ይነጋል በላቸው

በ”ሠላም ለሁላችሁም!” ጀመርኩ ይህችን አጭር አስተያየት። የአቶ ዘውገ ፋንታን ሐተታ (በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ስፖርት ፌደሬሽን ስለ ዳኛ ብርቱካን ሚደቅሣ የክብር እንግዳነት ምርጫ የወሰደው ፖለቲካዊ አቋም) አነበብኩ። ሀገራችን የገጠማትን ዘርፈ ብዙ ችግር እያሰላሰልኩም ብዙ ተከዝኩ። የወያኔም እጅ ምን ያህል ረዥም እንደሆነ ታሰበኝ። ለነገሩ በብሂሉ ”አለንጋ ጣት” ነበር የሚባለው፤ ግን ነገርን እንዳደረጉት ነውና ”አለንጋ እጅ” አልኩና ተነሳሁ። ዳሩ ዛሬ ዛሬ ምን ባለበት ቆሞ ያለ ነገር አለና ልጨነቅ? ሁሉም ነገር ሊያውም በአሉታዊ መልኩ እየተለወጠ አይደል ያለ?

 

የብርቱካንን ግብዣ በሚመለከት ብዙ ተብሎአል፤ ከሚገባው በላይ ጦዞአል ማለት ይቻላል። አብዛኛው ህዝብ ኢትዮጵያ እዚህ ባገር ቤት ውስጥ ይልሰውንና ይቀምሰውን አጥቶ በረሃብና በሰቆቃ እየተገረፈ ባለበት ሁኔታ ከዚህ ታላቅ ሀገራዊ መቅሰፍት አንፃር ሲመዘኑ ሚዛን በማይደፉ ጉዳዮች እንድንንጫጫ የወያኔ የዘወትር መሠሪ ሥልት መሆኑን የምናውቅ እናውቃለን። የትም የሚኖር ኢትዮጵያዊ የወያኔን ”በረከት” ማግኘት እንዳለበት የወያኔው ወያኔያዊው ክታበ ዲያቢሎስ የደነገገው ደንብ መሆኑንም ብዙዎቻችን እንረዳለን። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!