የቅንጅት አመራሮችን ከእስር በማስፈታት ኺደት የተሳተፈው የሽምግልና ቡድን፣ የኃይማኖት አባቶችንም እርስ በርሳቸውና ኦነግን ከመንግሥት ጋር ለማደራደር፤ ከኦነግ ጋር በተያያዘ በቁጥር ስር የዋሉ እስረኞችን ለማስፈታት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። በሌላ በኩል ኦነግን ከመንግሥት ጋር ለማደራደር ሦስት አባላት ያሉት ሌላ ቡድንም ተቋቁሟል። እነዚህ የሽምግልና ቡድኖች በሀገራዊው ተጽዕኖ ላይ ምን ዓይነት የፖለቲካ ድባብ ያሳድራሉ? ስትል የሚመለከታቸውን የተለያዩ ሰዎች የጠየቀቸው የእንቢልታ ጋዜጣ ዘጋቢ ጽዮን ግርማ ስትሆን፤ ጋዜጣው ይህንኑ ዘገባ ለንባብ አብቅቷል።

 

የፖለቲካ ውዝግቡና የሽማግሌዎቹ ሚና

“… አዲስ ዓመት በመጣ ቁጥር እስረኞችን የማስፈታት ባህል በኢትዮጵያ ስላለ ደርግ ከሥልጣን ወርዶ የሽግግር መንግሥት ሲቋቋም፤ እስረኞች ቢፈቱ የኢትዮጵያ መንግሥትን እንደሚያስመሠግነው በመግለጽ በ1984 ዓ.ም. ደብዳቤ ጽፈናል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮም ለመንግሥት የዘመን መለወጫ ሠላምታ ስንጽፍ፣ እስረኞች ምሕረት ተደርጎላቸው ቢፈቱ ለመንግሥት ከበሬታ ያስገኛል፣ እያልን ሳናሳስብ ያለፍንበት ጊዜ የለም። በ1990 ዓ.ም. የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ሲጀመር ግን ትኩረታችንን ወደዛው በማድረጋችንና ለመከታተል ባለመቻላችን ተቋርጦ ቆየ። በ1997 ዓ.ም. በተደረገው ሀገራዊ ምርጫ ግን በመንግሥትና በተቃዋሚዎች መካከል አለመግባባትና አለመተማመን በመፈጠሩ ያንን ተከትሎ ፓርላማ አንገባም በማለታቸው እኛም እኛና ሌሎች ሰዎች ያገኛችሁትን ድምፅ ይዛችሁ ብትገቡ ይሻላል የሚል ምክር መስጠት ጀመርን። የሽምግልና ኮሚቴው ጥንስስም የተጀመረው ፓርላማ ግቡ አትግቡ በሚል ከተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር በተያያዘ ሲደረግ በነበረው የተናጠልና የቡድን ውይይት ነው” በማለት ፕሮፌሠር ኤፍሬም ይስኃቅ የሽምግልና ኮሚቴውን አጀማመር አስመልክተው በ1999 ዓ.ም. ማጠናቀቂያ ላይ የገለጹት ይታወሳል። (ሙሉውን ዘገባ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!