መርስኤ ኪዲን

እንዳሁኑ ሳይሆን ቀድሞ “ገብረማሪያም” ምርጥ ከሚባሉ ስሞች አንዱ ነበር። እናም አንዳንድ ዓይነደረቅ ሰዎችን ለመግለፅ በትግርኛ ”ዘይሓፍር ድሙ ገብረማሪያም ሽሙ” የሚል አባባል አለ። ትርጉሙም “የማያፍር ድመት ስሙ ገብረማሪያም ነው” ማለት ነው። ይህን አባባል ለመጠቀም ያስገደደኝ በምርጫ ተፎካካሪ ፓርቲዎች መካከል ባለፈው ሣምንት በተደረገው ክርክር መድረክን ወክለው የተገኙት ሰው አቶ ገብሩ አስራት መሆናቸውን ሳይ የተፈጠረብኝ ግርምት ነው። የክርክሩ አጀንዳ “ሰብዓዊ መብት፣ የሕግ የበላይነትና መልካም አስተዳደር” ስለነበር ነው ግራ መጋባቴ። ምክንያቱም አቶ ገብሩ የትግራይ ፕሬዝዳንት እያሉ ትግራይ ውስጥ የዩንቨርስቲ ተማሪ ስለነበርኩ፤ የእሳቸው አስተዳደር ምን ይመስል እንደነበር ጠንቅቄ ስለማውቅ ነው።

 

አቶ ገብሩ በክርክሩ የተሰጣቸውን 8 ደቂቃ በሙሉ የተጠቀሙት ኢህአዲግን በመውቀስ ነው። በርግጥ በሰብዓዊ መብት አያያዝ ጉዳይ ችግር ያለበት መንግሥት በመሆኑ ብዙም የሚያስገርም አይሆንም። እኔን ያስገረመኝ የወቃሹ ማንነት ነው። አቶ ገብሩ አስራት በሥልጣን ዘመናቸው ባገሪቱ የከፋ የሚባለውን አፋኝ አስተዳደር ያቋቋሙና (የትግራይ ክልል በሳቸው ጊዜ ከየትኛውም የኢትዮጵያ ክልል የከፋ የመብት ጥሰት የሚፈፀምበት ነበረ። ያለምንም ጥርጥር ከሳቸው በኋላ ይሻላል።) በኢህአዲግ ክፍፍልም ወቅት በዲሞክራሲያዊነት ጉዳይ ችግር የለብንም፤ ችግራችን የሉዓላዊነት ጉዳይ ብቻ ነው ብለው የተከራከሩ ናቸው። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!