የዘፈንና የሙዚቃ ኮታችን እንኳን አይጠበቅልንም?

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ምሕረት ዘገዬ (ከአዲስ አበባ)

Ginbot 20
የግምቦት 20 የሙዚቃ ምርጫ። (ምስል ቅንብር፣ ኢዛ)

ይህ በዓል የማን እንደሆነ አሁን ገና በደምብ ገባኝ! “ኢሕአዲግ” የሚባለው የሕወሓት መሀል-አገራዊ የሠርክ መጠሪያም የለየለት ቅጥፈት መሆኑን በዛሬዋ አጋጣሚ ይበልጥ ተገነዘብኩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአንበሳ ልጅ ሳለ የጅብ ልጅ ገነነ፣ አላስበላም አለ ጸጉሩ እየበነነ

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

ይገረም አለሙ

Lion vs Hyena
ጅቦች አንበሲትን ሲያሳድዱ

ነገር በምሳሌ
ጠጅ በብርሌ፣
ይሉ የነበሩቱ
አበው እና እመው እነዛ የጥንቱ፣
እንደ አሁኖቹ ቃላት ሳይደርቱ
ዙሪያ ጥምዝ ሄደው ነገር ሳይጎትቱ፤
በምሳሌ አዋዝተው በስንኝ ቋጥረው
በሁለት መስመር ቃል - ቅኔ ተቀኝተው፤
ምክረ ነገራቸው - ከጆሮ ደጃፍ ነጥሮ ሳይመለስ
ከውስጠ ልቦና ከአዕምሮ እንዲደርስ፤
አድርገው ነበረ የሚያስተላልፉት
ሳይወርሰው ቀረ እንጂ ይሄ ትውልድ ንቆት፤

አልፎ አልፎ ለጽሁፌ የአበውን አባባል የምጠቀመው በሁለት ምክንያት ነው። ዋናውና የመጀመሪያው ምክንያቴ አባባሉ መልዕክቱ ጥልቅ ይዘቱ ምጥቅ የሆነና ዘመን ባዘመነው ይሁን ባደነዘዘው የእኛ ብዙ ደቂቃዎች የሚወስድ አገላለጽም ሆነ ቢጻፍም ገጽ የማይበቃውን ነገር መረዳት ለሚችልና ለሚፈልግ ሰው በአጭር የሚገልጽ በመሆኑ ነው። ሁለተኛው ሥልጣኔ የራስን እየተዉ፤ በተውሶ ነገር መኮፈስ ማለት ይመስል እንኳን ለልጆቻውን ሊያስተምሩ ለራሳቸውም ወግ ባህላቸውን የአነጋገር ዘያቸውን እየረሱ ላሉት ወገኖች በእግረ መንገድ ማስታወስ ከተቻለ በሚል ነው። ፕ/ር አዱኛ ወርቁ ጥርት ባለው አገርኛ አነጋገር ሲናገሩ፤ ሰለጠን ባዮቹ ቢከፍቱ ተልባዎች ብዙ እንደሚሉ ባውቅም፤ እኔ ግን እንዴት እንደምኮራባቸውና እንደምቀናባቸው እኔና እኔ ነን የምናውቀው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በወያኔ ዘመን ቀልዶች ለአፍታ ፈገግ በሉ!

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ (ከአዲስ አበባ)

በወያኔ ዘመን ቀልዶች
በወያኔ ዘመን ቀልዶች ፈገግ በሉ!

አንጀት እያረረ እርሱ ስለሚስቅ ሊሆን ይችላል “ጥርስ ሞኝ ነው” ይባላል - እንደማሽላዋ። ቢሆንም አይብዛ እንጂ ቁም ነገርን እያዋዙ በቀልድ መሰል እውነተኛ ገጠመኞች ማስተላለፍ መጥፎ አይደለም። አንድ ስዕል በሺህ ቃላት ይመነዘራል እንደሚባል አንድ ቀልድም በአንድ መጽሐፍ ቢመነዘር ቀልዱ ከሚሸከመው ቁም ነገር አንጻር ቢያንስ እንጂ አይበዛበትም። እናም ዛሬ የማስኮመኩማችሁ የወያኔ ዘመን ቀልድ በጣም ሊያስቃችሁ ስለሚችል ለዐይን ማበሻ መሐረብ ወይም እራፊ ጨርቅ ይዛችሁ አንብቡ። ትግሬ የሆናችሁ ወገኖቼ ከዘረኝነት ፈንጣጣ ካልተሸለማችሁና እንደጤነኛ ሰው ማሰብ ካልቻላችሁ በስተቀር ልትናደዱና ልትቆጡ ትችሉ ይሆናል። መፍትሔው ታዲያ አለማንበብ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሳምንቴ ትዝብትና ትንግርት!

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

አስፋ ጫቦ (Corpus Chirsti, Texas, USA)

Donald Trump.
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ “አርብ ማታ ስዊድን የደረሰው አደጋ!” አለ። ስዊድኖቹ “እንዴት እኛ ሳናይ፣ ሳንስማ ትርምፕ ሰማ!” አሉና አሽሟጠጡት። ይህንን ዜና ያገኘው ከFox ነበር።

አሜሪካ ዛሬም በሁለንተናው ግምባር ቀደም ነኝ ስለምትል (“ያማ ያለፈ ወሬ ነው!) የሚሉ ሞልተዋል) በፕሬዚዳንቱ፤ በዶናልድ ትራምፕ፤ ልጀመር። ”የኔ ጠላት የአሜሪካን ሕዝብ ጠላት ነው”፣ “They are not my enmeies but the enemy of the American people) ብሎ አረፈው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያና አሜሪካ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ሙሉነህ እዩኤል

ኢትዮጵያና አሜሪካ ምን አገናኛቸው ትሉኝ ይሆናል። ነገሩ እንዲህ ነው፦ ባለፈው ሳምንት ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራም የሰባት አገሮች ዜጎች ወደ አሜሪካን አገር እንዳይገቡ እግድ ጥለው ነበር። ፕሬዝደንቱን ለዚህ ያነሳሳቸው እግዱ ከተጣለባቸው አገሮች የሚመጡ ዜጎች ለአሜሪካን ደህንነት የሚያሰጉ ሆነው ስላገኟቸው እንደሆነ ይናገራሉ፤ ብዙዎች ይህን ስጋት ባለመጋራት እገዳውን ቢቃወሙም። እገዳው ውሎ ሳያድር የዋሽንግተን ክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ የተከበሩ ጀምስ ሮበርት በሰባቱ አገሮች ዜጎች ላይ የተጣለው የጉዞ እግድ በዋሽንግተን ክልል ብቻ ሳይሆን በአሜሪካን በሙሉ እንዳይተገበር የሚል ብይን ይሰጣሉ። የእግድ እግድ መሆኑ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጻዕረ ሞትና መስፍን ወልደማርያም

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

Mesfin Woldemariam

አንደኛ፣ ገና በልጅነቴ አሥር ዓመት ግድም ሲሆነኝ አንድ በድቀድቂት ከእንጦጦ ወደታች የሚወርድ ኢጣልያዊና እኔ ተጋጠምን፤ እሱ በዚያ በጥቁር ድንጋይ ኮረት በረበረበበት መንገድ ላይ ሲጓዝ ወደእንጦጦ የሚወጣ ወታደሮችን የጫነ ከባድ መኪና ቆሞ ነበር። በዚያ መኪና ላይ አንድ ዝንጀሮ ነበር፤ የኔ አትኩሮት በዚህ ዝንጀሮ ላይ ነበር። እንደሚመስለኝ ዝንጀሮውን እያየሁ ስሮጥ ከድቅድቂቱ ጋር ተገናኘን፤ እኔ ከስር በተረበረበው የጥቁር ድንጋይ ኮረት ላይ፣ ድቅድቂቱ ደግሞ የእኔን ራስ ጨፍልቆ! ምኒልክ ሐኪም ቤት ከስንት ቀኖች በኋላ የካቶሊክ መነኮሳት አስታማሚዎች ከነመለዮአቸው አልጋዬ አጠገብ ቆመው በትልቅ የበሽተኞች ድንኳን ውስጥ በአንዱ መደዳ ውስጥ ተኝቼ ነቃሁ፤ መድኃኔዓለም ማንን ልኮ የእኔን ጭንቅላት ከድንጋዩና ከድቅድቂቱ መክቶ እንዳዳነኝ አላውቅም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!