እስክንድር ነጋ (አዲስ አበባ)

መግቢያ ”ሻይ፤ በሎሚ፣ ያለስኳር” አልዃት፤ ትዕዛዝ ልትቀበለኝ ፊት ለፊቴ የቆመችውን ወጣት። ትላንት፤ ሰኞ፣ የካቲት 28 ቀን 2003 ዓ.ም፤ ከጠዋቱ 2 ሰዓት። ኢንተርኔት ካፌ እስከሚከፈት ሚጢጢ ሻይ ቤት ውስጥ ቁጭ ብያለኹ። በእጄ "OBAMAS" የሚባለውን ቢጫ እስክሪቢቶ ይዣለኹ። ጠረጴዛ ላይ ወረቀት አስፍሬያለኹ። የጀኔራል ፃድቃንን ክፍል ሁለት መጣጥፍ ለመጀመር እያቅማማኹ ነው። ቴሌቪዥኑ ትኩረቴን እየተሻማው ነው። የኒክ ኒልቴ የድሮ ፊልም በዐረብ ሳት እየተላለፈ ነው። ፊት ለፊቴ ሶስት ሰዎች ሞቅ ያለ ጨዋታ ይዘዋል። አንዱ ሽበት ጣል ጣል አድርጎባቸዋል። ሁለቱ ወጣቶች ናቸው።

 

”ዜና ላይ አድርጊው ...” አለ ወጣቱ ወደ ባሬስታዋ ዞር ብሎ። ባሬስታ ሆና የምትሰራው የሻይ ቤቷ ባለቤት ናት። ከደንበኞቿ ጋር ትግባባለች። ”ለምን? ...”። ”ስለማንቼ ጨዋታ ይኖራል ...” አላመነታችም። ሪሞቱን ብድግ አድርጋ ኢቲቪ ላይ አደረገችው። ”ዜና” የሚለው ምስል ብልጭ አለ። ዓይኔን ቶሎ ከቴሌቭዥኑ ላይ ነቀልኹ። አሁን ትኩረቴ ሳይሰረቅ መፃፍ ልጀምር ነው። እስከ ግማሽ ቀን ሁሉን ነገር መጨረስ አለብኝ። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!