ይሄይስ አእምሮ

ኢትዮጵያ ውስጥ በሠላም መኖር ከፈለግህ ማሟላት የሚጠበቅብህ ብዙ ነገሮች መኖራቸውን አትርሳ። በዋናነት ግን ገበያ አትውጣ። የምትገዛው ነገር አይኑርህ - እንዲኖርህም በፍፁም አትመኝ። የማንኛውንም ዓይነት አላቂም ሆነ ቋሚ ዕቃ ዋጋ አትጠይቅ።

አትብላ፣ አትጠጣ፣ አትልበስ፣ ቤትም እንዲኖርህ አትመኝ፤ ቀድሞውን ቤት ካለህም ሲያሻው በላይህ ላይ ይናድብህ እንጂ ለማደስ አታስብ። አምልኮት ቦታዎች አትሂድ - ግፋ ቢል የሚቀርብህ ’ለትራንስፎርሜሽኑ ዕቅድ ተግባራዊነት ምዕመናን ከኢህአዴግ ጎን ተሰልፈው አቅማቸው በፈቀደ እንደሚረባረቡ ብፁዕ አባታችን ያደረባቸውን ፅኑ ሕመም (ይቅርታ - ያደረባቸውን እምነት ለማለት ነው) ለፋና ሬዲዮ ገለጹ’ የሚለው የአባ ጳውሎስ ኃይማኖታዊ ካድሬ ስብከት ነው። የመንግሥትን የሐሰትና የበሬ ወለደ ቱሪናፋ የሚያራግቡ የኤፍ.ኤምም ሆኑ መደበኛ የሬዲዮና የቲቪ ፕሮግራሞችን በምንም መንገድ አትከታተል። ባጭሩ የአዕምሮ ጤንነትህን ከፈለግህ ያገኘኸውን እየቀመስክ ዝም ብለህ እንደከብት ኑር። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!