አንባገነናዊነትን እያስታመሙ መቅበርም ይቻላል!

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active
Dictatorship

ያሬድ ኃይለማርያም

የአንባገነናዊ ሥርዓት ሞት ሁለት መልክ ያለው ነው። አንደኛው ከሱ የፈረጠመ ጡንቻ ባለው ወይም በሕዝባዊ አመጽ ድባቅ ተመቶ በሱ መቃብር ሌላ ጉልበተኛ ወይም ሕዝባዊ መንግሥት የሚሾምበት ሁኔታ ሲፈጠር ነው። ሁለተኛው ሞት ደግሞ እያዋዛ እና ረዥም ጊዜ የሚወስድ በረዥም ጣርና የስቃይ ጉዞ ውስጥ የሚመጣ ሞት ነው። በሰው ብንወስደው የመጀመሪያው በድንገተኛ አደጋ ወይም በቀናቶች ሕመም የሚሞት ሰው ሲሆን፤ ሁለተኛው ሞት ደግሞ እያንዳንዱ የሰውነት ክፍሉ አንድ በአንድ እየከዳውና ከጥቅም ውጭ እየሆነ በስቃይ ውስጥ ለተራዘመ ጊዜ ወይም ለዓመታት ቆይቶ የሚሞት ሰው ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢሕአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ማለት የሕወሓት የበላይነት ማለት ነው

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active
The Executive Council of the EPRDF

ብርሃኑ ጉተማ ባልቻ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በኢትዮጵያ ሕዝብ ያልተቋረጠ ትግልና በኢሕአዴግ ምክር ቤት ውስጥ የኦሕዴድንና የብአዴንን ሙሉ ድጋፍና ከደኢሕዴንም የተወሰነ ድጋፍ በማግኘት ጠ/ሚ ለመሆን ችለዋል። የሊቀመንበርነቱ ምርጫ በኢሕአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ቢሆን ኖሮ ዐቢይ ጠ/ሚ ለመሆን አይችሉም ነበር። ምክንያቱም የሕወሓት የበላይነት በኢሕአዴግ ምክር ቤት ውስጥ እየተወገደ ቢሆንም፤ በተቃራኒው ግን የሕወሓት የበላይነት በኢሕአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ውስጥ እንደቀጠለ ነው። የሕወሓትን የፖለቲካ አቅም ለመገንዘብ እነዚህን የኢሕአዴግ ሁለት ቁልፍ የፖለቲካ መዋቅሮች ማለትም የኢሕአዴግ ምክር ቤትንና የኢሕአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴን በሚገባ መረዳት ይገባል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወታደር ”በአማራ ማንነቴ ተጠቃሁ” ሲል ያናድዳል፤ ያበሳጫልም፤ ወታድርነቱ የት ገብቶ ነው?

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

አርሶ አደር ተገፋሁ ብሎ መሬት ቢጭር ያሳዝናል። መገፋቱም ያበሳጫል። ወታደር በአማራ ማንነቴ ተጠቃሁ ሲል ግን አያምርም!

ሸንቁጥ አየለ

በማኅበራዊ ሚዲያው ላይ ሰሞኑን የተለቀቀውን እና ወታደሮች በአማራ ማንነታቸው ጥቃት ደረሰባቸው የሚለውን መረጃ እያነበብኩ በጣም ገረመኝ። መገረምም ብቻ ሳይሆን ብዙ ጥያቄዎችም በሕሊናዬ ተመላለሱብኝ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በጎ ጅማሪዎችና ቀጣዩ ፈተና

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active
Dr. Abiy Ahmed

በቀለ ደገፋ

ዶ/ር ዐቢይ ጠ/ሚ ሆኖ ከተመረጠ በኋላ በበጎ የሚነሱና አንዳንዴም በዚህ ፍጥነት ይሆናሉ ተብሎ የማይጠበቁ ነገሮችን አድርጓል፤ የለማና የገዱ ከእሱ ያልተናነስ አስተዋፆ ሳይዘነጋ። ከእነዚህም ውስጥ ጎልተው የሚወጡት ስለኢትዮጵያዊነት መናገር እንደ ወንጀል መቆጠሩ ቀርቶ ሊኮራበት የሚገባና ብዙ ዋጋ የተከፈለበት መሆኑን ማሳየቱ፤ በኦሮሞ ወገኖቻችን ዘንድ የነበረውን አንዳንድ ጥርጣሬ አስውግዶ ኦሮሞ ከሌላው ሕዝብ እኩል መሥዋዕትነት ከፍሎ ባቆያት አገር ውስጥ ሆኖ የፍትሕና የእኩልነት ጥያቄውን ማስመለስ እንደሚችል ማሳየቱ፤ በፖለቲካ አመለካከታቸው ብቻ ለእስርና ለእንግልት የተዳረጉ ወገኖቻችንን ከእስር እንዲፈቱ ማድረግ፤ ለዚህም አንዳርጋቸው ፅጌን ከመፍታት የበለጠ ምንም ዐይነት ማስረጃ አያስፈልግም። አንዳርጋቸው ምንም እንኳን ምርጥ የፍትሕና የእኩልነት ታጋይ ቢሆንም፤ ከመረጠው የትግል መንገድ አንጻር እንዲፈታ መደረጉ በቀላሉ ሊታይ አይገባውም። ለለውጥ ያለውን ቁርጠኝነት ያመላክታል። ቂመኞቹ አሁንም ከአገር አንጋግተው ሊያባርሩት ሲያሴሩ ዶ/ር ዐቢይ በክብር ቤተመንግሥት ጠርቶ በማናገሩ ያልተደመመ ያለ አይመስለኝም። የታሰሩትን ከመፍታት በተጨማሪ በተፈበረከ የአሸባሪነት ክስ ለስደት የተዳረጉ ምርጥ ኢትዮጵያዊያንን ክስ ማንሳትና ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ጥሪ ማቅረቡ ሌላው ወሳኝ እርምጃ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጥብቅ ማሳሰቢያ ለጠ/ሚኒስትር ዐቢይ - እኔም በሀገሬ ያገባኛል!

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive
 Abiy Ahmed and Lemma Megersa

ምሕረት ዘገዬ

መረጃ አይናቅም። መረጃ ሁሉ በግርድፉ እንደ እውነት አይወሰድም። መረጃዎች እንደየምንጫቸው ሰውን/ተቋምን ለማሳሳት፣ ለማደናገር፣ ለማስፈራራት፣ ለማስጠንቀቅ፣ ለማሳወቅ፣ ወዘተ ... ይለቀቃሉ። ጥንቃቄ ማድረግ የሚያሻው መረጃ ተጠቃሚው ወገን ነው።

ጠ/ሚ ዐቢይ ሥራው የተቃና ይሆን ዘንድ፣ እኛም ዜጎች የሚታየንን ባሉን ማስንተፈሻዎች እንጠቁማለን፤ ሰሚ ካገኘን እሰዬው። ሰሚ ባናገኝ ቢያንስ ከኅሊና ወቀሳ እንድናለን። የሚነገሩ ሁሉ እውነት ሊሆኑ እንደማይችሉ ሁሉ፤ የሚነገሩ ሁሉ ሐሰት ሊሆኑም አይችሉም። የአንድ መሪም ሆነ ጉዳዩ የሚመለከተው ወገን ዋና ኃላፊነት እውነቱን ከውሸቱ አበጥሮ የመለየት ትልቅ ተግባር ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!