ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ)

በ2008 ምርጫ ወቅት ዕጩውን ፕሬዜዳንት ኦባማን በደስታ ነበር የደገፍኳቸው? በእርግጠኝነት! ባለፉት አራት ዓመታት ጊዜ ያከናወኑት ሁሉም  ተግባራቸውንስ የምስማማበት ነው? ፈጽሞ! በ2008 የገቡትን ቃላቸውንስ በሙሉ አክብረዋል? እንዲያዉም! በ2012 በፕሬዜዳንት ኦባማ ቅር ተሰኝቻለሁ? በሚገባ! ግን: እኮ አኔ ብቻ ሳይሆን  በ2008 የደገፏቸው በሚሊዮን የሚቆጠሩ አሜሪካኖችም ቅሬታ አላቸው፡፡

 

በምርጫቸው ወቅት ታሪክ እንደተሰራ ያመኑና መልካሙን ሁሉ የተመኙላቸውም በአሰርት ሚሊዮን የሚቆጠሩም የዓለም ሰዎችም ባለቅሬታዎች ናቸው፡፡

 

ከሞላ ጎደል የሆነ ቅሬታ ቢኖረኝም ፕሬዜዳንት ኦባማ በድጋሚ እንዲመረጡ እደግፋለሁ:: ምክንያቴም የኣላማዬና የእምነቴ አራማጅ በመሆናቸው ነው:: ፕሬዜዳንት ቢል ክሊነተን ባለፈው ሳምንት በ2012ቱ የዴሞክራቲክ ኮንቬንሽን (ስብሰባ)ንግግራቸው እንዳስቀመጡት፤ በዚህ የ2012 ምርጫ ሁለት ምርጫዎች አሉን፤

 

“በራስህ ቧጠህ ተወጣውን ከፈለጋችሁ ሪፓብሊካንን ምረጡ፡፡በእኩልነት ሃላፊነትን የምንወጣበትና፤በሚገኘውም ውጤት እኩል የመገልገል እድል ካላችሁና ሁላችንም በአንድነት ያገባናል የምትሉ ከሆነ ድምጻችሁን ለባራክ ኦባማና ለጆ ቢደን ስጡ፡፡ሁሉም የአሜሪካን ዜጋ በምርጫ እንዲሳተፍ፤ የምርጫ ሕግንም አካሄድ መቀየር  አግባብ አይደለም ብላችሁ የምታምኑ ከሆነና የወጣቱን፤ የምስኪኑን ዜጋ፤የአናሳውን ዜጋ ክፍል፤የአካል ጉዳተኞችን መራጮች ቁጥር መቀነስ አገባብ አይደለም የምትሉ ከሆነ ባራክ ኦባማን ደግፉ፡፡ ፕሬዜዳንቱ የአሜሪካንን የሁለንተና ዕድል በጨቅላ እድሜያቸው ወደዚህ የመጡትን ወጣት ስደተኞች ኮሌጅ የመግባት እድል፤ በውትድርናው ተካፋይ መሆንን፤ድምጻችሁን ለባራክ ኦባማ ስጡ፡፡ የአሜሪካ ሕልምና ፍላጎት ጠንክሮ የሚጓዝበትንና በዚህ ውድድር በበዛበት ዓለም፤የአሜሪካ ለሰላም የቆመና የብልጽግና ተቀዳሚ መንግስት እንዲሆንና እንዲቀጥል ካለማችሁ ያንን ተግባራዊ ለማድረግ ለኦባማ ነው ድምጻችሁን መስጠት ያለባችሁ፡፡

 

እኔ እድልን በጋራ ሃላፊነትንም በጋራ የሆነ ሀገርን ነው የምመርጠው፡፡ ሁላችንም በአንድ ላይ የሆነ ሕብረተሰብን ነው የምደግፈው፡፡

 

ወከባው ሪፓብሊካኖች ከዘመናት ውድቀት ትንሳኤ እያደረጉ ነው በማለት ይጮሃል፡፡በ2008 ከነበራችሁበት ሁኔታ አሁን የተሸለ ሁኔታ  ላይ ናችሁ በማለት ይሳለቃሉ::  ሃቁ እራሱ እንዲናገር እንፍቀድለት፡፡

 

ፕሬዜዳንት ኦባማ በ2008 ሥልጣን ሲረከቡ አሜሪካ በወር 750,000 ሥራ አጦች ይፈጠሩባት ነበር፡፡ በፕሬዜዳንት ኦባማ አስተዳደር ግን ከግሉ ክፍለ ኤኮኖሚ 4.5 ሚሊዮን ተፈጥረው ሳለ ከ2011 ጋር ሲመዛዘን ከ2008 ወቅት አንሻልም? በሚገባ እንጂ!

 

በ2008 የአሜሪካን ኤኮኖሚ በዎል ስትሪት በትሪለዮን ውስጥ አዘቅዝቆ ነበር፡፡ የመኪናው ኢንዱስትሪም እርሙን ሊያወጣ ቀናት ነበር የቀሩት፡፡በ2012 የስቶክ ማርኬት (አክሲዮን) ዋጋው በእጥፉ ጨምሯል፡፡ ሚት ሮምኒ እንዳለውም የመኪናው ኢንደስትሪ አልሞተም ይልቅስ ተፍፉወመ እንጂ፡፡ በ2012 የጄኔራል ሞተርስ ገበያ በ15.5 ከመቶ ከ2011 በተሸለ አሻቀበ፡፡ ጂ ኤምም በ2008 ከነበረበት አዘቅት ወጥቶ 248,750 መኪናዎች ለመሸጥ በቃ፡፡ ይህም ከ2008 ዓም የተሸለና ተስፋ የሚሰጥ መሻሻል ነው፡፡ታዲያ የአሜሪካን የአውቶ ፋበሪካ እንደገና ወደ አንበሳነቱ ተመልሶ ማግሳት አልቻለምን?

 

ፕሬዜዳንት ኦባማ ሁሉም የሚችለውን ለሁሉም ጠቃሚነት ያለውን የጤና ኢንሹራንስ ዘዴ በፕሬዜዳንታዊ ዘመናቸው ይፋ ከማድረጋቸው ቀደም ብሎ 40 ሚሊዮን አሜሪካውያን የጤና ዋስትና የላቸውም ነበር፡፡ በ2014 አብዛኛው የአሜሪካ ዜጋ አቅማቸውን ያመጣጠነ የጤና ዋስትና ይኖራቸዋል፡፡ የጤና ዋስትና ድርጅቶችም በጤናማውና በበሽተኛው ባለውና በሌለው፤ በሚል ልዩነት ማድረጋቸው ያከተመ ይሆናል፡፡ ወላጆችም ልጆቻቸው 26 እስኪሆናቸው ድረስ በቤተሰባቸው የጤና ዋስትና ውስጥ አካተው ያቆዩዋቸዋል፡፡ የዕድሜ ባለጸጋ የሆኑና የሜዲኬር ተጠቃሚዎችም በመድሃኒቶቻቸው ላይ ቅናሻቸውን ያጣጥማሉ፡፡ እነዚህ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አሜሪካውያን ታዲያ በ2008 ከነበሩበት ሁኔታ የተሸለ ደረጃ ላይ አይደሉም? ያለጥርጥር እንጂ!

 

ከፕሬዜዳንት ኦባማ ሥልጣን መያዝ ቀደም ብሎ ሁሉም በየፈርጁ ተጠቃሚውን፤ከክሬዲት ካርድ እስከ የተማሪዎች መማርያ ብድር ከዚያም አልፎ ተጠቃሚውን ሁሉ ግራ ሲያጋቡትና በጥቃቅን ፅሁፎች በማደናበር፤ሕጋዊ በሚመስሉ አሳሳች መጠቀሚያዎች ሕብረተሰቡን አጃጅለውት ቆይተዋል፡፡ አሁንስ የአሜሪካን ተጠቃሚ ሕብረተሰብ በ2012 ያለው ሁኔታ በ2008 ከነበረው አይሻልም? አያጠያይቅም?

 

ሴቶች በስራው ዘርፍ 47 በመቶውን (66 ሚሊዮን ሴቶች በስራ ላይ) ይይዛሉ፡፡በብዙ ኢንዱስትሪዎች ሴቶች ከወንዶች ያነሰ ክፍያ ነው የሚደረግላቸው፡፡ ከ2008 በፊት ሴቶች ከወንዶች ባላነሰ መልኩ እንዲከፈላቸው ድምጻቸውን ማሰማት አይችሉም ነበር፡፡ፕሬዜዳንት ኦባማ ሊሊ ሌድቤተር እኩል ክፍያ ህግ ፤ ማንንም የማያገለውን ሴቶችን፤በጾታ ሰበብ እኩል ክፍያን የሚታገድባቸውን፤በቀለም፤ በዘር፤ በሃይማኖት፤በዕድሜ፤ በአከለ ጉዳተኛነት፤የተጎዱትን ሁሉ ያቀፈውን ህግ ፈርመው አጸደቁ፡፡ታዲያ እነዚህ አሜሪካኖች በ2012 ዓ.ም ከ2008 ዓ፤ም ሁኔታቸው አለተሻሻለም? ምንም አያጠራጥርም!

 

ከጁን 2008 በኋላ አሜሪካ 182,060 ሠራዊት ወደ ኢራቅ ልካለች፡፡ በ2012 ሁሉም የአሜሪካ ተዋጊ ሃይሎች ከኢራቅ ነቅለው ወጥተዋል፡፡በ2014 ደግሞ ሁሉም ተዋጊ ሃይሎች ከአፍጋኒስታን ለቀው ይወጣሉ፡፡ ሬዜዳንት ኦባማም እነዚህ የጦር አባላት ለሚቀጥሩ ድርጅቶች፤ትምህርታቸውን ለመቀጠል ለሚመርጡትም የትምህርት ዕድሉ እንዲሰጣቸውና የመልሶ በነበሩበት ቅድመ ዘመቻ የመቀጠር እድል እንዲያገኙ ይህንንም  ለሚያደርጉት ድርጅቶችና መሰል ተቋማት የታክስ ተጠቃሚነት (ታክስ ክሬዲትስ)፤ እንዲሰጣቸው በፊርማቸው አጽድቀዋል፡፡በፕሬዜዳንት ኦባማ አስተዳደር ውቅት ዓለም ስለአሜሪካ ያለው አስተያየት ‹‹በመጠኑ መሻሻልን›› አሳይቷል፡፡እነዚህ የጦር አባላትስ በ2008 ከነበሩበት ሁኔታ አሁን በ2012 የተሻሻለ ሁኔታ አይደሉምን? አሜሪካስ እንደሃገር ቀደም ሲል ከነበረችበት ሁኔታ አሁን ከበሬታን አላገኘችምን? በ2008  ከነበረን ጠቅላይ የጦር አዘዥ (ኮማንደር ኢን ቺፍ) አሁን ያለን አይሻልም? እንዴታ!

 

እርግጥ ሁሉም ነገር በ2008 ከነበረበት ሁኔታ ተሻ ሽሏል ማለት አይደለም፡፡ ኦሳማ ቢን ላደን ከአሁን ይልቅ በ2008 ዓም እርግጥ በተሸለ ሁኔታና ፓኪስታን ከነበረበት ቪላ የሽብር ተግባሩን ተንደላቆ ያ ቀነባብር ነበር፡፡ ከሱም ጋር የሽብር አጋሮቹ ሁሉ በምቾት  ሽብርተኛ ተግባራቸውን ያከናውኑ ነበር፡፡ ሼክ ሳዒድ አል ማስሪ፤(የአልቃዳው 3ተኛ ደረጃ ሃላፊ): አንዋር አል-አውላኪ (የአረቢያን ፔንሰዊላ አልቃይዳ): አቡ ሃፍሲ አልሻሃሪ (በፓኪስታን ኦፐሬሽን የአልቃይዳ ሃላፊ): ከፍተኛ የአልቃይዳ ባለስልጣኖች፤ አብድ አል-ራህማን፤ ኢሊያስ ካሲማሪ፤አማር አልዋ ኢሊ፤ አቡ አል አልሃሪቲ፤ አቡ አዩብ አል መስሪ፤ ሃምዛ አል ጃዊፊ፤ አቡ ኦማር አል ባጋዳዲ፤ አሊ ሳላህ ፋራሃን፤ ሃሩን ፋዙል እና ሳለህ አሊ ሳለህ ብሃን (የምስራቅ አፍሪካ አል ቃይዳ) በተሸለ ሁኔታና ነበሩ፡፡ ሌሎችም በባሊ የማታ ክበብ ለተፈጸመው የቦምን ጥቃትና ሕይወታቸው ላለፈው 180 ሰዎች ተጠያቂ የሆኑት የአልቃይዳ አባላት እና ብዙዎቹ አባላትስ አሁን በ2012 ካሉበት በተሸለ ሁኔታና ነበሩ፡፡

 

ፕሬዜዳንት ኦባማ ተግባራቸውን እንዳልፈጸሙ በመረዳት፤ እና ኤኮኖሚውን በማሻሻል ጥረቱ ገና የሚቀራቸው እንዳለ ይገነዘባሉ፡፡ ባለፉት 4 ዓመታት የተጓዙበትም መንገድ ቀላል እንዳልነበረ የምናውቀው ነው፡፡ በሚቀይሱት መንገድ ላይ ሁሉ ተቃውሞ ነበረባቸው፡፡ ከዓላማቸው ሊያናጥቧቸው ተሞክሯል፤መንገዱን ለመዝጋት ተጥሯል፤ከዚያም አልፎ የሪፓብሊካኑ ቁንጮ ሹም ‹‹አንድና ብቸኛው ታላቁ የፖለቲካ ግባችን፤ ፕሬዜዳንት ኦባማ የአንድ ተርም ፕሬዜዳንት ብቻ እንዲሆኑ ማድረግ ነው፡፡ የኔና በሃገሪቱ ያሉት የሪፓብሊካን ፓርቲ አባላት ብቸኛና ዋና የሆነው የፖለቲካ ተልዕኮ ይሄው ነው፡፡››  ሲሉ በሴኔቱ መድረክ ላይ ተናግረው ነበር፡፡

 

ፕሬዜዳንት ኦክሊንተን እንዳስተዋሉት፤ ፕሬዜዳንት ኦባማ ‹‹የወረሱት ባዶና የተሰናከለ ኤኮኖሚ ነበር፡፡ያንን የፈራረሰ ኤኮኖሚ ላማዳንና ወደ ነበረበት ለመመለስ ዘመናዊ መሰረት አዋቅረው፤ አስቸጋሪውን ጉዞ ተያያዙት፤ በዚህም ሚዛናዊ ኢኮኖሚ በመንደፍ ብዙ ሚሊዮን አስተማማኝ የሥራ እድል የሚፈጥር አደረጉት፡፡አሁንም መደረግ ያለበት በርካታ ጉዳይ አለ፡፡አዳዲስ ስራዎች መፈጠር አለባቸው፡፡በትምህርቱ ዘርፍ አዳዲስ ኢንቬስትመንቶች መምጣት አለባቸው፡፡የሥራ ስልጠናና አዳዲስ መዋቅሮች መዘርጋትም አስፈላጊ ነው፡፡ያም ሆኖ ግን በበርካታ ዘመናት ሂደት የተፈጠሩትን ችግሮች ሁሉ ፕሬዜዳንት ኦባማ በአንድ ተርም ውስጥ ማጠናቀቅ አይጠበቅባቸውም፡፡”

 

ፕሬዜዳንት ኦባማ፤ ኢትዮጵያና አፍሪካ

ሁል ጊዜም ፖለቲካዊ ንግግርና ፖለቲካዊ ተግባር ልዩነት አለው፡፡ በርካታ ትውልደ ኢትዮጵያ አሜሪካውያን በ2008 ምርጫ ወቅት በፍቅርና በእልህ ለባሮክ ኦባማ መመረጥ ደፋ ቀና ያሉ ደጋፊዎች፤  አሁን የተገባው ቃል አልተከበረም፤ ሁሉም ነገር ለይስሙላ የተባለ ነው በሚል ወቀሳ ይሰነዝራሉ፡፡ ለኢትዮጵያ ሊደረግ የታሰበውስ የፍትህ የሰብአዊ መብት የዴሞክራሲ ተስፋ ምን አጨለመው በሚል ቅሬታቸውን ያሰማሉ፡፡ የምር ግን ፕሬዜዳንት ኦባማን ግድ የለሽ በመምሰላቸው፤ በጉዳዩ ላይ ቀዝቀዝ በማለታቸው ልንወቅሳቸው ይገባልን?

 

እውነቱ ገሃድ ሊወጣ የግድ ነው፡፡ በኢትዮጵያ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ለዴሞክራሲ፤ ለሰብአዊ መብት እውነታነት፤ፕሬዜዳንት ኦባማ ያደረጉት አለያም ያላደረጉት እኛ ትውልደኢትዮጵያ አሜሪካውያን ካደረግነው ወይም ካላደረግነው ጥረት የተለየ አይደለም፡፡ ይህ ነው አፍጥጦ የሚያየን እውነት መቀበል ያለብን፡፡ የፕሬዜዳንቱ እርምጃ አለያም ያልተወሰደው እርምጃ፤የኛን ተግባር ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ መስታወት ነው:: ልክ እንደ ፕሬዜዳንቱ አባባል ሁሉ እኛም ለዴሞክራሲ፤ ለመልካም አስተዳደር፤ለሰብአዊ መበት ለኢትዮጵያና ለሌሎችም የአፍሪካ ሃገራት ያለንን ምኞትና ፍላጎት እንናገራለን እንመኛለን፡፡ ያም ሆኖ ግን ያንን በመተግበሩ ላይ ግን አልተሳካልንም፤ ከሽፎብናል፡፡ፕሬዜዳንት ኦባማ በአሜሪካ ብሔራዊ ፍላጎትና ደህንነት አተኩረው ነበር ያደረጉትም ያላደርጉትም፡፡ እኛ ደሞ በግላችን ችግርና በግላችን ደህንነት ላይ ተወጥረን ነበር ያደረግነዉም ያላደረግነዉም፡፡

 

በሶማሊያና በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ በነበረው የአልቃይዳ ችግር የኦባማ አስተዳደር፤ በኢትዮጵያ ያለውን የፍትሕ፤ የዴሞክራሲና የሰብአዊ መብት እጦትን ወደ ጎን ብሎት ነበር፡፡ በሶማሊያ ይካሄድ የነበረውን ጦርነት በመለወጥና የድሮን (አሮፒላን) ጣቢያዎች በመዘርጋት አጣዳፊውና የበሰለው ስትራቴጂ ነበር፡፡ በዚህም ሳቢያ የምርጫ ሂደቶች በገዢው መንግስት ሲጨናገፉና የምርጫው ውጤት ሲገለበጥና ተሸናፊውን አሸናፊ ሲያደርጉት፤ የነጻው ጋዜጣ አባላት ለእስር ሲዳረጉ፤ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ለግፍ እስር ሲዳረጉ አሜሪካ በሚያሳፍር መልኩ የአየሁትን አላየሁም የሰማሁትን አልሰማሁምን ዘዴ መረጠ፡፡ በኔ አስተያየት ያ ስህተት ነው፡፡ የአሜሪካ መንግስት በሶማልያ ሲያደርግ የነበረው ሽብርንና ሥብርተኞችን የመዋጋትና የማጥፋት ተግባሩ ጋር የማይተናነሰው በኢትዮጵያ ውስጥ የታየውና አሁን በመታየት ላይ ያለው የዴሞክራሲ፤የሰብአዊ መብት፤ የመልካም አስተዳደርና የፍትህ ጉድለት በእኩል ደረጃ ሊታዩ ይገባ ነበርና ነው፡፡

 

አስቲ ደሞ እኛ ትውልደ ኢትዮጵያ አሜሩካን የሆንነው በሃገራችን ስለፍትሕ፤ ስለሰብአዊ መብት፤ ስለዴሞክራሲ፤ስለመልካም አስተዳደር እጦት ባለፉት አራት ዓመታት ጊዜ ምን አደረግን?

 

በዚህ ጉዳይ ላይ ከመናገርና ለዚህም ሁኔታ ከመቆምና እነዚህን እሴቶች ተግባራዊነት ለማረጋገጥ አብዛኛዎቻችን ዝምታንና በታዛቢነት ራቅ ማለትን መርጠናል፡፡ አብዛኛዎቻችን በየግላችን የዴምክራሲንና የሰብአዊ መብትን ዋጋ ከፍተኛነት ስንነጋገር ስንመጻደቅ እንደመጣለን፡፡ያም ሆኖ ይህን እምነታችንን በአደባባይ ደፍረን ለመናገር ግን ሃሞታችን ይደክማል፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ደፍረን የተናገርን እንደሆነ፤ በኢትዮጵያ ያለው ገዢ መንግስት ቤታችንንና ኢንቬስትመንታችንን ይወስድብናል ብለን እንፈራለን፡፡ ወደ ሃገር ለመግባትም ቪዛ ከመከልከል አልፎ ሃገር ስንገባም ሊያስረን ይቸላል በሚል ፍርሃት ታጥረናል፡፡ በዚህም የግል ጥቅማችንንና ፍላጎታችንን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃገር አቀፍ ጥቅም ፍላጎትና ደህንነት በላይ አድርገን አስቀምጠናል፡፡

 

ከዚህም የከረሩና መመለስ የሚገባን ሌሎች ጥያቄዎች አሉ፡፡ባለፉት 4 ዓመታት የኦባማ አስተዳደር በሃገራችን ላይ ስላለው የዴሞክራሲ፤ የሰብአዊ መብት፤ የፍትሕ፤ የመልካም አስተዳደር እጦት አስፈላጊውን እንዲያደርግ ምን ውጥረት ፈጠርንበት?

 

በአስተዳደሩ ድምጻችን እንዲሰማ ተባብረን በአንድነት ቆምን?

 

የሕገመንግሥታዊ መብታችንን ተጠቅመን በዙህ ጉዳይ ላይ አስተዳደሩ ተጠያቂነቱን አሳወቅነው?

 

በግልጽና ሃቅን በያዘ መልኩ እኛ የኦባማ አስተዳደር ያደረገው ትክክል አይደለም፤ አስተዳደሩ ቃሉን አላከበረም ለዚህም ብለን ጣታችንን ወደ ፕሬዜዳንት ኦባማ በምንቀስርበት ወቅት የሶስቱን ቀሪ ጣቶቻችንን አቅጣጫ ብንመለከት ወደራሳችን ማመልከታቸውን እንረዳለን፡፡

 

እርግጥ ፕሬዜዳንት ኦባማ በኢትዮጵያና በአፍሪካ ስላከናወኑት ሁኔታ ቅሬታ ሊሰማን አግባብ ነው፡፡ የበለጠ ቅር ልንሰኝ የሚገባን ግን፤በራሳችን ጉድ ነው፡፡

 

ያገጠጠው እውነታ ግን በኢትዮጵያና በአፍሪካ ስላለው የዲክታተራዊ አገዛዝ የፕሬዜዳንት ኦባማ ሃላፊነት አይደለም እርግጥ ስለሁኔታው የሞራል ግዴታ አለባቸው ዲክታተሮችንም ደግፈው አብረዋቸው ሊቆሙ ተገቢ አይደለም፡፡ እንደ ፕሬዜዳንትም የአሜሪካንን ደህንነትና ፍላጎት ማስቀደም ተገቢ ነው፡፡እኛም የራሳችንን ፍላጎትና ደህንነት እንደምናስቀድመው ሁሉ፡፡ ለሁሉም ሚዛን ልናበጅለት ይገባል፡፡ማንም ቢሆን በመስታወት በተገነባ ቤት ውስጥ እየኖረ ድንጋይ ለመወርወር ቀዳሚ ሊሆን አይገባም፡፡

 

ፕሬዜዳንት ኦባማ ስለሰብአዊ መብት ከምርና ከልባቸው አስፈላጊነቱን ያምናሉ፡፡ ተግባራዊ ማደድረጉ ግን አስቸጋሪ ነው፡፡ባለፈው ስፕሪንግ፤ ሁኔታውን ረጂምና አድካሚ ትግል መሆኑን አስረግጠው ተናግረዋል፡፡ ‹‹የሲቪል ራይት እንቅስቃሴ በጣም አስቸጋሪ ነበር፡፡ለሴቶች መብት ድምጽ ማግኘትም አስቸጋሪ ነበር፡፡ለሰራተኛው ክፍል መሰረታዊ ጥበቃ ማስገኘትም አስቸጋሪ ነበር፡፡በዓለም ዙርያ ጋንዲም ማንዴላም ያደረጉት ሁሉ አስቸጋሪ ነበር፡፡ጊዜ ይወስዳል፡፡ከአንድ ትርም የበለጠ ጊዜ ይወስዳል፡፡ከአንድ ፕሬዜዳንት የበለጠ ይጠይቃል፡፡ከግለሰብም የበለጠ ሃይል ይፈልጋል፡፡የሚያስፈልገው ዕምነተ ጠንካራ የሆኑ ተራ ዜጎች፤ሃገራችን ወደ ክፍተኛው ጣሪያ ለማድረስ ሳይደክሙና ሳይሰለቹ ተስፋ ሳይቆርጡ የሚቆሙትን ነው፡፡”

 

ሰብአዊ መብትን በአፍሪካም ሆነ በኢትዮጵያ ለመጠበቅ አስቸጋሪ ነው፡፡ለኔልሰን ማንዴላ አስቸጋሪ ነበር፤ ለኦባማም አስቸጋሪ ነው፡፡እንደኛ ያሉ ዜጎችን ታግለውና በቆራጥነት ቆመው በኢትዮጵያና በአፍሪካ ለተግባራዊነቱ የሚሟገቱና እውን ለማድረግም የማይታክቱ የዜጎችን  ቆራጥ ተሳትፎ ይጠይቃል፡፡

 

ኖቬምበር 6 2012 እናስታውስ

በኖቬምበር 6 አንድ ጥያቄ ይጠብቀናል፡፡ ጥያቄው በኢትዮጵያ ስላለው ዴሞክራሲና ሰብአዊ መብት እጦት አይደለም፡፡ ጥያቄው በአሜሪካ ምን አይነት ሕብረተሰብ እንፈልጋለን የሚለው ነው፡፡ ፕሬዜዳንት ክሊንተን እንዳሉት፤ ‹‹ ከፈለግህ ብቻህን ነህና በራስህ ተወጣው››ን ከሆነ ምርጫህ የሪፓብሊካንን ቲኬት ቆርጣችሁ ተጠጋጉ፡፡ የእኩልነትና የጋራ እድልን ለመቅሰም የምትመርጡና የጋራ ሃላፊነትን ለመውሰድ ካሰባችሁና ‹‹በአንድነት እንወጣውን ሕብረተሰባዊ ስብስብ ካሰባችሁ ድምጻችሁን ለባሮክ ኦባማ ስጡ፡፡” በሚለው ሃሳብ እስማማለሁ::

 

የፕሬዜዳንት ኦባማ ሲናገሩ “የአሜሪካ  ህዝብ ሆይ ይህ ጉዞ ቀላል ይሆናል አላልኩም፤አሁንም ቢሆን አልልም፡፡አዎን፤ መሄጃችን አስቸጋሪ ነው፤ ሆኖም መድረሻችን የተሻለ ነው፡፡ አዎን ጎዳናችን ረጂም ነው ግን በአንድነት እንጓዘዋለን፡፡ ወደኋላ አንመለስም፡፡ ማንንም ወደ ኋላ እንተውም፡፡ተያይዘን በመደጋገፍ አብረን እንዘልቃለን፡፡ከድላችን ጥንካሬ እናመርታለን፤ከስህተታችን እንማራለን፤ ዕይናችንን ግን ባሻገር ባለው ጠፈፍ ላይ እናተኩረዋለን፡፡ደስታ ከኛ ጋር ነውና፡፡እናም የዚህ የተባረከ ሃገር ዜጎች በመሆናችን የተባረክን ነን፡፡”

 

በኖቬምበር 6 ለባራክ ኦባማና ለጆ ባደን ድምጼን እሰጣለሁ:: ምክንያቱም የዚያ ዕድልን በመካፈል ሃላፊነትን የሚወጣው የአሜሪካ አካል መሆንን ስለምመርጥ ነው፡፡ ፕሬዜዳንት ባራክ ኦባማን የምመርጠው ፍጹም ስለሆኑ ሳይሆን ሁሉም ጥቅምን በመካፈል፤ ሃላፊነትን የሚወጣ ፤ የተባበረና የተስማማ የአሜሪካንን ሕብረተሰብ ለመገንባት ቀና አቅጣጫ ስለያዙ ነው፡፡ ‹‹ሁላችንም በአንድ ላይ ለአንድነት የቆምን ነን::››

 

ፕሬዜዳንት ኦባማ በሚቀጥለው 4 ዓመታት ምን ማድረግ እንደሚገባቸውና  ከማረፋቸው ብዙ ጎዳና መጓዝ እንዳለባቸው ይገነዘባሉ፡፡ ገጣሚው ሮበርት ፍሮስት ቅኔያዊ በሆኑ ቃላቶች እንዳስቀመጠው ‹‹ጥሻው ወበት ፈሶበታል፤ጭለማና ጥልቀት ያለው፡፡ እኔ ደሞ ቃል ለምድር ለሰማይ ብዬ ቃሌን ሰጥቻለሁ፡፡ ስለዚህም ከመተኛቴ ማረፌ በፊት ብዙ ጎዳና ይጠበቅብኛልና፡፡

 

ፕሬዝዳንት ኦባማ አሁንም የሁሉንም ትውልደ ኢትዮጵያ አሜሪካናውያን ያልተቆጠበ የድምጽ ድጋፍ በኦሃዮ፤ቨርጊኒያ፤ፍሎሪዳ፤ሰሜን ካሎራይና፤ኮልራዶ፤ሚቺጋን፤ኔቫዳ፤ዊስኮንሲን እና በተቀረውም የአሜሪካ ግዛት  ሊያገኜ ይገባል፡፡ ሁለኩንም አንባቢዎቼን ፕሬዜዳንት ባሮክ ኦባማ በድጋሚ ምርጫ ለድል እንዲበቁ እጠይቃለሁ፡፡ አዎን አሁንም ይቻለናል…

 

የተተረጎመው ከኢንግሊዘኛው ጽሁፍ:  http://open.salon.com/blog/almariam/2012/09/09/why_i_am_supporting_president_obamas_re-election

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ