ይሄይስ አዕምሮ

ይድረስ ለኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን ጣቢያ፦

በቅድሚያ እንኳን ለ”ምርጫ 2002 በሠላም አደረሳችሁ!” ብዬ እንዳልጀምር ራሴን አከላከልኩትና፤ እንግዲያውስ ” እንኳን የኢትዮጵያ ህዝብ በጉጉት ለተቀበለውና እንዳይኑ ብሌን በስስት ለሚያየው የኢሳት ወይም የእሳት ቴሌቭዥን ሥርጭት መጀመር በሠላም አደረሳችሁ!” ማለትን ወደድኩ። የሚያግባባን ይመስለኛል። በዚያውም እናንተን ጨምሮ ብዙ ሰው ከማስቀየም እድናለሁ።

 

በሙከራው ሥርጭቱ ላይ የነበሩኝን አንዳንድ ቴክኒክ ነክ ሂሶችን በኢ-ሜይል አድራሻችሁ ሰድጃለሁ። በማንኛውም ውጥን የሥራ ሂደት ላይ እንደሚያጋጥም ሁሉ፤ በኢሳትም ይታዩ የነበሩና አሁንም ቢሆን ሊኖሩ የሚችሉ ቴክኒካዊ ችግሮች የሚጠበቁ ናቸው። በነገራችን ላይ ኢሳት ከተጀመረ ወዲህ የዲሽ ዋጋ ክፉኛ ማሻቀቡን ሰምታችሁዋል? ከብር 400 በላይ ጨምሯል። አንዳንድ ያገራችን ነጋዴዎች (አንዳንድ ልበል እንጂ ባንድ ምሽት ከስንቱ ጋር ተጣልቼ እዘልቀዋለሁ) እንደኢህአዲግ በገንዘብ ፍቅር ተለክፈውብን ኅሊናቸውን ስለሳቱ የወገናቸው እንግልት ሊሰማቸው አልቻለም። ክፉ ቀን መጣብንና የሚያልፍ ጊዜ የማያልፍ ትዝብት እያተረፈብን ወገን ለወገን ተቆራርጠናል፤ ብቻ አንድዬ ይሁነን እንጂ የኛስ ኑሮ ቴዲ አፍሮ ”መላም የለው” እንዳለው ሆኖብናል። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!