የኢትዮጵያ ህዝብ፣ አገር-ወዳድና ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች እና ኢህአዴግ፤ ከዚኽ ወዴት? ክፍል አስራ አንድ

አያልሰው ደሴ (የግል አስተያየት)

ሐ) አመራር፦ ቀደም ሲል እንዳየነውና ወደፊትም እንደምንመለከተው ለማንኛውም የተናጠልም ሆነ የጋራ ትግል መሳካት ወይም ውድቀት አመራር ቁልፍ የሆነ ሚና አለው። በመሠረቱ የትግል ድርጅት አመራር ሰጭ መሆን ከፍተኛ ኃላፊነት ስለሆነ በኅሊና ተገዥነት አገልግሎት የሚሰጥበት እንጂ የግል ጥቅም የሚገኝበትም ሆነ አጉል ዝና የሚፈለግበት ሹመት ተደርጎ መታዬት አይኖርበትም።

 

የአማራጭ ኃይሎች ምክር ቤት በተመሠረተበት መንፈሥ ለተጠበቀው ውጤት እንዳይበቃ ካደረጉት ዋና ዋና ምክንያቶች ውስጥም አንዱ የአመራር ችግር መሆኑ ግልጥ ነው። ይኽ ደግሞ ሁለት ገፅታዎች አሉት። አንደኛው አለመተማመን የፈጠረው ችግር ሲሆን፤ ሁለተኛው እራሱ ኃላፊነት የተሰጠው ክፍል ድክመት ይሆናል። ሁለተኛው ክፍል በተራው የራሱ ሁለት ዘርፎች አሉት። እነሱም ራሱ ምክር ቤቱን እንዲመሩ ኃላፊነት በተጣለባቸው ወገኖች በኩል የተከሰተ የግልና የወል ኃላፊነትን መወጣት አለመቻል እና ለመጀመሪያው ድክመት አስተዋፅዖ አድራጊ ሆኖ የምናገኘው የአባል ድርጅቶች አመራር ክፍሎችን የሚመለከት ይሆናል። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!