TPLFተሻለ መንግሥቱ

በብሂለ ግዕዝ “ትንቢትሰ ይቀድሞ ለነገር” ይባላል። አንዳንድ ነገሮችን በአፍ ወለምታም ይሁን በቴሌፓቲክ የነገሮች አፈጻጸም ሂደት ቀድመው ይጠቀሳሉ። መለስ ዜናዊ ስለአክሱም ሐውልት የይገባኛል ጥያቄና የባለቤትነት ይዞታ ሲናገር መረንን በማያውቀው ስድ አንደበቱ በርዕሴ ላይ የጠቀስኩትን ከፋፋይ ሃሳብ በገሃድ ተናግሯል። ለነገሩ መለስ ያልተናገረው ጠያፍ ነገር የለም። የአንዲት ሀገር መሪ ሆኖ ራሱን ሾሞ ሲያበቃ ሌሎችን እንደጨርቅ እርሱ የወጣትበን ጎሣ ግን እንደወርቅ መመሰሉን በአደባባይ ገልጾ እርሱና እርሱን መሰሎች ሀፍረትን ባያውቁም እኛ ስለነሱ አፍረናል።

መለስ የራሱ ዘር ከጎጃም ዐማሮች እንደሚሳሳብ አላወቀም ዌም ሊያውቅ አልፈለገም። በዚያም ላይ ደሙ በልጆቹ እናት በአዜብ ጎላ በኩል የጎንደር ዐማሮች ዘር ውስጥ መግባቱን አላወቀም ዌም ሊያውቅ አልፈለገም። መለስ ዕንቆቅልሽ ሕይወት እንደኖረ ችግሩን ማንም ሳያውቅለት በሽፍን ሄደ። ያሳዝናል። እርሱን መሰል ሌሎች በጥባጭ ዜጎችም እንደርሱው ያለ የተመሰቃቀለና በማንነት ኪሣራ የተዘፈቀ ሕይወት እየመሩ ሀገርንና ህዝብን እንደሚያውኩ በሕይወት ያለውን ወጣቱን ግማሽ ዐማራ ፖለቲከኛ በማስታወስ መረዳት ይቻላል። (በእናቱ በኩል መንዜ መሆኑን ያልደበቀውን ወጣትና መልከ መልካም ፖለቲከኛ ማለቴ ነው)

የሚገርመኝ ግን መለስ ከንቀቱ ብዛት “የአክሱም ሐውልት ለወላይታው ምኑ ነው” ብሎ ያኔ ከመነሻው እንዳላፌዘና እንዳልዘበተ ለዚህ ኃይለማርያም ለሚባል ስሙና ምግባሩ እንዲሁም ፈለገ እምነቱ ለማይገጣጠሙለት ከወላይታ ህዝብ ለተገኘ ዜጋ ለይስሙላም ቢሆን የም/ጠ/ ሚኒስትርነቱን ቦታ መስጠቱ ነው። የጠቅላይ ሚኒስትር መለስን ቃል ገልብጠን በመዋስ “ጠቅላይ ሚኒስትርነት ለወላይታው ምኑ ነው?” ብንል በሰው ቀለዳችሁ እንባል ይሆን? አስገራሚ ግጥምጥሞሽ። መለስ ፍጹም ታዛዥና ሽቁጥቁጥ አሽከር እንዴት እንደሚመርጥ በደንብ ያውቃል።

በነገራችን ላይ ወያኔዎች ኃይለማርያምን ገና ወደፊት እስከጥግ ይጠቀሙበታል። ጥሩ ፈረስ ነው ያገኙት። አንድ አምባገነን የህወሓት አባል ቤተ መንግሥት አስገብተው ነፃነታቸውን ማጣትና በአንድ ሰቅለው ማውረድ በሚያቅታቸው ወያኔ ምክንያት ዳግመኛ መንገብገብን አይፈልጉም። ሁሉም እንዳሻቸው የሚያዙትን የሚፈጽምና በስልክ የሚያሽቆጠቁጡት ሰው መመደብ እየቻሉ ለምን በገዛ ፈቃዳቸው እሥር ቤት ይገባሉ? የመለስ ጠ/ሚኒስትርነት ብዙ አስተምሯቸዋልና ከአሁን በኋላ ስድስት ወርም ይቆዩ ዓመት ፎርጅድ እንጅ ኦሪጂናል ወያኔን ቢሞቱ አራት ኪሎ ቤተ መንግሥት አያስገቡም - በፈለጋችሁት እምላለሁ፤ በዚህ ቀልድ የለም። ኃይለማርያምን በሆነ ነገር ቢጠሉት ከኦሮሞና ከፈረደበት ዐማራ ብሔሮች ሣይሆን ከሌላ በህዝብ ቁጥር አነስተኛ ከሆነ ጎሣ እንደ ኃይለማርያም ሁሉ የሱንም ጭንቅላት በሥውር ቀዶ ሕክምና አስወጥተው ባዶ ቀፎውን ቤተ መንግሥት ውስጥ ያስቀምጡና ይቀልዱበታል። ያ ሰው ጭንቅላት የሌለው ቡልሃ (moron) መሆኑን ካላረጋገጡ የቤተ መንግሥት ጠባቂነቱን ቦታ አይሰጡትም፤ ደግሞም ያን መሰሉን ሰው ልክ እንደ ኃይለማርያም ሁሉ የቤተ መንግሥት ጽዳትና አትክልኛ የሆነ ትንሹ ወያኔ ሣይቀር ሽንቱን በሱሪው እስኪለቅ ድረስ እያስፈራራ ያዘዋል - እያላገጠበትና እየተንቀባረረበት። ሰውዬው ባጭሩ “ህወሓት ሥልጣን ለሌሎች ያጋራል” እንዲባል ለይስሙላና ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የድጋፍና ዕርዳታ መጠየቂያ የሚጎለት ጉልቻ ነው። የሚገርም የሰው ጉልቻ።

ወደቀደመው ነገራችን እንግባና፤ እውነት ነው ጠቅላይ ሚኒስትርነት ለወላይታው ምኑም አይደለም። “የሰው ጥርስ ስቀው አያምሩበት፣ ግጠው አይበሉበት” እንላለን፤ “የተውሶ ይመለሳል ታጥቦ ተተኩሶ”ም ይባላል። የኢትዮጵያ ሥልጣን ሙሉ በሙሉ የተያዘው በህወሓት ነው። ይህን ግልጽ እውነት እንደየፍላጎታችንና የፖለቲካ አመለካከታችን ልንክደውም ልንቀበለውም እንችላለን። እውነቱን ግን አንለውጠውም። (ጎንደር ውስጥ ወያኔ አሁን እየገደለብን ያሉትን ዜጎች ነፍሳቸውን እግዜር ይማር።)

በቀደምለት የደረጀ ነጋሽን ድረ ገፅ ስጎበኝና አንዳንድ ግሩም መጣጥፎችን ሳነብ ከዚህ በታች ያለውን ካርቱን አገኘሁ። በጣም አሳቀኝ፤ እውነቱን በቀልዳዊ ስዕል ስመለከት የሀገራችን ቲያትር ቁልጭ ብሎ ታየኝ። ረጂም ዕድሜ ለከያኒያንና ለድረገፆቻችን። ትልቅ ሥራ እየሠሩ ነው። እነሱ ባይኖሩ ከናካቴው ዳፍንት ወርሶን ነበር፤ ከመንጋት መምሸቱ ውጪ የምናውቀው ነገር ባልነበረ። በተለይ ኢሳትንማ ተዉት …

ይህ የኔን ጨምሮ እንደአንዳንዶቻችን አካላዊው ዐይኑ ብቻ ሳይሆን አንጎሉም ጭምር የተንሸዋረረ ሰውዬ ምን ያህል የወያኔ መጫወቻ እንደሆነ፣ እኛም የሲአይኤና የሞሳድ እሥረኛ እንደሆነ በሚነገርለት ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ተብዬው ምን ያህል እየተቀለደብን እንደሆነ አጥንቴ ድረስ ዘልቆ ተሰማኝ። ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ እንደመስበሩ ዘመኑ እስኪብት የምናየውን የግፍ ድራማ ሁሉ ተገደን ከማየት በስተቀር ሌላ አዋጭ ምርጫ የሌለን መሆናችንን ሳስበው ደግሞ የበለጠ ተከፋሁ። በጥቂቶች የታሰረች እውነት ነፃ እስክትወጣ ቢሊዮኖች በመከራ እየማቀቁ መቆየታቸው የማያመልጡት መራራ ሐቅ ነው። እርግጥ ነው - ቢሊዮኖች ሲነቁና ወደኅሊናቸው ሲመለሱ የጥቂቶችን ሰቆቃና የግፍ አገዛዝ ከትከሻቸው አሽቀንጥረው ይጥላሉ። ሁነኛ አመራር ጠፍቶ እንጂ ብዙኃኑ ኃይልና ጥበብ አጥተው እንዳልሆነም መገንዘብ የሚቻል ይመስለኛል። “የጊዜ እንጂ የሰው ጀግና የለውም” ይላሉ፤ እውነት መሆን አለበት።

የመለስ ዜናዊ የጡት ልጅ ኃይለማርያም ጥሩ አሽከር ነው። በአሽከርነቱም አንድ የኮሌጅ መምህር ቀርቶ ተራ የመንደር ሀብታም የማያገኘውን ዕድል አግኝቶ በኔና ባንተ ገንዘብ ዐይን አስለውጧል አሉ፤ እኔ ቲቪ ስለሌለኝ አላየሁትም። ግን ጀርመን ሀገር ሄዶ በብዙ የሀገር ሀብት ወጪ በውድ ዋጋ ዐይኑን አስጠግኖ በወረት እሽቅንድር እያለ ነው የሚል ወሬ በከተማችን በስፋት ይናፈሳል፤ እነሱ ዋኖቹ ወርቃችንን ከጓዳችን እየዛቁ ለልጅ ልጆቻቸው ሲያከማቹ እነኃይለማርያም ደግሞ በአሽከርነት በሚሰጣቸው እንጥፍጣፊ ጤንነታቸውንና ውበታቸውን ያስጠብቃሉ፤ በዚያ ላይ ነገን የሚደርሱባት ከሆነ ለነገ የሚሆናቸው ርዝራዥም አያጡም። እንደኔ ግን ሸውራራና ሞራ የጣለበት ዐይን ሀገራዊ ጉዳቱ ቀላል ነው እላለሁ - ስለሆነም ጠቅላላውን የዐይን ብርሃን የሌላቸው ሆሜርንና ሄለን ኬለርን የመሳሰሉ ድንቅ የዓለማችን ዜጎች ስንትና ስንት ዘመን ተሻጋሪ ሥራ እንደሠሩ ለሚረዳ ንቁ ዜጋ የኃይሌ አካላዊ ሸውራራነት በመሠረቱ ምንም አልነበረም። ወዶ ባላመጣው ተፈጥሯዊ የጤና ችግር ይህን ያህል ሊሳቀቅና ድሆች በረሃብና በበሽታ ከሚያልቁባት ሀገራችን የተራቆተ ካዝና ብዙ ገንዘብ ወጥቶ የፊት ውበት ዕድሳት ሊደረግለት ባልተገባ፤ እርሱም ፈቃደኛ ሊሆን ባልወደደ ነበር። ይልቁንስ አንጎል ላይ የወደቀ ሞራና የተንሸዋረረ አስተሳሰብ የሚያስከትለው ዳፋ ብዙ ዋጋ እንደሚያስከፍል መረዳት ነበር የሁላችንንም የጋራ ስምምነት ሊያገኝ የሚገባው አስተሳሰብ። እነመለስ ዜናዊ በዚህ የተንሸዋረረ የአስተሳሰብ ቅኝት እየተመሩ ነው አንዲት ሀገር ድራሹዋን ያጠፉት። እንጂ መልክና የመልክ ውበትማ 50 ስትገባ እኮ እየከዱህ ይሄዳሉ - ኧረ ዛሬ ዛሬማ በአሥራዎቹ መጀመሪያ ላይ የሚሸብትና ከሃያዎቹ የማለዳ ዕድሜ ጀምሮ ደግሞ የሚመለጥም ታዳጊና ወጣት ሞልቷል። ነፍሱን ይማረውና “ዘመነ ግርምቢጥ ውሻ ወደግጦሽ፣ አህያ ወደሊጥ” ነበር ያለው ኃይሉ ገ/ዮሐንስ (ገሞራው)? በስልሳና በሰባ ምርኩዝ በሚያዝበትና በሰማንያ ፊት ተጨማዶ፣ ዐይን ተጋርዶ የከዘራ ያለህ በሚባልባት ድሃ ሀገር ውስጥ ለዐይን ውበት ተብሎ ከረሃብተኛ ጉሮሮ ብዙ ገንዘብ መዝረፍና በውድ ሐኪም ቤት መታከም ወንጀልነቱን በሕግ ብናለዝበው፤ ኃጢኣተኝነቱን ግን በምንም ብልሃት ሥርየትን እንዲያገኝ ልናደርገው አንችልም። ጦም ከሚያድር ሰው ቀምተህ እንዴት ኩል ትኳላለህ? ነውር ነው!

ይቺን ከዚህ በታች ያለች የኃይልዬን ካርቱን ተጋበዙልኝና ተዝናኑ፤ ምንጩን ከፍ ሲል ጠቅሻለሁ። የምታስደንቅ ሀገር ውስጥ እንደምንኖር ለአፍታም ቢሆን መዘንጋት አይገባንም። ችግሩ ግን ይህን ታሪካዊ የምቾትና የጥጋብ ዘመናችንን የተረዳልን፤ ተረድቶም በአስደናቂ ታሪክ መዝገብ ሊያሰፍርልን የሞከረ ሰው ማጣታችን ነው። If anyone of you have any slightetst chance of accessing the office of ‘Guinness Book of Records’, please do try your level best to get our country registered in connection with the TPLFite honor she has been lucky enough to obtain especially in the past 25 years. Do it now, tomorrow maybe too far and untimely. (teshalem1@ጂሜል.com)

TPLF

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!