"ፍልሚያ" (ብሩክ ግዛው)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ብሩክ ግዛው (ከአዲስ አበባ)

ላለፉት አምስት ዓመታት ኢትዮጵያ ከ10 በመቶ በላይ ዕድገት ማሳየቷን መንግሥት በተለያየ ጊዜ እየገለፀ ይገኛል። እንዲያውም ዕድገቱ በዚሁ ከቀጠለ በቀጣዩ 15 እና 20 ዓመታት ውስጥ ዓመታዊ ገቢያቸው ከ765.00 ዶላር በላይ ወደሆኑት የመካከለኛው ገቢ ሀገሮች ትመደባለች ሲል አስረግጦ ተናግሯል። እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ሀገሬ በ20 ዓመት ውስጥ እንኳን ባይሳካ በ30 ዓመት ውስጥ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ተርታ መሰለፍ በቻለችና ህዝቦቿ ጠግበው ማደር ቢችሉ ምንኛ በተደሰትኩ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፀረ ሁሉም አቋም የት ያደርሳል? (አዕምሮ በለጠ)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

አዕምሮ በለጠ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. ) - የአንድነት አባል ከአዲስ አበባ

በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ብዛት ያላቸው ድረ ገፆችና ብሎጎች ብዙ ያጽፋሉ። የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች የአንድነት አመራር አባላት በአውሮፓ እያደረጉ ያሉትን የሥራ ጉብኝት የተመለከተና ጥሩ፣ ሚዛናዊና የራስን አመለካከት በመግለፅ መብት የተፃፉ፤ ግማሾቹ አንድ ፅንፍ ይዘው የሚጓዙ፤ በምክንያትና በጨዋነት ያልታነፁ ጽሑፎችን አንብበናል። እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ በውጭ ሀገር ያላችሁ ወገኖች የምትጽፉትን ከፍቶ ለማንበብ የተለያዩ ሰርቨሮችን መጠቀም ግድ ይላል። ምክንያቱም መንግሥት ስለሚያግዳቸው በቀላሉ ተከፍተው የሚነበቡ አይደሉምና። እንዲህም ሆኖ አግኝተን የምናነባቸው ብሎጎች ፅንፈኛና ለመፃኢ የሀገራችን ሠላምና ልማት፤ ብሎም አሁን ካለው የመጠላላትና የመወነጃጀል ፖለቲካ ፀድቶ አንድ ሀገርን ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት የሚያንኳስስ፣ ከገዢው የመከፋፈልና የአንባገነንነት አገዛዝና አስተሳሰብ ያልተሻለ፣ በዚያው የተቃኘ ሆኖ እናገኘዋለን።

ቡሩክ ኦባማና የአሜሪካ ምርጫ (ፕ/ር መስፍን)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

Prof. Mesfin Woldemariamፕሮፌሠር መስፍን ወልደማርያም

የኦባማ የምርጫ ዘመቻና የመጨረሻው ውጤት፣ የዓለምን በሙሉ ቀልብ የሳበ ነበር። ለምን? በብዙዎች የመገናኛ ብዙኃን በአሜሪካም ሆነ ከአሜሪካ ውጭ እንደ ምክንያት የሚሰጠው የቆዳው ቀለም መጥቆሩ ነው። በአሜሪካ ታሪክና ባህል ጥቁርነት ከባርነት ጋር ይያያዛል፤ ስለዚህም ኦባማ ለአሜሪካ ፕሬዝዳንትነት ሲወዳደር፣ በስተጀርባው የባርነትን ታሪክ አዝሎ እንደሆነ አድርገው ያቀርቡታል። ከባርነት መሠረት ተነስቶ ወደ አሜሪካ ፕሬዝዳንትነት መገስገስ ከፍ ያለ እምነትንና ድፍረትን ስለሚያመለክት ቀልብ የመሳብ ችሎታ አለው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ግራ የሚያጋባ ስንዴ (ዳንዴው ሠርቤሎ)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ከዳንዴው ሠርቤሎ

የገበያ ዋጋ ለማረጋጋት ተብሎ መንግሥት ከውጭ ገበያ ገዝቶ ያስገባው ስንዴ፣ በየቀበሌው ኩንታሉ በ350 ብር ሂሳብ እየተሸጠ ነው። ጥያቄው ግን ከዋጋ ማረጋጋት ያልፋል። የማግኘት ወይም የማጣት ጉዳይ ስለሆነ ግማሹ ለክፉ ቀን ያስቀመጠውን ስንቁን እያሟጠጠ ገዝቷል። ግማሹ ደግሞ ተበድሮም ተለቅቶም ሸምቷል። “ምን እንደሚመጣ አይታወቅም” እያለ በሥጋት ምክንያት ባገኘው ዋጋ ከተገኘው ገበያ እየገዛ አስቀምጧል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የድል መንገድ (ከቅዱስ)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ቅዱስ - This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

... ኢህአዴግ የማይወድቀው በጥንካሬው ሳይሆን በተቃዋሚዎች ድክመት ነው። ድክመቱ የአለመተባበር ብቻ ሳይሆን የራዕይ ድክመትም ነው። ኦባማ የዘረኝነትን እንቅፋት ጥሶ፣ በአሜሪካ ታሪክ ታይቶ በማያውቅ መልኩ ወጣቱን ያሳተፈ ፖለቲካ ፈጥሮ አሸናፊ የሆነው የተለየ እና አብላጫውን፤ በተለይም የወጣቱን ኃይል ስላሰለፈ ነው። ... ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሚዲያ ሚና በኢትዮጵያ ፖለቲካ (ዳንዴው ሰርቤሎ)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ዳንዴው ሰርቤሎ

ከአንድ ተቋም ግቢ ውጪ ለብዙ ህዝብ በጽሑፍ ወይም በኤሌክትሮኒክ መሣሪያ አማካይነት ለህዝብ እንዲደርስ የሚፈለገው መረጃ የሚተላለፍበትን መሣሪያ ”መገናኛ ብዙኀን” ብለን እንቀበል። አጠር ባለ መልኩ የውጭውን ቃል ተውሰን፣ ”ሚዲያ” ብንለው ደግሞ የሚያግባባን ይመስለኛል። ሚዲያው ህዝብን ለማስተማሪያ፣ ለማሳወቂያ፣ ለመቀስቀሻና ለማዝናኛ ዓላማ እንደሚያገለግል ይታወቃል። በዚህ ጽሑፍ ማተኮር የፈለግሁት በፖለቲካ ረገድ በሚጫወተው ሚና ላይ ሲሆን፣ በዓለም አቀፍና በሀገር ውስጥ ከታዘብኳቸው ሁኔታዎች በመነሣት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...