የአፍሪካውያን ተስፋ (ከፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ከፕሮፌሠር መስፍን ወልደማርያም (መስከረም ፳፻፩ ዓ.ም.) 

ጥንት ስለአፍሪካ ጥሩ ነገር፣ ጥሩ ተስፋ ብቅ የሚለው ከወደ ምሥራቁ በኩል ከኢትዮጵያ ነበር። የአፍሪካ ደቡቡ ገና የኢትዮጵያ የነፃነት ጮራ ሊፈነጥቅበት እየሞከረው ነበር። በኬንያና በታንዛንያ በኩል አድርጎ፣ በዛምቢያና በዚምባብዌ ወደ ዘረኛው የጎሣ አገዛዝ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሙቀቱንና ብርሃኑን ማሰማትና ማሳየት ጀምሮ ነበር። ኔልሰን ማንዴላ በጎረምሣነታቸው ወደ ኢትዮጵያ የመጡት የኢትዮጵያን የነፃነት ሙቀትና ብርሃን ፈልገው ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወደራሳችን እንመልከት (ከዳኛቸው ቢያድግልኝ)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

የተማርነው ከእውቀት እንድንርቅ አምባገነንነትንም እንድናከብር ነው

ከዳኛቸው ቢያድግልኝ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.  

ጤና ይስጥልኝ ወገኖቼ! ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ጉዳይ ይቅርታን ማን ይጠይቅ ይቅርታስ ለምን? በሚል ርዕስ በኢትዮሚድያ (http://ethiomedia.com/accent/sorry.pdf) ላይ ጽሁፍ አቅርቤ ነበር። ወደራሳችን መልከት ማድረግ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን በማማመን በጥልቅ ጉዳዩን አውቃለሁ እንደሚል ጠቢብ ሳይሆን እንደ ትውልድ ያገባኛል በሚል እምነት ለውይይት፣ ለትምህርት፣ መንደርደርያ እንዲሆን በማሰብ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ጥቂት ማለትን ስለመረጥኩ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“በሌለ ስም” ንትርክ (ሙሉ ካሣ)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ሙሉ ካሣ (ቶሮንቶ) This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.  

“… የሚያሳዝነውም የሚያሳፍረውም በአሁኑ ሰዓት በሚልዮን የሚቆጠር ህዝብ የሚላስ የሚቀመስ አጥቶ በረሃብ እየረገፈ ባለበት ወቅት ጎራ የለዩ ሁለት ቡድኖች ለጠገቡ ጠበቆች እስከ አሁን $20000 አፍስሰዋል። ወጭው ገና ይቀጥላል። ጎበዝ ይህን ኃላፊነት የጎደለውን እኩይ ተግባር የምትቀጥሉበት ከሆነ የወያኔ/ኢህአዴግን ተዕልኮ በማሳካት በኩል ላደረጋችሁት አስተዋጽዖ እና ለከፈላችሁት መስዋዕትነት ወያኔ/ኢህአዴግ በጀት እንዲመድብላችሁ የመጠየቅ መብት ያላችሁ ይመስለኛል። …”

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢዴአፓ “ልጓም ለቅቆ ቼቼ” (ከቃልኪዳን አምባቸው)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ከቃልኪዳን አምባቸው

ለፖለቲካ ንቃተ ኅሊና መፈጠር ገንቢ ሚና ከተጫወቱ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ ኢዴአፓ-መድህን በዋናነት ተጠቃሽ ነው፤ ከሀገራችን የፖለቲካ ፓርቲዎች በአብዛኛው በወጣቶች ተደራጅቷል የሚባለው ኤዴአፓ-መድህን፣ በምርጫ 97 ቅንጅትን ከፈጠሩ አራት ፓርቲዎች አንዱ በመሆን ፖለቲካውን ከማሟሟቁም በላይ፣ በተሣትፎ የሚያምን ፓርቲ ስለመሆኑም ተመስክሮለታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የመንፈሣውያን ማኅበራት ሀገራዊ አስተዋፅዖ (ከጊዜው ይታየው)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ከጊዜው ይታየው

"ማኅበረ ቅዱሳን በቤተክህነቱ ያገኘውን ቦታ፣ ያቀፋቸው አባላት ያላቸውን ሁሉን ዐቀፍ ዕውቀት፣ ያሰባሰበውን ብሔራዊ ተዋጽኦ፣ የዘረጋውን ዓለም አቀፋዊ መዋቅር ያህል በምሣሌነት ከላይ እንዳነሣናቸው ማኅበራት የጎላ ሀገራዊ አስተዋጽዖ አይታይበትም። ከኃይማኖት ክርክሮች፣ ከመጻሕፍት እና መዝሙሮች፣ ከጉባዔያት እና ስብሰባዎች ባለፈ ለሀገር ዕድገት እና ለህዝቡ ማኅበራዊ አገልግሎት መስፋፋት ብሎም ኅብረተሰቡን ለዕድገት በማነሣሣት ረገድ ዘገምተኛነት አስተውላለሁ።"

ከላይ ያለው "የመንፈሣውያን ማኅበራት ሀገራዊ አስተዋፅዖ" በሚል ርዕስ ጊዜው ይታየው ከፃፉት አስተያየት የተቀነጨበ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሙስና (ከፕ/ር ሰይድ ሐሰን)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

በመሪ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስና ፋይናንስ ዲፓርትመንት ውስጥ የኢኮኖሚ ፕሮፌሠር የሆኑት ዶ/ር ሰይድ ሐሰን "On the Menaing and Practical Implication of Corruption" በሚል ርዕስ ሙስንና አስመልክቶ በእንግሊዝኛ ያቀረቡት ጽሑፍ፣ ”የሙስና ትርጉም፤ ተዛማጅ ክስተቶቹና በሀገርና በህዝብ ላይ የሚያስከትላቸው ጠንቆች” በሚል ርዕስ ወደ አማርኛ ተተርጉሞ ለአማርኛ አንባብያን እንደሚከተለው ቀርቧል። መልካም ንባብ!

ሙሉውን አስነብበኝ ...