(የማስጠንቀቂያ ጦማር፣ ቁጥር ፩)

ገሞራው - ዘስዊድን

ለማላከብርዎ ቀማተኛ ...

በዚህ ቀዳማዊ ደብዳቤዬ ላይ ብዙኃን ቁምነገሮችን ለማስፈር፣ እምብዛም አያመቸኝም። ሊመቸኝ ካልቻለበት ወይም ከማይችልበት ምክንያቶች ውስጥ ዓይነተኛውና ተቀዳሚው ስለርስዎ ስለቀማኛው ማንነት በዝርዝር ለማወቅ ባለመቻሌ ነው። ስለቤተሰብዎ መሠረት፣ ስለሶሻል ዕርከናዊ ደረጃዎ፣ ስለትምህርት ጣራዎ፣ ስለሥራ ክፍልዎ፣ ስለኑሮ ባህርይዎ፣ ... በዝርዝር ባውቅ ኖሮ፣ በሰፊው አሟልቼ እጅግ በሚያመረቃ አቀራረብ፣ በጽፍኩልዎ ነበር። የእርስዎን ገበናዊ ራዕይ በመላምት ጅምላዊ ትኩረት ሳይ ግን አንድ ነጥብ ፍንትው ብሎ በግልጽና በጉልህ ታይቶኛል።

 

የሰውን መብታዊ ድንበር በመጣስ፣ የሕግን ሉዓላዊ ሕንፃ በመናድ፣ የነፃነትን የሰዎችን ፀጋ በማርከስ፣ ... ከግልዎ ሀብትና ንብረት ውጭ በጊዜያዊ ትምክህትና በማንአለብኝ ዕብሪታዊ ውጥረት የሌላ ሰው ዐፅመ-ርስት መዝረፍዎ ነው። ድርጊትዎ ጥሩ ማጋለጫ ስለሚሆን ”ቢንጎ!” ብያለሁ። (ሙሉውን ጦማር በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

 

 

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!