ከኢትዮጵያዊ ማንነት አንጻር ለውይይት መነሻ እንዲሆን የቀረበ ጽሁፍ

መምህር ልዑለቃል አካሉ (ሲያትል፣ ዋሽንግተን)

መግቢያ

ሰሞኑን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መጽሐፈ ቅዳሴዋን ወደ ኦሮምኛ ቋንቋ ተርጕማ አሳትማለች። መሆን ያለበትና መደረግም የነበረበት ነው። በምርቃቱ መርሐ ግብርም የቀድሞውን ፕሬዝደንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስን ጨምሮ ብዙ እንግዶች ተገኝተው እንደ ነበር ታውቋል። ይሁን እንጂ ከግርማ ወልደ ጊዮርጊስ በቀር የላቲንን ፊደል በቅዳሴው ላይ መጠቀሟ ትክክል አለመሆኑን ያስታወሰ እና ለወደፊትም ቤተ ክርስቲያን እንድታስብበት የጠየቀ የለም ተብሎአል።

ከ15 ዓመታት በፊት ኢትዮጵያ ሳለሁ ከአዲስ አበባ ወደ ናዝሬት በምሄድበት ወቅት ደብረዘይት ላይ በላቲን ፊደል የተጻፈውን ማስታወቂያ በሱቆች ላይ ስመለከት ህዝባችን በታላቅ የማንነት ጥያቄ ውስጥ እንዳለ፣ የኦሮምኛ ቋንቋ በላቲን ፊደል መጻፍ አለበት ብለው የሚያምኑ ፖለቲከኞች የኦሮምኛ ተናጋሪዎች ኢትዮጵያውያንን ማንነት ይወክላል ብለው እና በሚገባ አስበውበት ነው ከዚህ የደረሱት? ወይስ ኦሮምኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያንን፤ ኢትዮጵያውያን አይደላችሁም ለማለት ፈልገው ነው? እያልኩ በማሰብ በጣም እገረም ነበር። እኔም በሀገሬ ላይ በባዕድ ሀገር ውስጥ እንዳለሁ ተሰምቶኝ ነበር። ምክንያቱም ለኦሮምኛ ተናጋሪዎች የማንነት መገለጫ ሊሆን የሚችለው የአፍሪካውያን ብቸኛ ፊደል የሆነው የግዕዝ ፊደል እንጂ የላቲን ፊደል አለመሆኑንዕ እንኳን አፍሪካዊ ምዕራባዊም ያውቀዋልና። ይልቁንም በምዕራቡ ዓለም ለትምህርትም ይሁን ለኑሮ ወጥተው የሚኖሩ ሁሉ ለአፍሪካዊ ማንነት ኢትዮጵያዊነት ምን ያክል ክብር እንደ ሆነ ይረዳሉ ብዬ እገምታለሁ። … (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!) 

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!