ይሄይስ አእምሮ

Tigrinya. ትግርኛ

መምህር ልዑለቃል አካሉ የተባሉ ኢትዮጵያዊ በቅርቡ በኦሮምኛ ቋንቋ የላቲን ፊደል አጠቃቀም ዙሪያ የጻፉትን መጣጥፍ ቆየት ብዬም ቢሆን ዛሬ አነበብኩት፤ ግሩም ነው። እሳቸው የሚሉት “ለኦሮምኛው ከላቲን ይልቅ የግዕዙ ፊደል አይቀርብም ወይ?” ነው። ይሄን ያህል ለምን ሩቅ ተሄደ ነው ጥያቄያቸው። ላቲኑን ለመጠቀም ለምን ያን ያህል ሩቅ መንገድ መጓዝ እንዳስፈለገም መልሱ በመጣጥፉ ውስጥ አለ - ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች በወያኔ በመታገዝ ሀገሪቱን ለመበታተን ከሸረቡት ሤራ አንዱ መሆኑ በስፋት ተጠቅሷል።

መጣጥፉ ከኢትዮጵያዊ ማንነት አንጻር ለውይይት መነሻ እንዲሆን የቀረበ ጽሁፍ ሲሆን፣ ርዕሱም “ከኢትዮጵያውያን ቋንቋዎች አንዱ የሆነው ኦሮምኛ ቋንቋ መጻፍ ያለበት በግዕዝ ፊደል ወይስ በላቲን ፊደል?” ይሰኛል፣ የመምህር ልዑለቃል አካሉን መጣጥፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ! 

እኔ የምለው ደግሞ ትግርኛም አማርኛም የላቲኑ ፊደል ያስፈልጋቸዋል ነው። የግዕዝ ፊደል ባየን ቁጥር በአንጻራዊ አነጋገር በጣም ውብና ቆንጆ የነበረችዋን የቀድሞዋን ኢትዮጵያ እያስታወስን በትዝታ ሰቀቀን ከምንንገላታ፤ እንደኔ እንደኔ ሁለቱንም እትማማች ቋንቋዎች በላቲኑ እንጻፋቸውና፤ ከዚህ ወያኔን ሽብር ከሚለቅበት ግዕዛዊ የአጻጻፍ ሥልት እንገላገል። ግን ግን ወያኔዎች ላማሮች ካላቸው ሥር የሰደደ ጥላቻ አንጻር የትግርኛውን ቋንቋችንን በላቲን እንዲጽፍ የትግራይን ህዝብ ያኔ ጥንት ሲነሱ ጀምሮ ያላስገደዱት ምን ወይም ማንን ፈርተው ይሆን? አስበውት አስበውት ሊሆንላቸው እንደማይችል ሲረዱት እነሱ የኛ ነው የሚሉትን ህዝብ የአጻጻፍ ዘይቤ ወደ ላቲን ሊለውጡ እንዳልቻሉ መገመት አያቅትም - ይብላኝ እንጂ ለሌላው ገራገር ወገኔ። የአማራው ህዝብም ከዚህ ወያኔያዊ መቅሰፍት ለጥቂት የዳነው በ“ኢሕዲን/ብአዴን ተጋድሎ” ሊሆን ስለሚችል የአማራው ህዝብ ለዚህ ብርቅዬና ቅን አሳቢ ቅንቅን ድርጅቱ ባለውለታ ነው ማለት ይቻላል። እግዜር ይስጥልን ውድ የአማራው ህወሓት ብአዴንዬ። እናንተ ባትኖሩ ኖሮ ይሄኔ baattam eenichagaar nebbber, “በጣም እንቸገር ነበር” ለማለት ፈልጌ ነው በላቲን ፊደል ስራቀቅባችሁ።

እኔ ዛሬ ልጀምረውና ከሁለቱም ቋንቋዎች አንድ አንድ አንቀጽ በመጻፍ በላቲን ፊደል መጠቀም እጅግ ቀላል መሆኑን ለትግርኛና አማርኛ ተናጋሪ ወገኖቼ በተግባር ላስረግጥ። ከዛሬ ጀምሮ ታዲያ በላቲን ፊደል የማይጽፍ ትግሬና አማራ ቢገኝ ውርድ ከራስ - ሁልሽም ይህን አጻጻፍ ልመጂና አንድ ዐረፍተ ነገር ለመጻፍ ዕንቅብ ሙሉ ወረቀት ፍጂ። ይህን ትዕዛዝ አለመፈጸም ከሦስት ዓመት እስከ 15 ዓመት ጽኑ እሥራት ያስቀጣል - ልክ የቀድሞውን ሰንደቅ ዓላማ ሲያውለበልብ እንደሚያዝ “ፌዴራላዊ” ዜጋ! ወይ እኚህ ነጫጭባዎች! የዐድዋንና የአምባላጄን ሽንፈታቸውን ሳይዘነጉ ዘመን ጠብቀው ወኔያችን ላልቶ ክንዳችን መዛሉን፣ ዝናችን መጠየሙንና ታሪካችን መደብዘዙን አይተው በገዛ ወገኖቻችን ተበቀሉን አይደል? ግዴለም። እነሱንም እንዲህ የሚያዝረጠርጥ መከራና ስቃይ ይመጣባቸዋል። እነሲአይኤና ሞሳድ የስም አጠራራቸው እንኳን በታሪክ የማይወሳበት ወርቃማ ዘመን እየመጣ ነው - ሊነጋጋ ሲል መጨላለሙ እውነት በመሆኑ ይህ ዘመን የድቅድቅ ጨለማ ዘመን መሆኑ የግድ ነው። ለአብነት ወደምጽፍላችሁ ወያኔያዊ የፊደል ሠራዊት ልውሰዳችሁና ዛሬስ በጊዜ እንፋታ። እንዲያው የላየ ላይ በል በል እያለኝ እንጂ የሚጻፍበት አጀንዳ ተሟጦ አዲስ ነገር እያጣሁ ተቸግሬያለሁ፤ የምጽፈው የማይገባው ኦነግንና ህወሓትን ይጠይቅ።

Yaamariignaw aanniqaatsii yiihhinnin yiimmaassillal

Huulaachihoom aammaarouch beyyaalaachihuubett enniddamiiin saanabbettachchihuu. Inniee fattarrii yeemaasgheen dahhinnaa naagn. Baallaafaouw ssemmoon aaandi mattattiiiff be’intterrneeit likkee sle’eettioopiaa ayyyer maanghed enndaasneebebbkuachihhuu aatzannagguum. … ኤጭ የምን መጃጃል ነው - በቃኝ እባክህ። አጃጅሎ ከሚያጃጅል የብልጥ ሰው ዐረመኔያዊ የተንኮል ሤራ ይጠብቃችሁ።

naayttigirrignaa aanniqaatsii kaammzzisseeb yiimasssiil

ziittefaattewukeen ziittefeeqqerkeen aaddii seebb Tiigraayy keemeelaahuummeyii, anne biiffiirqqi’aan naattkhan zikhonkooo wooddii eettioppia Yiihheyyiss aaaemroo ziibbhaal see’eb khaab zelookhuowo aaddii koyyinney zeeseddidelkka ddebbddabbe khemzziibetsihakha ye’aamminn. Bezhhaaleffe soomunzii bizza’eba eeettioopia nefariit maanghaddi ghhelle tsiihhuuf saaddide nee’yyirre khhemzenbbebbkha yeeammin … ዋይ የአኽለኒባ፣ ከመይ ዓይነት አሌታዊ ሸግር እዩ ዝገጠመና!

አዎ፣ ውድ ኢትዮጵያውያን ማሽላ ሲያር ይስቃል። ውኃም ሲወስድ እንደዚሁ እያሳሳቀ ነው። ከፍ ሲል እንደጠቀስኩት እነዚህ ፈረንጆች የገዛ ሰዎቻችንን ተጠቅመው ታሪካዊ ቂማቸውን እየተወጡ ነው። በሰው ቁስል እንጨት መስደድ ቀላል ነው። ወያኔዎች ማድረግ ስለቻሉ ብቻ ብዙ ኢትዮጵያውንን ከኢትዮጵያዊነት የጋራ ኑባሬና ማዕድ እያስወጡ ነው። ሸሩን ያላወቁና አዲስ ነገር ብርቅ የመሰላቸው የዋሃን ደግሞ የተጠመደባቸውን ፈንጂ ሳይረዱ ወጥተው አናቱ ላይ ቁብ ብለው የመፈንጃውን ጊዜ በጉጉት እየተጠባበቁ ያሉ ይመስላል። ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ነበር ጠልፈው የጣሏት። “እንዴ፣ አንቺስ ምን ይጎድልሻል? በሬ እኮ ነሽ! በይ ነይ በዚህ ገመድ ውስጥ አንገትሽን አስገቢና ወጉ ይድረስሽ።” የወደደ በገመዱ ይግባበት። ሲነጋ ግን ሁሏም የሀፍረት ሸማዋን ተከናንባ መግቢያ ቀዳዳ ታጣለች። ክፋትን መሥራት የመጨረሻው ቀላል ነገር ነው። የእግዜር ፍርድ ሲዘገይ የቀረ የሚመስላቸው ገልቱዎች እጅግ ብዙ ናቸው። ሞት ሲዘገይ በዚያው የሚቀር የሚመስላቸውም እንዲሁ።

በመሠረቱ አንተ የምትጸየፈውን ምግብ ለሰው አትሰጥም፤ አንተ የምትጠላውን ልብስም ሆነ ማናቸውም ነገር ለሰው ብትመጸውት ነውር ነው። አንተ የማትጠጣውን መጠጥ ለሰው ብትጋብዝ ወንጀልም ነውርም ኃጢኣትም ነው። ወያኔዎች የላቲንን ፊደል ለሌሎች ኢትዮጵያውያን ዜጎች በግዳጅ የጣሉባቸው ኢትዮጵያን ያፈራረሱ መስሏቸው ነው - በርግጥም ለተወሰነ ጊዜ ይህን የዘመናት ተጋምዶና ተመሳሳይ ሥነ ልቦና ሊያደበዝዙት ይችሉ ይሆናል፤ እየቻሉም ነው። ቁናውን ባሰፉት ቁጥር ይበልጥ የሚጎዱት እነሱ እንጂ ተቀባዩ ብቻ አይደለም። ለነሱ መልካም የብቀላ ዘመን ይሁንላቸው። እኛ ግን ወያኔያዊ ብል የቀዳደደውን የታሪካችንን ቡልኮ በአፋጣኝ ለመጠገንና ወደቀድሟችን ለመመለስ እንዘጋጅ፤ ኢትዮጵያ ለየት ትላለች፤ ነገ ሌላ ቀን መሆኑን የምናይ እናያለን። ይህ ደግሞ እንደኒኩሌር ሣይንስ የመንኮራኩር ማምጠቂያ ፊዚክሳዊ ቀመር የሚከብድ ሣይሆን አምናና ታች-አምናን በማየት ብቻ በቀላሉ የምትደርስበት ታሪካዊና ለሚያምኑ ደግሞ መለኮታዊ ብይን ነው። …

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!