ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

አንድ ጉድ ልንገራችሁ!

ያለፈው እኁድ የዱሮው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ ኢሰመጉ (ዛሬ በግድ ስምን ለውጦ ሰመጉ የተባለው) የሃያ አምስተኛ ዓመት በዓሉን ለማክበርና በዚያው እርዳታ ለመሰብሰብ በደሳለኝ ሆቴል የምሳ ግብዣ አዘጋጅቶ ነበር፤ ኢትዮጵያውያንም የውጭ ሀገር ሰዎችም ነበሩ፤ ፕሮግራሙ ሲካሄድ ቆይቶ አንድ ሰዓት ያህል ሲቀረው ፖሊሶች መጥተው ፕሮግራሙ እንዲቋረጥ አዘዙ፤ ተቋረጠና ወደየቤታችን ሄድን! ስብሰባው የተደረገው አስፈላጊው ፈቃድ ሁሉ በጽሑፍ ከተገኘ በኋላ ነበር፤ ምናልባት ፈቃጆቹና ከልካዮቹ አይተዋወቁም ይሆናል!

ይኸ በዶላር የሚገዛ የውሸት የትምህርት ማዕረግ ማሰብ አያስተምርም፤ በተፈጥሮም የማሰብ ችሎታ የሌላቸው በዚያ ሰፈር መጥፋታቸው ገና ብዙ ጥፋቶችን ያመጣል፤ በዚህ በግብዣው ጉዳይ፤

• አንደኛ ሰዓቱ አልቋል "መንግሥት ፈቅዶ ስብሰባው ተካሄደ፤" ቢባል "መንግሥት ስብሰባውን ዘግቶ ሰው ተበተነ፤" ከሚባል ሳይሻል አይቀርም፤

• ሁለተኛ ብዙ የውጭ ሀገር ሰዎች ነበሩ፤ ከልካዮች የእነዚህ የውጭ ሰዎች ታዛቢነት ጉዳትን አያስከትልም የሚል ግምት ነበራቸው ማለት ነው?

ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

ጥቅምት ፲፮ ቀን ፪ሺህ፱ (October 26, 2016)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!