጋዚ ጦር

ይገረም አለሙ

የተረገምንበት ጊዜና ምክንያቱ
አልታወቅ ብሎ ከጠዋት ከጥንቱ
ከትውልድ ትውልድ እየተሻገረ
ይላላል ያልነው ብሶ እየከረረ
ችግር በሽታችን ዘመን አስቆጠረ፤
ከእውነተኛው ታጋይ - የአስመሳዩ ቁጥር እጅግ ስለላቀ፣
ግድያ ፍጅቱ ከአደባባይ አልፎ እስር ቤት ዘለቀ።

2010 ከባተ ገና ሁለተኛ ወሩን ያልጨረሰ ቢሆንም፤ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ብቻ ያየን የሰማናቸው ነገሮች ፖለቲከኛ ነኝ ለለውጥ እየታገልኩ ነው የሚሉትን ቀርቶ ማናቸውንም ሰው የሆነ ፍጡር ሁሉ እንቅልፍ የማያስተኛ ነበር። በምሥራቁ የአገራችን ክፍል የተፈጸመውን ሰምተን ከንፈር መጠን አጀኢብም ብለን ሳናበቃ (የእኛ ተቃውሞም ሆነ ቁጣ ከዚህ አይዘልም) ኢሉባቡር ላይ ሌላ ፍጅት ሌላ አልቂት ተፈጸመ። ይህኛውን ገና በወጉ አዝነንበት አይደለም አውርተንበት ሳንጨርስ ከትናንት በስቲያ አምቦ ላይ ሌላ የግፍ ግድያ ተፈጸመ። በእኔ አረዳድ የአንቦው ሁለት መሰረታዊ ልዩ ገጽታዎች ተንጸባርቀውበታል። የመጀመሪያው የወያኔ ቅኝ ገዢነት የተረጋገጠበት ሁለተኛው የኦሕዴድ ሰዎች ትእግስት በሉት ሎሌነት ወደ ጫፍ እየደረሰ መሆኑ መታየቱ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አገራዊ የጸሎትና ምህላ ጥሪ

ጸሎት

ምሕረት ዘገዬ

የአገራችን ጉዳይ ከድጥ ወደ ማጥም አልፎ ልንገልጸው ቃል ያጣንለት የመቅሰፍቶች ሁሉ ትንግርታዊ ትዕይንት ሆኖኣል። አንዱ ቀን አልፎ ሌላው ሲተካ ከመሻሻል ይልቅ እየባሰበት ሄዶ ዜጎች በቋሚነት ወላፈኑ በማይበርድ ምድጃ ላይ ተጥደው እንዲቃጠሉ ተፈርዶባቸዋል። በዚህም ምክንያት የምናደርገው ጠፍቶን ብዙዎቻችን በአገራችን የወደፊት ዕጣ ፋንታ ላይ ክፉኛ ተጨንቀን ተጠበናል። የዚህች ታሪካዊ አገር መጥፋት የሚያስደስታቸው ካልሆነ በስተቀር ጤናማ ለሆነ የዓለም ዜጋ ለኛ ለኢትዮጵያውያን የተደገሰልን መከራ እጅግ ዘግናኝ ነው። በዚህን ወቅት አገር አማን ብሎ የሚተኛ፤ ከዚያም ባለፈ በእህል ውኃ ስካርና ጥጋብ ጮቤ የሚረግጥ ካለ ዓለም ብታልፍ የማያሳስበው ግዴለሽ እንጂ የሚያስብ አንጎል ባለቤት የሆነ ጤናማ ሰው አይደለም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጽንፈኛ ብሔርተኝነት መዘዝ

ኢትዮጵያዊ ብሔርተኝነት ይለምልም!

በቀለ ደገፋ (ከኦስሎ)

ከሁለት ዓመት በፊት በኢሕአዴግና በተቃዋሚ ቡድኖች መካከል ሲደረጉ የነበሩ ክርክሮች ከሞላ ጎደል በዴሞክራሲ፣ ፍትሕና ልማት ዙሪያ ያጠነጠኑ ነበሩ። አሁን አሁን ግን ፖለቲካችን መጀመሪያውም መጨረሻውም የማንነት ፖለቲካ ሆኗል። እንደዚህ ዐይነት የፖለቲካ አካሄድ ከ40 ዓመት በፊት ማርክሲዝምን እንደ ሃይማኖት በተቀበሉ ተማሪዎች የተጀመረና በገዥው ፓርቲም እንደ ብቸኛ ማደራጃና ማታገያ መንገድ የተያዘ ከመሆኑ አንጻር፤ አሁን ያለንበት ቀውስ ብዙዎችን አያስገርምም። ምናልባትም እንደ ትንቢት እያንዳንዱ ነገር ከታቀደለት ጊዜ ሁሉ ቀድሞ እየተደረገ ያለ ነው የሚመስለው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አቶ ግዛቸው ሺፈራውና ሀብታሙ አያሌው

አቶ ሀብታሙ አያሌውና ኢንጂንየር ግዛቸው ሺፈራውና (ፎቶ ቅንብር ኢዛ)

ይገረም አለሙ 

በቅድሚያ ኢንጂንየር ግዛቸው አለማለቴ፤ መጠሪያ አይደለም ከሚል እምነት የዘለለ ምክንያት እንደሌለው ይታወቅልኝ።

ለዚህ ጽሑፍ አብይ መነሻ ምክንያቱ “የሀብታሙ አያሌው ቅጥፈትና የባዶ ቅል መንኳኳት” የሚለው የአቶ ግዛቸው ጽሑፍ ነው። የሀብታሙ አያሌውን መጽሐፍ አላገኘሁትም። በአቶ ግዛቸው ጽሑፉ እንደተገለጸው የአቶ ሀብታሙ መጽሐፍ እንዲህ ከእውነት ይልቅ በስሜት ከማስረጃ ይልቅ በጥላቻ የተሞላ ከሆነ አለማግኘቴን እሰየው እላለሁ። ምክንያትም ምላሽ በመስጠት ያደክመኝ ነበርና።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሲያልቅ አያምር፤ “የሥርዓቱን አሟሟት ያሳምርልን!”

Ethiopian PM Hailemariam Desalegn

ያሬድ ኃይለማርያም (ከብራስልስ)

የዛሬ ሦስት ዓመት ታህሳስ 10 ቀን 2007 ዓ›ም “ግፍና አፈና ዐመጽን ይወልዳሉ፤ የዐመጸኛ አፍ ጥልቅ ጉድጓድ ነው (መ.ምሳሌ ም.22፣ ቁ.14)” በሚል አርዕስት ለንባብ ባበቃሁትና በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ በገመገምኩበት ጽሁፍ ይህን ከትቤ ነበር፤ “አንድ ሕዝብ በላዩ ላይ ገዢዎች እየተፈራረቁበት ረዘም ላለ ጊዜ በአገዛዝ ሥርዓት ሥር ስር ሊቆይ ይችል። ይሁንና ዕድሜ ልክ የገዛ አፋኛ ሥርዓት ግን የለም። ሥርዓቱም እንደ ድርጅት፣ ሹማምንቱም እንደ ሰው የጉብዝና ዕድሜያቸው የተወሰነ ነው። የአፈናን ስልት በመለዋወጥና ሸምቀቆውን በማጥበቅም ዕድሜን ማራዘም የሚቻል ቢመስልም በተቃራኒዉ ውድቀትንም ያፋጥናል። ግፉ እየበረታና የመብት ጥሰቱም መረን እየለቀቀ በሄደ ቁጥር የሕዝብ ትእግስት ይሟጠጣል። ሕዝብ መቆጣት ከጀመረና ቁጣውም ወደ አደባባይ አመጽ በተቀየረ ጊዜ የግፍ አገዛዝ ወደ መቃብር፣ ግፈኞቹም ወደ ዘብጥያ እንደሚወርዱ እርቀን ሳንሄድ ባለፉት አምስትና አሥርት ዓመታት ውስጥ በአለም የታዩ ሕዝባዊ ነውጦችንና ያስከተሉትን መዘዝ ማጤን በቂ ነው።” የዚህ ጽሁፍ አላማም የነበረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ደግ ቀን ይመጣል እያለ አምቆ የያዘው ብሶትና ክፌት ሊፈነዳ ጥቂት ስለቀረው ሥርዓቱ በጊዜ እራሱን ያርቅ፤ ካልሆነ ግን የማይቀረው አመጽ ይነሳል። የሥርዓቱም ፍጻሜ እንዳያምር ይሆናል። የሚል ማሳሰቢያ ጭምር ነበር። ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነገሮች እያፈጠጡ መጡ። ይህን ጽሁፍ ምሉውን ለማንበብ ከዚህ ገጽ ሥር ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ።[1]

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!