ዮፍታሔ

GODs eye

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጃችኋል።

በግልጽ አፋኝ የሆነ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈጻጸምና ዝርዝር ደንብም አውጥታችኋል።

ከዚህ ቀደም ሁሉን አድራጊው ራሱ ያልሆነ ይመስል፤ "ኮማንድ ፖስቱ የሀገር መከላከያ ኃይል፣ የፌዴራል ፖሊስ እና የክልል መንግሥታት ልዩ ኃይሎችን ያካተተ" መሆኑንም በመግለጽ አላግጣችኋል።

እንዲህም ሆኖ የራሳችሁን ሕገ-መንግሥት ታከብሩ ከሆነ ሌላ የሚቀራችሁ ነገር አለ። እንደማይጠቅም ብናውቅም በሰነድ ይይዘው ዘንድ ህዝቡ ይከታተላችኋል።

የተወካዮች ምክር ቤት ከራሱ ከአባላቱና ከሕግ ባለሙያዎች መርጦ የሚመድባቸው "ሰባት አባላት ያሉት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ" አባላትን አላሳወቃችሁም። ለይስሙላም ቢሆን ይህ አካል ብቻ ነው በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የምትሠሩትን "ኢሰብዓዊ" ድርጊት የሚከታተለው። ይህ ቡድን የታለ? አባላቱስ እነማን ናቸው? እንዲህ ዓይነት አፋኝ አዋጅ አውጥታችሁ፣ ስልክና ማኅበራዊ መድረኩን ዘግታችሁ፣ ዲፕሎማቶች እንኳን ከአዲስ አበባ 40 ኪሎሜትር በላይ ርቀው እንዳይሄዱ በተከለከሉበት፤ የምትፈጽሙትን ግፍ ማን ይከታተላችኋል? የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ የማቋቋምና አባላቱን የማሳወቅ ግዴታ አለባችሁ።

ሌላም አለ። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ለተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተወካዮች ምክር ቤት በሁለት ሦስተኛ ድምፅ መፈቀድ ይኖርበታል።

ለራሳችሁ ሕገ-መንግሥት እንጥፍጣፊ እንኳን ክብር ካላችሁ፤ ይህን የማድረግ ግዴታ አለባችሁ። የእግዚአብሔርና የህዝብ ዓይኖችም በናንተ ላይ ናቸው።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ