(ትንታኔ)

በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ሠላም ለማስከበርና ለማስፈን በሚል በሁለቱ ሀገራት ድንበር መሃከል ሰፍሮ የነበረው የተባበሩት መንግሥታት ሠላም አስከባሪ ቡድን (አንሚ) ባለፈው ሐምሌ 23 ቀን 2000 ዓ.ም. ተልዕኮው መገባደዱን ገልጾ ከሰፈረበት ጥሎ መውጣቱ አይዘነጋም። የአንሚ ውሳኔ በርካቶችን ያሳሰበ ጉዳይ ከመሆኑም በላይ ሁለቱ ሀገራት ወደ ሠላም ወይንስ ወደ ጦርነት ነው የሚያመሩት? የሚል ጥያቄ አስከትሏል።

 

በአጠቃላይ በኢትዮጵያና በኤርትራ መሃከል በ1991 ዓ.ም. የተከሰተውን ጦርነትና ተያያዥ ጉዳዮች አስመልክቶ በሀገር ውስጥ የሚታተመው እንቢልታ ጋዜጣ በቅጽ 1፣ ቁጥር 34 ዕትሙ “ኢትዮጵያና ኤርትራ ወደ ሠላም ወይስ ወደ ጦርነት?” በሚል ርዕስ አንድ ትንታኔ አስነብቧል።

 

በዚሁ ትንታኔው ላይ የኢትዮጵያና የኤርትራ የድንበር ውዝግብ የመፍትሔ መሰናክል በሁለቱም ሀገሮች ላይ የዴሞክራሲያዊ መንግሥታት አለመኖር ነው ወደሚል መደምደሚያ መደረሱን ያትታል። ጋዜጣው የድንበር ኮሚሽኑና የአንሚ ፋይዳ፣ በኤርትራና በኢትዮጵያ ዳግም ጦርነት ይቀሰቀሳል?፣ ኢትዮጵያና ኤርትራ ጤናማ ግንኙነት ሊጀምሩ ይችላሉ? ለሚሉት ወሳኝ ጥያቄዎች የተለያዩ ወገኖችን በማነጋገርና የተለያዩ ጽሑፎችን በማጣቀስ ልዩ ትንታኔ ሰጥቶባቸዋል። (ይህንን ትንታኔ በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!)

 

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!