ከአሜሪካኖቹ ምርጫ አንድ ነገር ብቻ መማር በቂ ነው

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ሸንቁጥ አየለ

U.S. President Barack Obama shakes hands with Donald Trump

አሜሪካኖቹ የተዋጣለት ሥርዓት እና ተቋም በመገንባታቸው ብቻ የተለያዩ ውስብስብ እና አስቸጋሪ አስተሳሰቦችን እና ዕይታዎችን ይዘው የሚመጡ ፖለቲከኞችን ማስተናገድ የሚችል ሁኔታን፤ ብሎም አሜሪካ እንደ አገር የምትቀጥልበትን ጥልቅ መሰረት ጥለዋል። ለምርጫ ሲወዳደሩ ያለው ሂደት፣ ምርጫው ሲጠናቀቅ የሚያሳዩት የሠለጠነ ባህሪ እና የሥልጣን ሽግግሩ አስደማሚ ሂደት ሁሉ የአንድ ነገር ውጤት ነው። ተገቢውን ሥርዓት እና ተቋም በመገንባታቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለአዋጁ አዋጅ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ይገረም አለሙ

ኢትዮጵያውያን ለሃያ አምስት ዓመታት ባካሄድነው ትግል ከወያኔ አገዛዝ መላቀቅ አልቻልንም። በዚሁ መንገድና ስልት ቀጥሎም ከወያኔ አገዛዝ መላቀቅ እንደማይቻል ከመቼውም ጊዜ አሁን ግልጽ ሆኗል። ሕዝቡ በራሱ ተነሳሽነትና መንገድ ባካሄደው ትግልና እሱን ተከትሎ ወያኔ የወሰደው የአስቸኳይ ጊዜ ርምጃ በግልጽ ያሳየንም ይህንኑ ነው። ስለሆነም እስካሁን በተከተልነው አሠራርና በተጓዝንበት መንገድ ከወያኔ አገዛዝ ለመገላገል እንደማይቻል በመረጋገጡ ባልተሄደበት መንገድ ለመሄድ ይቻል ዘንድ ከሕዝቡም በኩል የአስቸኳይ ጊዜ ማወጅ አስፈላጊ ይመስለኛል። በዚህ የምትስማሙ ከዚህ በታች በቀረበው መነሻ ሃሳብ ላይ አስተያየት ስጡበት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከ“አማራ ይደራጅ” መፈክር ጀርባ …? ለጥሞና ውይይት

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

አመለ በየነ

በቅድሚያ ተማጽኖ፣

1. ትግሉ የሕዝብን የሥልጣን ባለቤትነት ለማረጋገጥ ይሁን!

ለራስ ሥልጣን አልሞ የሚደረግ ትግል ለምንይልክ ቤተመንግሥት አይደለም ለፓርላማ ወንበርም እንዳላበቃ አይተናል፣ አልተማርንበትም እንጂ ቤተ መንግሥት ደርሶም መገፍተር እንደሚያስከትል በኦነግ አይተናል፣ እናም ይቅር ተዉት፣

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሥርዓት ለውጥ በሥርዓት

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

Girma Seifu Maru. Photo TheGuardianግርማ ሰይፉ ማሩ

የሰሞኑን የካቢኔ ሹመት አስመልክቶ ብዙ አስተያየት እየተሰጠ ነው። አስተያየት መስጠቱ ትክክል ነው። በሕይወታችን ላይ ከፋም-ለማም ውሳኔ የሚያሳልፉ ሰዎች ምደባ በመሆኑ የመሰለንን አስተያየት መሰንዘር ተገቢ ይመስለኛል። በእኔ እምነት ኢህአዴግ ባልሆንን ሰዎች፣በተለይ ደግሞ የተሻለ አማራጭ ይታየናል፣ አለንም ለምንል ዜጎች ዋናው ጉዳይ የኢህአዴግ ፖሊሲ በምን ዓይነት ካቢኔ በደንብ ተግባራዊ እንደሚሆን መምከር አይመስለኝም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

”ጥልቅ ቅሌት”

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

WHO Director General Candidate Dr Tedros Adhanom.ወለላዬ ከስዊድን

ግብዝና አላዋቂ ሰዎች ጊዜና አጋጣሚ ፈቅዶላቸው በሥልጣን ላይ ሲቆዩ የእውቀትና የትልቅነታችው መጠን የት ድረስ እንደሚያደርሳቸው የሚገምቱበት ማስተዋል የላቸውም።

ሁሉንም የተካኑ፣ ለሁሉም ነገር ተመራጮች፣ ብልህና አዋቂዎች አድርገው እራሳቸውን ስለሚገምቱ ስህተት ላይ ይወድቃሉ።

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኃኖም ለዓለም የጤና ድርጅት ዳይሬክተርነት ለመወዳደር ቀርበው ያሳዩን ይሄንኑ የሚያመላክት ነው። አጠያያቂ ጉዳይ ግን አለ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“ጃዋር፦ ያልተናገረውን በተናገረው ውስጥ መስማት”

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

Jawar Mohammedታፈሰ ወርቁ

“ወያኔ አንድ ታንክ ከመግዛት፣ በ10 ሚሊዩን ዶላር አንድ ከፋፋይ አክቲቪስት መግዛት ትመርጣለች” መስፍን ፈይሳ ሮቢ

ጋዜጠኛ ምናላቸው ስማቸው በ“አፈርሳታ” ዝግጅቱ ጃዋርን አቅርቦ አነጋግሮት ነበር። ለጃዋር የቀረበለት አንዱ ጥይቄ “... የግንቦት ሰባት እና የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባርን ጥምረት እንዴት አየኸው?” የሚል ነበር። ጃዋር “... ቅን አመለካከት ነው ያላቸው ... ጥሩ ሙከራ እያደረጉ ነው ... ኢንቴንሽናቸው ቅን ነው ...” ብሎ በተናገረው ውስጥ “... በትክክል የተሠራ ግን አይደለም፣ የፖለቲካ ብስለት ያለበት ግን አይደለም” የሚል እና ያልተናገረውንም ነገር (between the lines) ትሰማለህ። ነገሩ “ከኛ ወዲያ ፉጭት አፍ ሟሞጥሞጥ ነው ...” ወይም “... ፖለቲካ ከኔ ወዲያ ላሳር ነው” የሚል ድምጸት አለው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!