Graduationተሻለ መንግሥቱ

ከኢትዮሚዲያ ድረገጽ ያገኘሁትን አንድ በፈረንጅ አፍ የተጻፈ መጣጥፍ ይዤ ሳነብ የንባብ ፍላቴን ማረከውና ዘለቅሁት። በዚያም አልበቃኝም። እዚያው መጣጥፍ ውስጥ በተጠቆመ ማስፈንጠሪያ (ሊንክ) ወደ ኢካድፎረም ድረገጽ አመራሁና በዶክተር ተድላ ወ/ዮሐንስ የተጠቀሰውን የፀጋየ አራ አርሳ ፌስቡካዊ ንግግር የተተቸበትን የራሱን የተድላን ትንሽ ቆየት ያለ የሚመስል ጽሑፍ አነበብኩ ... አነበብኩ እንኳን ሳይሆን በንዴት ተቃጠልኩ ነው ማለት ያለብኝ - ለነገሩ እንዲህ ዓይነት የታሪክና የትውልድ ጭንጋፎች በአነስተኛው የሚፈልጉት እንዲህ ዓይነቱን የዜጎችን በንዴት መንጨርጨር ነው። ወፍ ዘራሾች አዕምሯዊ ሥሪታቸው ወይም የአስተሳሰብ ቀመራቸውና ነገረ ሥራቸው ሁሉ ግራ በመሆኑ የሚያስደስታቸው የሚያሳዝን ነገር ነው። ያን ጽሑፍ ስጨርስ ነው እንግዲህ በመግቢያየ ባስቀመጥኩት ርዕስ የተሰማኝን እንደወረደ ለማስቀመጥ ብዕር ያሳሁት። ይህን ግን ያዙልኝ፡- እንደኢትዮጵያ የተረገመ አገር የለም!!!

እውነቴን ነው በኢትዮጵያ ሁኔታ መማር አደንቋሪ ነው - ከንቱም ጭምር።

ዋለልኝ መኮንን የተባለ የደናቁርት ክበብ አባል ተማርኩ ተመራመርኩ ብሎ በገዛ ወገኖቹ በአማሮች ላይ ምን ሠርቶ እንደሄደ እዚህ ላይ ማውሳቱ ሙት መውቀስ ነውና ይቅርብኝ። ከዚህ ልጅ በፊትም በኋላም ትምህርት ያደነቆራቸው ብዙዎች አማሮችና የሌሎች ነገዶች አባላትም ሞልተዋል።

ልደቱ አያሌው የተባለ ደንቆሮ - ይቅርታ ለዛሬ ይህች ቃል የኔ የነገር ማሳመሪያ ቅመም ናት - ልደቱ አህያሌው የተባለ ደነዝ በልቶ ለማይጠረቃው ሆዱ ሲል ከወያኔው የትግሬዎች ማፊያ ቡድን ጋር ሲያሻው በኅቡዕ ሳያሻው በግልጥ እየተሞዳሞደ የተማረውን ትምህርት ሁሉ እንዴት ገደል እንደሰደደው የምናውቀው ስለሆነ እሱንም አናንሳው። እዚህ ላይ ክህደቱ አያሌውንም ሆነ ሌሎችን እየጠቀስኩ “ተምረዋል/አልተማሩም” ስል በደንቡ መሠረት ክፍል ገብቶ ለማለፍ ለመውደቁ የምሥክር ወረቀት እየተሰጠ የሚታለፍበትን የትምህርት ሂደት ማለቴ እንጂ፤ የህወሓቱ የሽፍቶች መንግሥት በተካነበትና እንደሕጋዊ አድርጎ ጭፍሮቹን የሚያጥለቀልቅበትን የግዢና የሐሰት (ፎርጅድ) ዲግሪ አይደለም።

ገነት ዘውዴ ከነዘመዶቿ ራሷ የወጣችበትን የአማራን ዘር በተለይ በማይምነት አለንጋ በማስገረፍ በኩል ያደረገችውን ታሪካዊ ተሣትፎ ራሱ ታሪክ ይያዘው እንጂ ከሁላችንም አዕምሮ በላይ ነው።

በግለሰብ ደረጃ ስንቱን አንስተን እንዘልቀዋለን? ተከድኖ ይብሰል እንጂ በአጠቃላይ ኢትዮጵያንና በተለይ ደግሞ የኢትዮጵያዊነት አንዱ መሠረት የሆነውን አማራን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ከትግሬዎቹና ከአዛዦቻቸው በበለጠና በከፋም ደረጃ የሠሩና እየሠሩ ያሉ አማሮች ብዙ ናቸው - “ጥቁር ውሻ ይውለዱ!” ብዬ በበኩሌ ረግሜያቸዋለሁ። እነዚህ ከውስጥ ምንደኞችና ከውጭ ኃይሎች ጋር በመመሣጠር የገዛ የዘር ሐረጋቸውን በማጥፋት ላይ የሚገኙ አማሮች ሁሉ ክፋታቸውንና የሆዳቸውን ስፋት በትምህርት አማካይነት “ያሻሻሉና ያዘመኑ” ናቸው። ከነዚህ ተማሩ ከተባሉ ከሃዲዎች ይልቅ ምንም ያልተማረው ባላገር ለሀገሩ ብዙ ተዓምር እየሠራ ነው - በተለይ አሁን። ወደፊት ደግሞ ገና ይታያል። “ግምበኞች የናቋት ድንጋይ የማዕዘን ራስ ሆነች” ይላል ፍርድ አስተካካዩ ክርስቶስ።

በብአዴን ስም የተደራጁ ይሁዳዎች ደግሞ ብዙዎቹ ምን እየሠሩ እንደሆነ እኛም ባለንሥር ዐይኖቹ ታሪክም እየመዘገብነው ነው። ሁሉም ምንዳውን ስለሚያገኝ በዚህ በኩል ሃሳብ አይግባን፤ ማንም ይሁን ማን የመሰለውንና ያመነበትን ያከናውን። ወቅቱ ደርሶ ምርቱ ከግርዱ፣ ፍሬው ከገለባው፣ እንክርዳዱ ከስንዴው በሚለይበት የመኸር ወቅት ዐውድማው ላይ የሚለየው ይለያል። በስመ አብ፣ የትምህርት ጉዳይ ግን አዲዮስ! ትምህርት አዕምሮን ማስፋትና ወልጋዳ አስተሳሰብን ማቃናት ሲገባው አለተፈጥሮው ሆድን እያንዘረጠጠ ስንቶችን መና አስቀረ። የት ይደርሳሉ የተባሉ ጥጆችን በሉካዳ ቤት ደጃፍ እንዲልከሰከሱ እያደረገ ብዙ ጉድ ሠራን። ያሳዝናል። ትምህርት እንዲህ ከሆነ ባፍንጫ ይውጣ።

የነዲባቶ ፀጋየ ደግሞ ትንሽ ለየት ይላል - ለነገሩ አይለይም። መበላሸት መበላሸት ነው። ብልሽት ደግሞ ዘርን አይለይም። ክፋትና በጎነት የጎሣና የነገድ ዳር ድንበር የለውም። ስለዚህ ተያይዘን ጠፍተናል ማለት ነው የሚቀለው። ዘመናችን የመጥፋት ዘመን ሳይሆን አልቀረም። ማርከሻውን በተሎ ያምጣልን።

ተድላ ወ/ዮሐንስ ድከም ብሎት ስለነፀጋየ ዓይነቶቹ በቁም የጠፉ ዜጎቻችን ደጋግሞ የጻፈ ይመስለኛል። እኔም ለምን ይቅርብኝ ብዬ ነው። በዚህ አጋጣሚ “እነ ...” በሚል የምጠቀልላቸው የፀጋየ የሃሳብም ይሁን የትውልድ እኩዮች በቁማቸው መሞታቸውንና በፀረ-ሕዝብና በፀረ-አገር ዘመን-ወለድ ልምሻ መሽመድመዳቸውን በመጠቆም ከነሱ ጋር ሕብረት ሊፈጥር የሚዳዳውን ኢትዮጵያዊ ሁሉ ጆሮውን እንዲያውሰኝና የምለውን እንዲሰማኝ ማሳሰብ እፈልጋለሁ።

ኢትዮጵያ እንደእስካሁኑ ሆደ ሰፊ ሆና የምትቀጥል አትመስለኝም። እንደእስካሁኑ የአዕምሮ በሽተኛ ልጆቿን እያስታመመችና ባለጌዎችን በጨዋዎች ላይ እያነገሠች ከአሁን በኋላ በኢዮባዊ ቁስል ለመንፈር ፈቃደኛ የምትሆን አትመስለኝም። እንደእስካሁኑ አንዱ ከሌላው በሚቀጥል እልህ አስጨራሽ የስቃይ አዙሪት የምትገባና የዋህና ገር ልጆቿን ለተጨማሪ መከራ የምትዳርግ አይመስለኝም። ስለሆነም ሁሉም አፈንጋጭ ቆም ብሎ ማሰብ የሚገባበት ዘመን ላይ የደረስን ይመስለኛል። የማነበው የፍየል ሞራ ገልጬ አይደለም፤ አቦል ቡና የተጠጣበት ስኒም አጠገቤ የለም። መጽሐፍ ገልጬ ወይም ኮከብ ቆጥሬም አይደለም። ነገር ግን አምላከ ኢትዮጵያ እንዲህ በል በል ይለኛል። ዱሮም ብዙ ነገር በል በል ብሎኝ ብዙ ነገሮችን አይቻለሁ፤ በወቅቱም ተናግሬ ባለመደመጤ (ጥቂቶችም ብንሆን እንጮህ ስለነበር “ባለመደመጣችን” ብል ‹ጉራየን‹ የሚቀንስልኝ ይመስለኛል) ባለመደመጣችን የሆነው ሁሉ ሆነ - ምናልባትም መሆን ስለነበረበት ይሆናል። “ሁሉም ነገር በጉልበተኞች ሥር ነው፤ እነሱን የሚያሸንፍ ከየት ይመጣል?” ብለን ተስፋ አንቁረጥ። ኃይል የእግዚአብሔር እንጂ የጉልበተኞች አይደለምና ነገን እንደዛሬ አንየው፤ ትናንት ዛሬን አልነበረምና። እናም የእግዚአብሔርን ትግስት አሟጠው መለኮታዊ ጦርን የሚመዙ ብዙ ምድራዊ ሕዝባዊ ግብኣቶች እንዳሉ እንረዳ። የጭቁኖችና የድሆች ዕንባ የኒኩሌር ሚሣይል ነው፤ እርግማንም አቶሚክ ቦምብ የታጠቀ SU-27 ሚግ ጀት ነው፤ ሥልጣንን ለማቆየት ሲባል ባልተለመደ ሁኔታ በትግሬዎች መንግሥት ለርኩሳን መናፍስት የሚቀርበው የሰው ደምና አጥንትም መለኮታዊ ጦርን የሚመዝ አቤላዊ መስዋዕት ነው፤ ብናምንም ባናምንም አሁን ጽዋው ሞልቷል። ስለሆነም ቁናው እየተሰፋ ባለበት በዚህ ታካዊ ወቅት ላይ ሌላ ዙር የሕዝብ ማደንቆሪያ ከርቀት እያናፈሱ መጃጃልና ማጃጃል የበሉትን ዕቁብ ደግማችሁ ስጡኝ እንደማለት የለዬለት ሞኝነት ነው። አንዲት ትንሽ መዘናጊያ ልስጥና ፈገግ ብትሉልኝ ልሞክር። ፈገግታ ጥሩ ነው። እኔ እወዳለሁ። የናንተን እንጃ።

አንድ አጭበርባሪ ሌባ ከሚያውቀው ሰው ልብስ ይዋስና ከነክራቫቱ ቂቅ ብሎ አንድ ቡና ቤት ይገባል - በጁ ይዞ የገደላትን አንዲት ዝምብ በኪሱ ውስጥ አድርጎ ነው ታዲያ። ከዚያ ሆቴሉ ውስጥ ምሣውን ከመጀመሪያ ኮርስ እስከመጨረሻ ኮርስ ጣፋጭ ጭምር ግጥም አድርጎ ይበላል። መጠጥም አልቀረው። በመጨረሻው የዕለቱን ሜኖ የሚያዘውን የምሣ ላይ ሾርባ ያዝዝና ሲመጣለት በድብቅ የያዛትን ዝምብ ይጨምርበታል። በንዴት እየፎገላም አስተናጋጁን በአውራ ጣትና በቀለበት ጣት በሚደረግ የፍትጊያ ድምጽ እያጮኸ ይጣራል። “ይሄ ዝምብ ምንድን ነው? እኛ ትልልቅ ሰዎች ከስንትና ስንት ቦታ ነዳጅ እየጨረስን ወደዚህ የምንመጣው እኮ ደረጃውን የጠበቀ ሆቴል ነው ብለን ነው። በል ባለቤቱን ጥራልኝ!” ይላል። ትንሽ ላሳጥረው። ... ባለቤቱ ይመጣል “ጌታዬ ይቅርታ፣ የበሉትንም እንዳይከፍሉ። ስማችንን ብቻ ይጠብቁልን ...” ብሎ ያሰናብተዋል።

ይህ አጭበርባሪ ያደረገውን ሁሉ ለሌላ አጭበርባሪ ሌባ ጓደኛው ይነግረዋል። ያኛው ጓደኛም ቀጣዩ ቀን እስኪነጋና የምሣ ሰዓት እስኪደርስ ይቸኩላል - ልክ እንደጓደኛው የሞተች ዝምብ ይዞ ወደዚያ ሆቴል ሊገባና በነፃ ሊበላ። መመኘት ጥሩ ነው። አይከለከልምም።

ቀኑ አይደርስ የለም ደረሰ። ሁለተኛው ሌባ ሰውዬም ልብስ ተውሶ ዝምቡን በኪሱ ይዞ ወደ ሆቴሉ ምግብ ገባ። ያዘዘውን ሁሉ ተመገበ፤ ጠጣም። ሾርባውን ሲጠይቅ ግን ያች ነገረኛ ሾርባ ለዚያን ቀን አልተሠራች ኖራ “ጌታየ ሾርባ አልተሠራም!” ብሎ አስተናጋጁ ሲነግረው አጭቤው ሌባ ዕጢው ዱብ ይላል። ያኔም ነው “ታዲያ ይህችን የሞተች ዝምብ የት ላድርግልህ?” ያለውና በሆቴሉ አስተናጋጆች እንዳይሆን ሆኖ ተደብድቦ አውራ መንገድ ላይ የተጣለው። ነገሬ ይገባችኋል መቼም። ሥልት መቀየር ይገባ(ው) ነበር። የደንቆሮ ልቅሶ መሆን የለበትም። አንድ ሥልት አንዱን ማር ያበላል ሌላውን ደግሞ ሌላ። ስሙን ከፈለግህ አንተ ጥራው። ዓለም እንዲህ ናት፤ እንደወያኔ የቀናው ግን በዚህች ምድር አንድም የለም። ቢሆንም ደግሞ አያስቀኑም። ማጣፊያው ሲያጥራቸው እነሱን አለማየት ነው። በኢትዮጵያ ጉድ እየተንተከተከ ነው። ሲገነፍል አያሳየኝ፤ ከዚያ በፊትም ይውሰደኝ። የኔ ምኞት ነው።

የኢትዮጵያ ሕዝብ አቅሙም ዕውቀትና ችሎታውም ከሚችሉት በላይ በአሰለጦች ለዘመናት ተጭበርብሯል፤ ከክርስቶስ ባልተናነሰ በከሃዲ ጻፎችና ፈሪሣውያን ተወግሯል። በዐረመኔዎቹ ትግሬዎች በዚህ ዘመን እንደተሰቃየው ግን በውጭ ኃይሎች በየትኛውም ዘመን አልተሰቃየም፤ ይህን እውነት የሚክድ እግዚአብሔር ይካደው። ከሕዝቡ ንቃት እጅግ የወረደ ንቃትና የትምህርት ደረጃ ባላቸው ተራ ሽፍቶችና የጫካ ወምበዴዎች ሳይወድ በግዱ ተገዝቷል። አሁንና ከአሁን በኋላ ግን ጫንቃው ተላልጦ አልቋልና ምንም ዓይነት ጭቆና መሸከም የማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል - አንዳችም ርህራሄ የሌላቸው ቀማኞችንና የቀን ጅቦችን አዝሎ እሹሩሩ የሚልበት አንቀልባው ተበጣጥሷል። እናም እንኳንስ በዱሮው ምንሊክ ባልገባው ነገር የሚንገፈገፍና በዘንድሮው መለስም የሚምል ታሁን በኋላ ቦታ የለውም። የቀበሮ ባህታውያን ከንግዲህ በበጎች መሀል አይመላለሱም። የተኩላና የቀበሮ ዘመን አብቅቶ ኢትዮጵያዊ ዘመን ሊብት ነው። በፈጣሪ የምናምን ይደረግልናል ብለን የተስፋ ቃሉን እንጠብቃለን፤ ቃሉም ሥጋ ሊሆን ማለትም ወደ እውንነት ሊቀየር የቀረው ጊዜ በጣም አጭር ነው። አናንያን፣ አዛሪያንና ሚሣኤልን ከእሳት ያወጣ አምላከ ምሕረት ኢትዮጵያንም ዙሪያዋን ከተጠመደባት የጠላቶቿ ወጥመድ ነፃ ያወጣታል። ...

ለመሆኑ ምኒልክ ምን አደረጉ? ምኒልክ ማን ናቸው? የምኒልክ የዘር ሐረግ ከየት ነው? እናንብብ። በጭፍን ጥላቻ አንታወር። አፄ ምኒልክ ኦሮሞ ናቸው - አፄ ኃይለሥላሤ ኦሮሞ ናቸው - መንግሥቱም ኦሮሞ ነው። ኦሮሞ ደግሞ ኦሮሞን በቅኝ ግዛትነት አይዝም። ይህን አስተሳሰብ ማራመድ ተወዳዳሪ የሌለው ድንቁርና ካልሆነ ድንቁርና የሚባል ነገር ከናካቴው የለም ማለት ነው። አስቂኝ ትውልድ፤ አስቂኝ አስተሳሰብ። በዚያ ላይ ዛሬ 21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን እንጂ 18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አይደለም። ያ ሌላ ይሄ ሌላ። ጭቆና እንኳን ነበረ ቢባል የተጨቆኑና የጨቆኑ አሁን የሉም። ደግሞም ተጨቋቆኑ እንጂ እንዲህ እንደዛሬው አንዱ ዘውግ ተነስቶ በብቸኝነት አልጨቆነም። ታዲያ የአሁኑ መንገፍገፍና መርገፍገፍ ከምን የመጣ ነው? “የምታሸንፈውን ምታ ቢሉት ወደ ሚስቱ ሮጠ” ብሎ የተረተ ሰው ዘር ይውጣለት። የተያያዝነው ይህንን ነው። ወይም በገንዘብ ተገዝተን “እንዲህ አድርጉ፤ እንዲህ ስታደርጉ እንዲህ እናደርግላችኋለን” ተብለናል ማለት ነው። ታሪካዊ ጠላት ውሉን አይስትምና ሁሉን መጠርጠር ነው - ግን ደግሞ ሁሉም ያልፋል። ማለፍ ባይኖር ምን ይውጠን ነበር? ሳስበው ራሱ ይጨንቀኛል።

ራሳችንንም ሆነ ሕዝብን ለማሞኘት አንሞክር። አንዳች በሽታ ካለብን ወደሚቀርበን ጠበል ሄደን እንጠበል - ከዚያም ያለብን አጋንንት ጮኾም ይሁን ለፍልፎ ይውጣልን። በተረፈ “ምኒልክ ነጭ ነበር፤ ምኒልክ ኦሮሞን በድሏል፤ ....” የሚለው እንጉርጉሮና ሙሾ “ይቺን የሞተች ዝምብ የት ላድርጋት ታዲያ?” ብሎ እንደጠየቀው “አራዳ ሌባ” የሥልጣንና የሀብት ሥነ ልቦናዊ ጥማትን ለማርካት እንዲሁም የወያኔን መድከም ተከትሎ ቤተ መንግሥትን ባረጀ የትግል ሥልት ለመቆጣጠር ወረፋ እንደመያዝ የሚቆጠር ቀድሞ የተነቃበት አካሄድ ነው። ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አዝማሚያ ሌላ ነው። የመኖር ጥያቄ እንጂ የቅንጡ ዲያስፖራ የሥልጣን ኮርቻ ለመጫን የሚፈልግ አንድም የሕዝብ ፈረስ የለም። ይህን አለማወቅ ራሱ ድንቁርና ነው። ለዚህ ነው በትምህርት ውስጥ እንደሚገኝ ያለ ድንቁርና የትም የለም የምለው። ወያኔን ያዬ በዚህ የከረፋ የዘረኝነት አባዜ ሊጠመድ አይገባውም ነበር።

ፀጋየ የተባለው “ምሁር” ምን እንዳለ ቀጥለን እንይ። ያገኘሁት በተድላ ጽሑፍ ውስጥ ኢካድፍ ላይ ተለጥፎ ነው። የዚህን ሰውዬ ሕመም የሚረዳለት የቅርብ ዘመድ ካለ ሳይብስበትና አቅሉን ሳያስተው ይድረስለት። ዘመድ ለመቼ ነው? ኢትዮጵያን የተማረባትና ያደገባት መሆኑን ጭራሽ ረስቶ በአዲስ አገር ፍቅር ያበደ ይመስላል። ማበዱን ከወደደው ግዴለም ራሱ ብቻውንና ከፈለገም ከጥቂት ቢጤዎቹ ጋር ይበድ፤ አንድ ሰው መቼም መሆን የሚፈልገውን ሆኖ ሲያገኘው ይደሰታልና ከሚፈልገው “መሆን” የሚያደናቅፈውን ነገር ይጠላል። ግን ዜጎችን በአጃቢነት ለማሰለፍና ዕብደትን ለማስፋፋት የሚያደርገውን ሩጫ ማቆም አለበት። ከባሕርይ አባቶቹ ከቀደምት የትግሬ ወያኔዎች ይማር - ሳይኖሩ ከሞቱና ከሚሞቱ ወያኔዎች የማይማር ሰው ቢኖር ከእንስሳም የወረደ መጥፎ ተፈጥሯዊ ጠባይ ያለው ነው።

በተድላ ጽሑፍ ውስጥ የተጠቀሰው የአማራና የኢትዮጵያ ጥላቻ በግልጽ የሚንጸባረቅበት የፀጋየ መርዛማ ጥቅስ የሚከተለው ነው። የአማርኛውን ትርጉም ከግርጌው አስቀምጣለሁ።

“To say Menelik fought a black war of independence at Adwa is at best inaccurate and at worst a deliberate distortion of history intended to galvanize legitimacy for his rule and to print an image of a saint in the face of the need to acknowledge responsibility for his failings or the atrocities of the [Ethiopian] state he founded.”

“የዐድዋን ጦርነት በምንሊክ መሪነት የተካሄደ የጥቁሮች የነፃነት ጦርነት እንደሆነ ማመን በትንሹ በጣም ትልቅ ስህተት ሲሆን እጅግ ሲከፋ ደግሞ የሰውዬውን ዝናና ክብር በማጉላት እንዲሁም ያልተገባ ቅድስና በመስጠት ስህተቶቹን ለመሸፈንና ራሱ በፈጠራት አገር የሚኖሩ ሕዝቦችን ስቃይ ለመደበቅ ሆን ተብሎ የሚደረግ የታሪክ ጥመት ነው። ”

ያባቴ አምላክ ያጣምህ! ምን ዓይነቱ ጠማማ ሰው ነው እባካችሁ።

ወንድሞቼና እህቶቼ። ዐውቆ የተደበቀን ቢቀሰቅሱት አይሰማም። ዐውቃችሁ የተደበቃችሁትን አማራም ሆናችሁ ኦሮሞ ወይም የሌላ ነገድና ጎሣ አባላትን ለመቀስቀስ እንኳን ኃጢኣተኛው እኔ፣ ቅዱሱ እግዚአብሔር ራሱም የሚችል አይመስለኝም - በዚህ ረገድ ልደክም አልፈልግም። ዐውቆ የተኛን መቀስቀስ አስቸጋሪ ስለሆነ ይመስለኛል አይተ መለስ ዜናዊና አባቱ ሊቀ ኃጥኣን አባ ገብረ መድኅን ረጂም የንስሃ ዘመን ተሰጥቷቸው ያን እንኳን ባለመጠቀማቸውና አገርንና ሕዝብን በማጥፋቱ ልዩ ሙያ ላይ ተሠማርተው በስፋት በመቀጠላቸው ፈጣሪ በሚችለው ሩህን ከሥጋ የመለየት ጥበቡ በጊዜ የገላገለን። አሁንም ክራቸው የተፈተለ፣ ጉድጓዳቸው የተማሰ፣ ልጣቸው የተራሰ ብዙ ከፋፋይና ጭራቅ ዜጎች ስላሉ ለቀብር ሥነ ሥርዓቱ እንዘጋጅ። እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ምን ጊዜም ከአሣር እያወጣ ወደነበረችበት የክብር ማማ እንደሚመልሳት የታወቀ ነውና ተስፋ ሳንቆርጥ የነገሮችን አካሄድ እንከታተል። ግን እኛም ራሳችንን ከጥፋት መንገድ እንጠብቅ - እንዳንጠፋ እንጠንቀቅ። በኋላ ማቄን ጨርቄን የለም። ዋ! ብያለሁ።

ዐውቃችሁ ላልተደበቃችሁ የዋሃን ግን የምለው አለኝ። በማንም ስብከትና ወሬ እንደከብት አትነዱ። የራሳችሁ አዕምሮ፣ የራሳችሁ የማሰብ አቅም፣ የራሳችሁ ኅልውና አላችሁና በሰው ሣምባ እየተነፈሳችሁ በሰው ጭንቅላት አታስቡ። አጭር ልቦለድ ባቅሟ የረጂም ልቦለድ ቅጣይና ቅርንጫፍ እንዳልሆነች በባለሙያዎቹ እንደሚነገርላት ሁሉ እናንተም የራሳችሁ ሙሉ ስብዕናና የዕድሜ ዘመን ያላችሁ እኩል ዜጎች ናችሁ። ስለሆናችሁም ልደቱን በመሰለ አወናባጅ ሆዳም ከሃዲ፣ ፀጋየን በመሰለ ትምህርት ዘልቆ ባልገባውና ባልለወጠው እንዲያውም በተቃራኒው ትምህርቱ ወደቫይረስነት ተቀይሮ እንደኮምፒውተር ፋይል ኮራፕት አድርጎ ባደነቆረው ከፋፋይ ዘረኛ፣ ... ላለመነዳትና ከእውነት መንገድ ላለመውጣት ተጠንቀቁ። “ዕወቅ ያለ በ40 ቀኑ ያውቃል፤ አትወቅ ያለው በ40 ዓመቱም እንደደነቆረ ነው” ይባላል።

ከዚህ አኳያ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ብቸኛ ችግር ወያኔ ብቻ መሆኑን ተረዱ። ምሥኪን አማራ እንኳስ የችግር ምንጭ ሊሆን ራሱ የትግሬው ገዢ መደብ በደገሰለት እንደበርበሬ የሚተነትንና እንደእሳት የሚለበልብ የችግር ማጥ ውስጥ ተዘፍቆ መከራውን እያዬ ነው። በርግጠኝነት ግን በቅርብ ነፃ ይወጣል። ነፃ የሚያወጣውም እግዚአብሔር የባረካቸው የራሱ ልጆች ናቸው። ይህ ህልም ወይም ምኞት አይደለም፤ ራዕይ ወይም የመንፈስ መገለጥም አይደለም። በተግባር እየታዬ ያለ አስገራሚ ነገር ነው። ደግሞም ይህን አውቃለሁ - የሱዳን መተት፣ የህንድ መተት፣ የናይጄሪያ መተት ... የሚከሽፍበት ወቅትና አበቅቴ አለው። ለአብነት ያቺ ከሱዳን የመጣች ሆን ተብሎ ዐይኗ የጠፋ ጥቁር አህያ አርጅታ ከሞተች ከ2004 ዓ.ም. አካባቢ ወዲህ በመለስና በቤተ መንግሥቱ እንዲሁም በህወሓት ውስጥ በአጠቃላይ ምን ተዓምር እንደተፈጠረና እየተፈጠረም እንደሚገኝ አውቃለሁ። አዲስ አበባ ውስጥ ሜክሲኮ አደባባይን የዑደት ማዕከል አድርጎ በወየንቲ ሠራዊት እየታጀበና እየተጠበቀ ሌሊት ሌሊት በትግሬ ሴቶች ይደረግ ስለነበረው የከበሮና ማሲንቆ ጭፈራም አውቃለሁ። በቱጃሩ እንትና ኮንቴይነር ከህንድ ወደ ኢትዮጵያ ሳይፈተሹ ስለሚገቡ የቅልብ ዘንዶዎች ሟርትና ደንቃራም አውቃለሁ። ወያኔዎች በስንትና ስንት የሱዳን መተትና የምዕራባውያን የመረጃ ተቋማት የኢንተሊጀንስ፣ የሥልጠናና የገንዘብ ድጋፍ መላ ኢትዮጵያን እንደተቆጣጠሩ አውቃለሁ። ጎበዝ ይህ ነገር ተዓምር አይደለም - እውነት ነው፤ እውነትን ሁሉ ደግሞ በአምስት የስሜት ህዋሳት ብቻ አትደርስበትም።

ብዙነት ብቻውን ዋጋ የለውም። ጥቂትነትም አልፎ አልፎ ከብልጣብልጥነት ጋር ትልቅ ቦታ ሊያደርስ ይችላል። ጥቂት ወያዎች ይህን ሁሉ ጀብድ እንደሠሩ የምታምን ከሆነ ስህተት ነው - በእያንዳንዱ ጀብድ ውስጥ ብዙ ውስብስብ ነገሮች ሊኖሩ እንደሚችሉ ቢያንስ መጠርጠር አለብህ። ይህ ሁሉ ደግሞ የዓለም ሥራ ነው። ሥልጣንና ሀብት ከምን ጋር እንደሚያያዝ ለሚረዳ ይህ ዓይቱ ነገር አያስገርመውም። መጽሐፉ “አንቺ ባቢሎን ሆይ! መተትሽና ትብታብሽ ሁሉ በመጨረሻው አያድንሽምና ወዮልሽ!” ይላል። በትክክል ባልጠቅሰው በስንፍናየ ነውና ይቅርታ። ይህን ሁሉ የምለው ብዙዎች በጥቂቶች ሊታሠሩ የሚችሉበትን paranormal situations በመጠኑ ለመዳሰስ ነው። አንባቢን ተስፋ የማስቆረጥ ዓላማም የለኝም። ይልቁንም ጥንቃቄውን እንዲጨምርና እንዲያሰፋም ነው ተጓዳኝ መልእክቴ። በተረፈ የሁሉም ነገር ማለቂያ ያለው በመሆኑ የኛም ነገር በሁሉም ዘርፍ አልቆ ጫፍ ላይ ነን። የተሠራ የሚከሽፍበት፣ የተቀባበለ ጥይት የሚደነብሽበት ወቅት አለው። የኛን አገር ሁኔታም ስናጤን ይህ ጊዜ አሁን ነው። በዱር በገደል ያላችሁ የበቃችሁ ወገኖቼ በርትታችሁ ጸልዩ። ከ50 በመቶው በላይ የነፃነቱ ትግል ከናንተ ነው የሚጠበቀው። “እሾህን በእሾህ” እንዲሉ ደንቃራን በልባዊ ጸሎት መምታት ይቻላል።

ለማንኛውም አማራን አትጥሉት፤ የክፉ ቀን ወንድማችሁ ነው፤ በክፉ ቀን የሚደርስላችሁ ደማችሁ ነው። የዛሬውን ደግሞ አትዩ፤ ቀን ይለወጣል። ከማንኛውም ሕዝብ የበለጠ ቅድስናም ሆነ ርኩሰት የለበትም። እንዲጠላ ያደረጉትን እንወቅ። ገር ሕዝብ ነው፤ እንግዳ ተቀባይ ሕዝብ ነው። ከራሱ ይልቅ ለሌሎች የሚጨነቅ ሕዝብ ነው። ባህል ያለውና ወገኑን የሚወድ ሕዝብ ነው። አብሮ መኖርን፣ ተጋብቶ መዋለድን፣ ሰው ሰራሽ የልዩነት ድንበርን ተሻግሮ መስተጋብራዊ የጋርዮሽ ኑሮ መፍጠርን ያውቅበታል። ይህን ሕዝብ መጥላት፣ በዚህ ሕዝብ ላይ እየተፈራረቁ አርማጌዲዮንን ማወጅ ኩነኔ ነው፤ ወንጀልም ነው። ዋጋም ያስከፍላል። አለዚያማ እግዜር በመንበሩ የለማ!! ... የሰማ ሰማ።

“በል የተባልኩት”ን አደረስኩ። ትግሬ ሲነካ የሚንጨረጨሩና አካኪ ዘራፍ የሚሉ አንዳንድ የሌሊት ወፎች አማራን የሚሳደብና የሚወርፍ ጽሑፍ ሲደርሳቸው ግን በአንደኛ ደረጃ ዜናነት ያቀርቡታል። ይህንን ጽሑፍ እነዚህ ወገኖች አይወዱትምና እያወቅሁ አልክም። ለኔ ግን አንድም ሰው ቢሆን ካነበበልኝ ለምሥክርነት በቂየ ነው። ለዛሬ አበቃሁ። ሰላም ለኢትዮጵያ፤ ለእናንተም።

ተሻለ መንግሥቱ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!