ጅሃዳዊ ሐረካት Jihadawi Harekat ለማየት የጓጓነው ዘጋቢ ፊልም

ነቢዩ ሲራክ - ከሳውዲ አረቢያ

"ጅሃዳዊ ሐረካት" ዘጋቢ ፊልም ”በኢትዮጵያ እስላማዊ መንግስት ለመመስረት ከሃሳብ ያለፈ እቅድ አላቸው" የተባሉት ተጠርጣሪ አሸባሪዎችን ገመና አንጠርጥሮ ሊያሳየን መሆኑን ሞቀ ደመቅ ደመቅመቅ ያለው የኢቲቪ ማስታወቂያ ልባችን አንጠልጥሎት ከርሟል።

 

ሳምንት በድምጽና በምስል በለፈፉትና በናኙት ማስታወቂያ የሙሰሊማን የመፍትሄ አፈላላጊ ኰሚቴ አባላት "አሸባሪ" አካሄድ በተጨባጭ መረጃ እንደሚያሳዩን የነገሩን የመንግሥት መገናኛ ብዙሃንን የተለመደ ስራ የማውቀው ሳይቀር ነፍሴ በአንገቴ እስክትወጣ ጉጉት አሳድሮብኛል።

 

ይህ መሰሉ ስሜት ለጊዜው ምንጩ ከየት እንደሆነ ባውቀውም ስሜቴን ተቆጣጥሬ በሰዓቱ ደረስኩ። ተመሳሳይ ስሜት አድሮባቸው እንደሁ በሚል እዚህ ሳውዲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውንን እየደወልኩ ስሜታቸውን መጠየቅ ያዝኩ። እውነት ነው! ኢቲቪ ሞቅ አድርጎ ማስታወቂያ መልቀቅ ከጀመረ ወዲህ የመንግሥት ደጋፊም ሆነ "መንግስት በጣልቃ ገብነት ሕገ መንግሥታዊ መብታችንን ነካ!" ብለው የተቃወሙ በርካቶች ማክሰኞን እንደኔ በከፍተኛ ጉጉት በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን ተረድቻለሁ። ከሁሉም በላይ ጉጉቴን የናጠው ደግሞ "የኃይማኖት ጣልቃ ገብነት ያቁም!" ባዮች አቀንቃኝ የሆነው የፌስ ቡክ ቡድን "የድምጻችን ይሰማ" ተከታታይ መረጃ ነበር። ይህ ቡድን ባቀረበው መረጃ ኮሚቴዎች በደረሰባቸው ከፍተኛ ድበደባና ስቃይ በሚቀርበው "ጃሃዳዊ ሐረካት" ዘጋቢ ፊልም ላይ ተገደው "በሉ" የተባሉትን ሁሉ ማለታቸውን በትረካ ሳይቀር አቀናብረውት መስማቴ ነበርና ይህም ሕመም ሆኖኛል። … (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!